Monday, October 18, 2010

ዳግማዊ ክህደት!!!!




የሆለታ 33ተኛው ዙር ምሩቅ የሆኑት ሻለቃ ተፈራ ወርቅ አስፋው በ1966 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ንቅናቄ ሲያደርግ የኢሃፓ አባል ነበርኩ በማለት ማውራት ይወዳሉ። ደርግ የህዝብን አብዮት ቀምቶ ስልጣን ላይ ሲወጣ ሻለቃው ተገልብጠው የሰደድ አባል ይሆናሉ። ለወታደራዊ ግዳጅ በተሰማሩበት የውጊያ ቀጠና ላይ ደግሞ ከሻብያና ከወያኔ ላይ ብር ተቀብለው ወታደሩ እንዲመታና እንዲበተን ካስደረጉ የጦር መኮንኖች መሃል እንዱ እሳቸው ነበሩ። ህዝብንና ሃገሪቱን ከጠላት ጥቃት እንዲጠብቁ በወታደራዊ ሙያ የሰለጠኑት ሻለቃ የሻቢያና የወያኔ ጦር እየገፋ ሲመጣ በቀውጢው ቀን ሰራዊቱን ክደው ተሰወሩ። ሻለቃ ተፈራ ወርቅ አስፋው ሃገርን ለመክዳት ከሻብያና ከወያኔ ጋር ጦር ሜዳ ለይ ድርድር በሚያደርጉበት ሰዓት ዳላስ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደግሞ

ቤተክርስቲያን ለማቋቋም ይመካከሩ ነበር። የህዝቡም ውይይት ፍሬ አፈራ። በአምላክ ቸርነት በሰሜን አሜሪካ ንብረትነቱ የኢትዮጵያውያን የሆነ የመጀመሪያውና ግንባር ቀደም ቤተክርስቲያን ተከፈተ። በአሜሪካ ውስጥ በተለያዩ ከተሞች ውስጥ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በምሳሌነት የሚጠቅስና ተስፋ ስጭ ደብር ለመሆን በቃ። እንደምታውቁት ወያኔ ስልጣን ላይ ሲወጣ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ተበተነ። ጉልበት የነበርውና የተመቸው ወደ ጎረቤት ሃገሮች ተሰደደ። ብዙዎች ታሰሩ፡ አብዛኛው ሰራዊት በሃገሩ ላይ የሚገባበት ቀዳዳ አጣ፡ ተራበ፤ ታረዘ፤ ለማኝ ሆነ። ሻለቃ ተፈራወርቅን በመሰሉ አድር ባዮች ጠቋሚነት አብዛኛው የሰራዊት አባል

በወያኔው ጀኔራል ጻድቃን ትእዛዝ ከተደበቁበት እንደ ድኩላ እየታደኑ ተረሸኑ። ሻለቃ ተፈራወርቅ ግን የወያኔ የዉስጥ አርበኛና ሰላይ ስለነበሩ አዲስ አበባ ከተማ ላይ ዋልያ ኢንሹራንስ ውስጥ ተመድበው እንዲሰሩ ይደረጋሉ። የጦር ባለሙያ ለመሆን የሰለጠኑት ሻለቃ ለወያኔ የሚሳነው የለም በአንድ ቀን ጀንበር የፋይናንስ ባለሙያ ተብለው የኢንሹራንሰ ሰራተኛ ለመሆን በቁ። ካመታት በኋላ የአሜሪካ

መንግስት ዲ.ቪ በሚባል ፕሪግራም ብዙ ኢትዮጵያውያን ማስመጣት ሲጀምር፤ ወያኔም ካድሬዎቹ በዚህ እድል ተጠቅመው ያልቻሉም እጣውን ገዝተው ወደ አሜሪካ እንዲገቡ ያስደርጋል። በሰሜን አሜሪካ ውስጥ ባሉ ቤተክርስቲያናት፤ በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበራት፤

በእድሮች፤ በእቁቦች፡ በሰንበቴ ማህበራት ውስጥ በአባልነት ተመዝግበው ያመራር ስፍራ እንዲይዙ ባለ ሃምሳ ሁለት 52 ገጽ የስራ መመሪያ ትእዛዝ ወያኔ ይሰጣቸዋል። የዚህ ፕሮግራም ተቀዳሚ ተግባር በውጭ ያሉ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን ለመበተንና ህዝቡን በሙሉ በወያኔ ቁጥጥርና ፕሮግራም መሰረት በሚዋቀሩ ድርጅቶች ውስጥ ብቻ ተሳትፎ እንዲያደርግ ለማድረግ ነው። ሻለቃ ተፈራወርቅ ቀደም ብለው ወደዚሁ ከተማ ከመጡት ባለቤታቸው ጋር ለመቀላቀል ዳላስ ከተማ ሲደርሱ የወያኔ ሰላዮች የኢትዮጵያን ኮሚኒቲ ተቆጣጥረው ስለነበረ እሳቸው ውደዚሁ ማህበር ውስጥ ገብተው ቀደም ሲል በተጀመሩት የወያኔ ድርጅቶች አማካኝነት ህዝቡን ማደንዘዝና ከትግሉ አላማ ህሊናውን የመስለብ ስራ ዉስጥ እንዲሳተፉ ይደረጋል። ሻለቃው የዳላስ ኮሚኒቲ ማህበር ሊቀ መንበር ሆነው

በሚሰሩበት ወቅት የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ባልደረባ የነበሩ ወታደሮች ከየመን ወደ ዳላስ ሲመጡ ኮሚኒቲው እርዳታ እንዲያደርግላቸው ሲጠየቅ እኝሁ ሻለቃ ስፖንሰር ሆኖ ላመጣቸው ድርጅት እነዚህን በጥባጭ የባህር ሃይል ወታደሮች ወደ አሜሪካ ማስመጣት አልነበረባችሁም ስህተት ሰርታችኋል በማለት አጥብቀው ሲከራከሩ ነበር። እነዚህም ወታደሮች ዛሬ ዳላስ ውስጥ አሉ። ምስክርነታችሁን ስጡ እንላለን። በዳላስ አካባቢ በወያኔ ካድሬዎች የተዋቀሩ ድርጅቶች የስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፡

1 የአማራ ልማት ድርጅት

2 የምእመናንና የካህናት ጉባኤ

3 ሆርን ኦፍ አፍሪካ ደቨሎፕመንት ኤንድ ፒስ

4 ኢትዮጵያን አሜሪካን ቻምበር ኦፍ ኮመርስ

5 ናሽናል አይ ባንክ ኦፍ ኢትዮጵያ

6 ወርልድ አሶሲኤሽን ኦፍ ፓሪሽነርስ ኦፍ ዘ ኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቸርች፡

7 ኢትዮጵያን ኮሙኒቲ ሊደርሽፕ ካውንሰል

8 ደጀን ፖለቲካል ግሩፕ

9 በትሩስ ዩዝ ፕሮግራም በመባል የሚታወቁ ድርጅቶች ናቸው።

እንደምትመለከቱት የኢትዮጵያን ኮሚኒቲ ተቆጣጥረው መጠነ ሰፊ ድርጅቶችን አቋቁመው ጨርሰዋል። በከተማው ውስጥ ያሉትንም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጆቶች ደጀን ለዲሞክራሲ በሚባለው ድርጅታቸው ውስጥ በማስገባት እኮላሽተዋቸዋል። ያም በመሆኑ ዛሬ ሃገራችን ላይ ህዝቡ የመምረጥ መብቱን ለማስጠበቅ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ላይ አጋር ሆኖ ለመቆም እንዳይችሉ ተደርገዋል። በአንጻሩም እነዚህ የወያኔ ካድሬወች የምእመናንና የካህናት ጉባኤ በሚባለው ድርጅታቸውና በአማራ ልማት ድርጅት እንደዚሁም በማህበር ቅዱሳን አማካኝነት ቤተክርስትያናችንን ለመበተን ባለ ሃይላቸው በመስራት ላይ ይገኛሉ። ሻለቃ ተፈራወርቅ በምእመናንና የካህናት ጉባኤ አማካኝነት ባለፈው የቤተክርስትያን የቦርድ ምርጫ ላይ ተሳታፊ ሆነው ነበር። የወያኔ ካድሬ መሆናቸውን ምእመኑ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ሳይመረጡ ቀሩ። እርሳቸውም እንዲህ ያለ ሽንፈት እንዲደርስብኝ ያደረገው በደጀን የፖለቲካ ደርጂት ዉስጥ ያቀፍኩት የኢህአፓ ድርጅት ነው ብለው ማስወራቱን በአደባባይ ተያያዙት። እንግዲህ በስውር ስሠራ የነበረው ስራ በህዝቡ ዘንድ ከታወቀ በይፋ መንቀሳቀስ አለብኝ ብለው ወሰኑ። የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ደብር መላከ ሳህል አወቀ ሲደልል የሚባሉ በዲፕሎማት ፓስፖርት የሚንቀሳቀሱ ያባ ጳውሎስ ካድሬ ካህን የሆኑትን ክስራ ሲያሰናብት ሻለቃ ተፈራወርቅ አስፋውና አቶ በትሩ ገ/እግዚአብሄር በነገሩ ዉስጥ ጣልቃ በመግባት አስር ሰው የሚገኝበት ኮሚቴ አቋቋሙ። በዚህ ኮሚቴ ውስጥ አቶ ተኮላ መኮንን እና አቶ ሃይሉ እጅጉ የሚባሉ ግለ ሰቦች በአባልነት ይገኙበታል። ደብሩን ለወያኔ ለመስጠት ካልሆነም ለመበተን ቀን ክሌት በመስራት ላይ ይገኛሉ። ይህ ደብር ሲመሰረት እነዚህ ሁለት ካድሬወች ኢትዮጵያ ውስጥ ህዝብ ሲያደሙ ነበር። ደብሩን ለማቋቋም ድንቡሎ ያልከፈሉ ሰወች ተልኳቸው ሃገርና ህዝብን መበተን ስለሆነ ዛሬም ዳግማዊ ከህደት ላይ ተሰማርተዋል። እዲስ ባቋቋሙት ኮሚቴ አማካኝነት የሚከተሉትን ስራወች ሰርተዋል።

1 ቤተክርስትያን ውስጥ በተደጋጋሚ ጊዜ ርብሻ አስነስተው መቅደስ አስደፍረዋል

2 ቤተክርስትያኑን የሚከስ ቡድን አቋቁመው በገንዘብ እየረዱ ይገኛሉ

3 ጉባኤ ጠርተው ተጨማሪ ኮሚቴ አቋቁመዋል። በዚሁ አዲስ ኮሚቴ ውስጥ ሻለቃው በድጋሜ ተመርጠው ገብተዋል።

4 በ 05/17/10 ዓ.ም. ፎክስ ቴለቪዥን (Channel 4 news) የውሸት ፕሮግራም እንዲቀርብ አስተባብረዋል።

ወደፊት እነዚህ የወያኔ ካድሬወች የሚሰሩትን ተንኮልና ስራ እየተከታተልን እናቀርባለን።

እግዚአብሄር ጽናትና ሃይሉን እንዲሰጠን እንጸልይ። አሜን!!