Wednesday, June 23, 2010

እንደምን ከረማችሁ?

እንኳን ለአመቱ የሚካኤል ንግሠ በአል አደረሳችሁ!
የሰሞኑን አጫጭር ዜናወች እናቀርብላችኋለን። 
ሰብተምበር 25 2009 (September 25, 2009) ላይ የሽማግሌን ኮሚቴ በአዲስ መልክ ለማዋቀር ጅምሩ ቀጥሏል በማለት መጻፋችን አይዘነጋም። ይሄው ኮሚቴ (June 22, 2009) ዓ.ም ላይ በዳብለትሪ ሆቴል ተሰባስቦ ያዋቀረው ኮሚቴ አንደኛ ዓመቱን አከበረ። ለበዓሉም ድምቀት ይሰጠው ዘንድ “ የዓርብ ጉባዔ በአዲስ መልክ ተጀመረ፡፡ ብለው በደብራችን አጠገብ በሚገኘው የኬንያውያን ቤተ ክርስቲያን ላኛው አዳራሽ ውስጥ ስብሰባ ጀምረዋል”።
አቶ ሃይሉ እጅጉ ይሄንኑ የኬንያውያን ቤተክርስቲያን ገዝቼ ለዚሁ ቡድን እሰጣለሁ ሲሉ ተሰምቷል። ቤተክርስቲያኑንም በቅዱስ ሚካኤል ስም እንደሚሰይሙት የደረሰን ዘገባ ይጠቁማል። እኝህ በፍትዎኦት እና በንዋይ ልባቸው የታወረ ግለሰብ ለዝና እና ለርካሽ ወሬ ካልሆነ በስተቀር ገንዘብ ያወጣሉ ተብሎ አይጠበቅም።
ታዛቢዮች ይህ ደርጊት፤ለአቶ ሃይሉ እጅጉ ከመድሃኔአለም ት/ቤት ባሻገር የነበረችውን የጉለሌዋን የቡና ቤት እመቤት እና የቦሌዋን ወ/ሮ ጽጌን እስከነ ልጃቸው የመደባለቅን ያህል ቀላል ታስክ(Task)እንደማይሆንላቸው ይገምታሉ። እኛ በበኩላቸን ግን መልካም እድል እንመኝላቸዋለን።
ሁላችሁም እንድምትመለከቱት ግልጽ እየሆነ የመጣው የቀድሞው የቦርድ አባላት እና ክኋላ ሆነው ችግሩን ሲገምዱ የነበሩት አቶ ጌታቸው ትርፌና ቤተሰቦቻቸው ግንባር ቀደም የኮሚቴው መሪ ሆነው መቅረባቸው ነው። ቤተክርስቲያን ላይ ፐቲሽን አልፈርምም ብለው ሲገዘቱ የነበሩት ወ/ሮ አዜብ ዛሬ ግንባር ቀደም አስፈራሚ ናቸው።
አቶ ሃይሉ አራጋውም ደጀ ሰላም ውስጥ በግልጽ ሽማግሌ ጠልፈው ለመጣል ውንጀል ሲፈጽሙ ታይተዋል። ከዛም አልፈው በሚካኤል በዓል ላይ የድምጽ ማጉያውን ለማበላሸት ሲሯሯጡ ብዙ ምእመን አይቶ ታዝቧቸዋል። የገንዘብ መቀበያ ኮምፒተሩንም እንዳበላሹት መረጃ አለ። በነጻ ለበረከት ተብሎ ለሚሰጥ ግልጋሎት ቦታውን አለቅም ብሎ አምባጓሮ መፍጠርን ምን አመጣው?
በሌላ በኩል ሰሞኑን ከተማችኝ ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ ለሚተላለፍ TV እርዳታ ለመሰብሰብ ጉባኤ መደረጉ ይታወሳል።
የሆለታው ሻለቃ ተፈራ ወርቅ በዚህ ስብሰባ ላይ አልተገኙም ነበር።ስራቸው ኢትዮጵያን ማድማት የኢትዮጵያ የሆኑትን ተቋማት ማፍረስ ስለሆነ ለ June 27 2010 ሚካኤልን ለማፍረስ በጠሩት ስብሰባ ቀድመ ዝግጅት ለማደረግ ጎንበስ ቀና ሲሉ ጊዜ አጥሯቸው እንደሆነ ይገመታል።
ለዛሬው በዚህ ይብቃን! 
ቸር ይግጠመን! አሜን!

No comments:

Post a Comment