Friday, June 25, 2010

ለ (June 26 2010) ዓ.ም ስብሰባ የጠራው የአማራጭ ፈላጊ ኮሚቴ በሁለት ቡድን ተከፈለ!!! 
ከእናንተ አንዱ ክርስቲያን ከሆነው ወንድሙ ጋር ቢጣላ፣ ጉዳዩን የእግዚአብሔር ሰዎች በፍርድ እንዲያዩለት በማድረግ ፈንታ ለክስ ወደ አረማውያን የፍርድ ሸንጎ ለመሄድ እንዴት ይደፍራል? 1ኛ ቆሮ፡ 6፡1 
ታዲያ አንድ ክርስቲያን ሌላውን ክርስቲያን ከሶ ወደ አረማውያን ፍርድ ቤት መውሰድ ይገባዋልን? 1ኛ ቆሮ፡ 6፡6
August 18 2009 ዓ.ም
1 ከአገር ቤት በመጡ ንቡረእድ                  4 አቶ መስፍን ወልደየስ
2 አቶ ጌታቸው ወ/ሚካኤል                       5 አቶ ኪዳኔ አለማየሁ 
3 አቶ በቀለ ተክሌ                                  6 ወ/ሮ ጥሩአየር ፍስሃ
አማካኝነት በሰላምና በእርቅ ስም የተዋቀረው ኮሚቴ አንዴ የሰላም፤ የሽማግሌ፤ የእርቅ፤ አማራጭ ፈላጊ ኮሚቴ የሚል የተለያየ ስም እየተሰጠው በተለያየ ወቅት አባላቱን እየቀያየረ አዲስ ሃሳብ ያመጣ ለማስመሰል ቀደም ሲል የቀረበውን ሃሳብ እየለዋወጠ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ውስጥ አዲስ ክስ እየመሰረተ ይገኛል።
June 26 2010 ዓ.ም በጠሩት ስብሰባ ላይ
1 የዝህን ቡድን ስውር ደባ ውለው አድረው በተረዱና ከኮሚቴው ውስጥ ለመውጣት በወሰኑ የአመራር አባላት ምትክ ጉዳዩ በግልጽ ያልገባቸውን አድስ ሰዎች ለማስመረጥ
2 የአስተዳደር ቦርዱ ሊያነጋግረን ፈቃደኛ ስላልሆነ ለዚህ መፍትሄው ሌላ ክስ መስርቶ ቤተክርስቲያኑን ውጥረትና ኪሳራ ላይ ለመጣል የገንዘብ መዋጮ ማሰባሰብ ግንባር ቀደም አጅንዳቸው ነው።
ዉድ ምእመን ሆይ!
የአስተዳደር ቦርድ እንዚህ መጠነ ስፊ ስም ያላቸው ኮሚቴዎች እንደሚያስወሩት ምእመንን አላነጋግርም ያለበት ወቅት የለም። ቀደም ሲል አባል ከሆኑ ከኮሚቴው ተወካዮች ጋር በተደረገ ስብሰባ ላይ ቦርዱ ለመታረቅ ያቀረበው ሃሳብ የሚከተለው ነው።
1 ውይይት ለመጀመር ከሳሾች ክሳቸውን ያንሱ!
2 ቤተክርስቲያን ለክሱ ያወጣቸውን ገንዘብ ይተኩ!
3 ፍርድ ቤት ከሰው ያቀረቡትን ምእመን ይቅርታ ይጠይቁ የሚል ነበር።
በነዚህ ስመ ብዙ ቡድኖች በኩል የቀረበው ሃሳብ ደግሞ፡
1 ክሱን ለማቆም ወደ ፊት እንደራደራለን፡
2 ቤተክርስቲያኑ ለክሱ ያወጣውን ገንዘብ ቤተክርስቲያን የሚመጣ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንደ አባል ተቆጥሮ ድምጽ ይስጥበት፡
3 ክሱን ለማቆም በጊዜው የነበረው ቦርድ ወርዶ በውጭ ስወች ሞግዚትነት መተዳደር አለበት
4 አዲስ የቦርድ ምርጫ መደረግ አለበት።
5 አዲሱ ህግ ተሽሮ በድሮው ህግ መተዳደር አለበት።
6 ቤተክርስቲያን መጥቶ የሚሳለም ሰው በሙሉ እንደ አባል ተቆጥሮ ድምጽ የመስጠት መብት ይሰጠው። የሚሉ ነጥቦች ነበሩ። ውይይቱ ወደፊት ያልሄደው ከላይ በተጠቀሱት ነጥቦች ምክንያት እንጅ ኮሚቴወቹ እንደሚያናፍሱት ወሬ ቦርዱ አልወያይም ያለበት ጊዜ የለም።
ይህ ደብር የዚህ ሃገር መንግስት በሚፈቅደው ህግ መሰረት የተቋቋመ የራሱ መተዳደርያ ደንብ ያለው ቤተክርስቲያን ነው። በየጊዜው የሚመረጡ የአስተዳደር ቦርድ አባላት የመተዳደርያ ደንቡ በሚፈቅደው መሰረት መስራት ግዴታቸው ነው። አሁን ያለው አስተደአደር ቦርድም ከመተዳደሪያ ደንብ ውጭ የሰራው ስራ ካለ አባላት የመጠየቅ መብታቸው በዚሁ ህግ ላይ በማያሻማ ሁኔታ ሰፍሮ ይገኛል።
እውነቱ ይሄው ነው።
የሃሰት እድሜ አጭር ነው። እውነት ግን ለዘላለም ትኖራለች። ምሳሌ 12:19
 ወዳጄ ሆይ! ደጉን ምሰል እንጂ ክፉውን አትምሰል። ደግ ስራ የሚሰራ ሁሉ የእግዚአብሔር ነው። ክፉ ስራ የሚሰራ ግን እግዚአብሔርን አላየውም። 3ተኛ የዮሓንስ መለክት ቁጥር 11

Wednesday, June 23, 2010

እንደምን ከረማችሁ?

እንኳን ለአመቱ የሚካኤል ንግሠ በአል አደረሳችሁ!
የሰሞኑን አጫጭር ዜናወች እናቀርብላችኋለን። 
ሰብተምበር 25 2009 (September 25, 2009) ላይ የሽማግሌን ኮሚቴ በአዲስ መልክ ለማዋቀር ጅምሩ ቀጥሏል በማለት መጻፋችን አይዘነጋም። ይሄው ኮሚቴ (June 22, 2009) ዓ.ም ላይ በዳብለትሪ ሆቴል ተሰባስቦ ያዋቀረው ኮሚቴ አንደኛ ዓመቱን አከበረ። ለበዓሉም ድምቀት ይሰጠው ዘንድ “ የዓርብ ጉባዔ በአዲስ መልክ ተጀመረ፡፡ ብለው በደብራችን አጠገብ በሚገኘው የኬንያውያን ቤተ ክርስቲያን ላኛው አዳራሽ ውስጥ ስብሰባ ጀምረዋል”።
አቶ ሃይሉ እጅጉ ይሄንኑ የኬንያውያን ቤተክርስቲያን ገዝቼ ለዚሁ ቡድን እሰጣለሁ ሲሉ ተሰምቷል። ቤተክርስቲያኑንም በቅዱስ ሚካኤል ስም እንደሚሰይሙት የደረሰን ዘገባ ይጠቁማል። እኝህ በፍትዎኦት እና በንዋይ ልባቸው የታወረ ግለሰብ ለዝና እና ለርካሽ ወሬ ካልሆነ በስተቀር ገንዘብ ያወጣሉ ተብሎ አይጠበቅም።
ታዛቢዮች ይህ ደርጊት፤ለአቶ ሃይሉ እጅጉ ከመድሃኔአለም ት/ቤት ባሻገር የነበረችውን የጉለሌዋን የቡና ቤት እመቤት እና የቦሌዋን ወ/ሮ ጽጌን እስከነ ልጃቸው የመደባለቅን ያህል ቀላል ታስክ(Task)እንደማይሆንላቸው ይገምታሉ። እኛ በበኩላቸን ግን መልካም እድል እንመኝላቸዋለን።
ሁላችሁም እንድምትመለከቱት ግልጽ እየሆነ የመጣው የቀድሞው የቦርድ አባላት እና ክኋላ ሆነው ችግሩን ሲገምዱ የነበሩት አቶ ጌታቸው ትርፌና ቤተሰቦቻቸው ግንባር ቀደም የኮሚቴው መሪ ሆነው መቅረባቸው ነው። ቤተክርስቲያን ላይ ፐቲሽን አልፈርምም ብለው ሲገዘቱ የነበሩት ወ/ሮ አዜብ ዛሬ ግንባር ቀደም አስፈራሚ ናቸው።
አቶ ሃይሉ አራጋውም ደጀ ሰላም ውስጥ በግልጽ ሽማግሌ ጠልፈው ለመጣል ውንጀል ሲፈጽሙ ታይተዋል። ከዛም አልፈው በሚካኤል በዓል ላይ የድምጽ ማጉያውን ለማበላሸት ሲሯሯጡ ብዙ ምእመን አይቶ ታዝቧቸዋል። የገንዘብ መቀበያ ኮምፒተሩንም እንዳበላሹት መረጃ አለ። በነጻ ለበረከት ተብሎ ለሚሰጥ ግልጋሎት ቦታውን አለቅም ብሎ አምባጓሮ መፍጠርን ምን አመጣው?
በሌላ በኩል ሰሞኑን ከተማችኝ ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ ለሚተላለፍ TV እርዳታ ለመሰብሰብ ጉባኤ መደረጉ ይታወሳል።
የሆለታው ሻለቃ ተፈራ ወርቅ በዚህ ስብሰባ ላይ አልተገኙም ነበር።ስራቸው ኢትዮጵያን ማድማት የኢትዮጵያ የሆኑትን ተቋማት ማፍረስ ስለሆነ ለ June 27 2010 ሚካኤልን ለማፍረስ በጠሩት ስብሰባ ቀድመ ዝግጅት ለማደረግ ጎንበስ ቀና ሲሉ ጊዜ አጥሯቸው እንደሆነ ይገመታል።
ለዛሬው በዚህ ይብቃን! 
ቸር ይግጠመን! አሜን!

Friday, June 11, 2010

ቤተክርስቲያናችን ወደት እየሄደች ነው?
ይህንን ጥያቄ የጠየቁት ወ/ሮ አዜብ ኅይለማርያም ናቸው። ወ/ሮ ፈትለወርቅ ጎላ በምርጫ በተሸነፉበት ጌዜ ለወዳጆቻቸው በሙሉ ያቀረቡት ጥያቄ ነበር። ጊዜም ሳያጠፉ በምርጫው ከተሸነፍን አበራን እና ዶ/ር ግርማን ሌባ ብለን ወንጅለን ህዝቡን በማስቆጣት አነሳስተን ያቀረቡትን ሪፖርት እንኳን ለምእመኑ ሳያቀርቡ ለማባረር ተብሎ በተቀነባበረው ሴራ ውስጥ ያጣሪ ኮሚቴ ሆነው ገቡ። በዚህ ኮሚቴ ውስጥም አቶ ኪዳኔ ምስክር አብሯቸው እንዲገቡ የጠቆሙት እኝህ ወ/ሮ ነበሩ። አቶ ኪዳኔ ምስክር ከባለቤታቸው ከወ/ሮ ጥሩአየር ፍስሃ ጋር ቤተክርስቲያንን የከሰሱ፤ የዲያቆን አለማየሁ አጎትና የቦርድ አባል በነበሩበት ወቅት ወደ ሃያ ሽህ የሚጠጋ ብር ከቤተክርስቲያኑን የዘረፉ ናቸው።
ወ/ሮ አዜብና አቶ እዮኤል ነጋ አዴስ የተመረጡትን የቦርድ አባላት የተተራመሰውን ቦርድ መስመር እስከምናሲዝ ድረስ ስራቸውን እንዳይጀምሩና የድሮዎቹ እንዳሉ እንዲቀጥሉ ለማድረግ ያደረጉትን ጥረት ማን ይዘነጋዋል? ጥረታቸው መክሸፉን ሁላቸንም ያየነው ጉዳይ ነው።
ቄስ ነኝ የሚለው አወቀ ሲደልል በሰራው ሃጢያት ከቤተ ክርስቲያን ሲባረር ቤተክርስቲያን ላይ ሁከት የፈጠረው ቡድን
1  የወያኔ ድርጅት መስራች የሆኑት ያቦ ጸሃየ ቤተሰብና የሟቹ የትግራይ ልማት ድርጅት ሃላፊ እህቶች
 ሀ   ወ/ሮ  የሽ ዘሪሁን
 ለ   ወ/ሮ  ሶፊያ ዘሪሁን
2     የወያኔው መሪ  የአቶ መለስ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ጎላ ቤተሰቦች
ሀ    ወ/ሮ   አዜብ ኅይለማርያም
ለ    አቶ   ጌታቸው ትርፌ
3   ማህበረ ቅዱሳን
4    የወያኔ አባላት እና ደጋፊወች እንደነበሩ ሁላችንም እናስታውሳለን።
ሚካኤል በጥበቡ ይህንን ደባ ሲያከሽፍ ወደ ፍርድ ሸንጎ ተሯሩጠው ነጎዱ። በየቦታውም ጸረ ቤተክርስቲያን ስብሰባወች አካሄዱ። ቤተክርስቲያን የማዘጋት ህልማቸውም ከሸፈ።
ወ/ሮ  አዜብ ግን ትግላቸውን በመቀጠል
1    አቶ   እዮኤል ነጋ   ከእግዚአብሄር ቤት በገዛ ፍቃዱ የኮበለለ፤
2    ወ/ሮ  ፈትለወርቅ ጎላ፤
3    አቶ  ሃይሉ አራጋው   በውሸት ብዛት ምላሳቸው የተቆለፈ፤ በቴፕ ሲቀዱ የነበረውን የቤተክርስቲያን ሰነድ እስከዛሬ ያላስረከቡ፤
4    ሻምበል  ግዛው ገድሉ   ከማህበረ ቅዱሳን ጋር በመሆን ብዙ መቶ ሽህ ብር በላይ ቤተክርስቲያኒቱን ያራቆተ፤
5    አቶ   ኪዳኔ ምስክር  ከባለቤታቸው ጋር የቤተክርስቲያን ከሳሽና ብዙ ገንዘብ ያባከኑ፤
6    አቶ ጌታቸው ትርፌ   ከቀድሞው ቦርድ ጀርባ በመሆን ለደረሰው ጥፋት ሁሉ ግንባር ቀደም አማካሪና አስተባባሪ። ሃሰተኛ ኦዲተር ለቦርድ አቅራቢ፤
7   ሻለቃ ተፈራወርቅ   ቤተክርስቲያኑን የሚከሱና የሚወነጅሉ ሽማግሌዎች ነን የሚሉ ያባ ጳዉሎስ ተወካዮች ግንባር ቀደም አስተባባሪ። አሁንም እንሸመግላለን ስብሰባ ለማድረግ ፐቲሸን አለኝ ብለው ማቅረብ አቅቷቸው June 27 ስብሰባ የጠሩ በዛ ላይ የሚገኘውን ሰው ስም ዝርዝር  ይዘው ለመቅረብ በዝግጀት ላይ ያሉ፤
8   አቶ በትሩ  ቤተክርስቲያኑን የሚከሱና የሚወነጅሉ ሽማግሌዎች ነን የሚሉ ያባ ጳዉሎስ ተወካዮች ጋር የሚዶልቱ፤
ለአብነት ስማቸው ከላይ የተጠቀሱትን ግለሰቦች ከነባለቤቶቻቸው በማስተባበር በህግ የተቋቋመውን ቦርድ አዉርደው ሌላ ቦርድ ለመመስረት በመሯሯጥ ላይ ይገኛሉ።
የመሪነቱን ቦታ አንለቅም ተብሎ ይሄ ሁሉ ትግልና መሰሪነት የሚካሄደው እውነት  ለቤተክርስቲያን ደህንነት ታስቦ ይሆን ወይስ ሌላ የተሸፈነ አጀንዳ ይኖር ይሆን? እና ወ/ሮ አዜብ ቤተክርስትያናችንን ወዴት እየወሰዱት ነው?
መልሱን ለናንተ ለውድ ቤተክርስቲያን ወዳጆች እንተዋለን።
አምላካችን ለቤተክርስቲያናቸን የሚበጀውን ተግባር ይለግሰን አያልን ጸሎታችንን አናቀርባለን።
አምላክ በቸርነቱ ከዚህ ሁሉ ፈተና ያድነን።
ሁላቸንንም ለንስሃ ያብቃን
አሜን! አሚን1 አንበል!!!!!