Friday, October 30, 2009

እርምጃ መዉሰድ አስፈላጊና ማብታችን ነዉ!!!
እንድታዉቁት ያህል!
ካሁን ቀደም የቦርዱ ሊቀ መንበራችን ቤተ ክርስቲያናችንን ላባ ፓዉሎስ ሊሸጥ ተስማምቶ አቡነ
ቆስጦስን ለማስመጣትና ለማስረከብ ተደርሶበት እንዳልተሳካለት ስንነግራችሁ ልታምኑን
ያልቻላችሁ ሁሉ ለነ አቶ አፈ ቀላጤወች ትልቁ ማስተማኛ ይሄዉላችሁ።
ይሄዉ ሊቀ መንበር ጥር ስላሳ አንድ ላይ ያወጀዉን የቦርድ አዋጅ በመጀመሪያ ቤተ
ክርስቲያናችን ገለልተኛ ነች በተከታይ 501 c ያላቸዉ ቡድንም ሆነ ማንኛዉም ማህበር የቤተ
ክርስቲያኑ መምበር አይሆንም እያለ ይሄዉላችሁ እራሱ ህጉን እየጣሰና እራሱን ብቻ ሳይሆን
የቦርድ ግብረ አበሮቹንና የግል ጓደኞቹን እነ ዶክቶር…. እነ አቶ… እያዋረደ ነዉ።
(ስልካቸዉን ላባ ፓውሎስ በጻፈው ደብዳቢ ላይ ይገኛል)
በጣም የሚገርመዉ እኝህ ዶችቶር ጓደኛዉ አለም አቀፍ ድርጂት ሲሰሩ ኖረው አርፈው ያለ
ምንም ጭቅጭቅ ጡረታቸዉን እግዚአብሄርን እያመሰገኑ በመኖር ፋንታ እዚህ ቁማርተኛ ነጋዴ
እኩያቸዉ ያልሆነ ሰዉ ጋር ዶልተው የሰዉ ስም ሲያጠፉ እየታዩና ቤተ ክርስቲያን ለመሸጥ
እያስማሙ መሆናቸዉን ለአባ ፓዉሎስና ለአዲስ አበባዉ ሲኖድ እንጠቅሳለን “እኛ በዓለሙሁሉ
ተሰራጭተን የምንገኝ ተባባሪዎች” በማለት መማጠናቸዉን እራሳችሁ አንብቡ።
በተደጋጋሚም ልንገልጽላችሁ የምንፈልገዉ አቶ ሊቀ መንበርና እነዚሁ ጓደኞቹ የቴክሳስ ቀረጥ
ነጻ ግብር ክፍያ 501 c አዉጥተዉ ገንዘብ እየሰበሰቡ መሆናቸዉን ላላወቃችሁ ሁሉ እውቁ
እንላለን።
እኝሁ ዶክቶር ጓደኛዉ ባለፈዉ ጥቂት ስብሰባ ላይ ይሄዉ ሰነድ ሲነበብ ሊቀ መንበሩ እኮ የጻፈው
በግሉ ነዉ በማለት ሃፍረታቸዉን ተጎናጽፈዉ ሄደዋል።
አፈ ቀላጤዉም ይሄ ድርጊት አዋራጅ መሆኑን ተመልክቶ አቶ ሊቀ መንበር ይሄን አይጽፍም
እያለ በሃይል ቃል ሲያስተባብል መዋሉን ልንገልጽላችሁ እንወዳለን። ይህንኑ ግለ ሰብ ጓደኛችንን
የዎያኔው ተጠሪ በዳላስ ከተማ ያሉት የቤተ ክርስቲያኑ አስተናጋጅ ኮሚቴ ዋና ሹምና የሊቀ
መንበሩ ብቻ ሳይሆን የማህበረ ቅዱሳን ደጋፊ ዉስጠ ሚስጥሩን ሳይነግሩት በየ ስብሰባዉ ላይ ሁሉ
እንዲጋፈጥ አድርገዉታል።
እጥብቀን ይህን ጓደኛችንን የምንመክረዉ ለነሱ ስትል ስምህን አታጥፋ ነው።
በተጨማሪ ልናሳስባችሁ የምንፈልገው የቦርዱ ጸሃፊ ህዝብ በተሰበሰበበት የመዕማናን ስብሰባ ላይ
ለዛሬ ሳይሉ ግጥም አድርገዉ መዋሸታቸዉን ነዉ እንጠቅሳለን “ የቤተ ክርስቲያኑ ከሳሾች
እቤተ ክርስቲያኑ ዉስጥ ያስገበኋቸው እኔ ነኝ እንጅ አቶ ኢዩኤል እይደለም፡ እንዲያዉም
በቦታው አልነበረም” ብሎ በአይናችን ያየነውን ለማስተባበል ሞክሯል።
ይሄ ሃሰተኛ የቦርድ አባል መሆን ይገባዋልን?
እናንተው ፍረዱ።
በድጋሜም ለቦርድ የምርጫ ኮሚቴ ድሮ የተሰናበተው የማህበረ ቅዱሳን የትምህርት ኮሚቴ
አሁንም ስላለ የምርጫ ኮሚቴ ዉስጥ መግባት አለበት እያለ ማወናበዱን ሰምተናል።
ዉድ ማህበርተኛ ሆይ፦
እነዚህን የቦርድ ሊቀ መምበርና ይህን ከሃዲ ጸሃፊ ምርጫዉ ከመካሄዱ በፊት ማባረር ይገባናል
ብለን ስለምናምን ሰሞኑን ስብሰባ ጠርተን እንዲዎርዱ እንጠይቅ።
በትናንትናው ቀን በሽምግልና ስም አይን ያወጣ ድርቅና!!!! ብለን መጻፋችን ይታወሳል!
ቦርዱ ይህን አንብቦ የስብሰባዉን ሰአት ለመለወጥና ህዝቡ ስብሰባዉን ገብቶ እንዳያዳምጥ
ለማድረግ እየተወያዩ መሆኑን ሰምተናል።
የሄ ቦርድ አይጥና ድመት ይመስል እዉነትን ክህዝቡ ለመደበቅ መሯሯጡን መቸ ያቆም ይሆን?
ለያንዳንዱ ሰዉ የተለያየ ወሬ በመፍጠርና በማሰራጨት ህዝቡን እርስ በራሱ እንዳይተማመንና
እንዳይቀራረብ ማድረግን የእለት ከእለት ዋና ተግባሩ እድርጎ ይዞ ቤተ ክርስቲያኑን ወደ ጥፋት
ጎዳና እየመራ ነዉ።
ከዚህ ይልቅ ህዝቡን ሰብስቦ ላደረሰዉ ጥፋት ይቅርታ መጠየቅና ንስሃ መግባት ይሻለዉ ነበር።
የክርስትና እምነታችንም የሚያዘዉ ይህንን ነዉ።
ቦርዱ ግን ክዚህ ይልቅ ካድሬ ይመስል እየዋሸ መሞትን መርጧል!!
ስለዚህ እኛ ምእመናን ይሄንን እየተከታተልን በስብሰባዉ መሳተፍ ይኖርብናል።
የሚወደኝ ህጌን ይጠብቃል ዮሓንስ 10፡15
ህዝበ ክርስቲያን ሆይ መቅደስ ሲደፈር ሰምተህ እንደት ዝም ትላልህ?
ቦርዱ መቅደስ ዉስጥ በመቋሚያና በመስቀል የሚማታ ካህን አቅፎ ይዟል።
ያስተዳድረኛል ብለህ የመረጥከዉ ቦርድ የቀጠረዉ ካህን ከታቦቱ ጋር እንድህ ሲዳፈር ሰምቶ
አንዳልሰማ፤ አይቶ እንዳላየ ፤ ይህን የድፍረት ሥራ ዉጦ ዝም ብሏል።
በዚህ ግለሰብ ላይ እርምጃ ከመዉሰድ ይልቅ ካአባ ፓዉሎስ ሰወች ጋር ቤተ ክርስቲያኑን አሳልፎ
ለመስጠት በሽምግልና ስም ክሚንቀሳቀሰዉ ቡድን ጋር እየተደራደረ ይገኛል።
ምእመናን ሆይ!
መቅደሳችን እንደ ፕሮቴስታንቶች ቤተ ክርስቲያን ባዶ አዳራሽ መሆኑ ነዉ ወይ?
ድብድብ የሚካሄድበት!
እግዚኦ! አግዚኦ! አምላክ ከዚህ ስውረን! ክቁጣዉ አድነን! ወደ ማን እንጮሃለን! ማንስ
ይሰማናል!
ያላባት እንድናመልክ ፈርደዉብን የእግዚአብሄርን ልጆች በተኑን!!
ይሄዉ ዛሬ ደግሞ መቅደስ ዉስጥ የሚደባደብ ካድሬ ለቀቁብን!!
መቸ ነዉ እነዚህን ጉዶች በቃችሁ የምትሉት!!
የሚወደኝ ህጌን ይጠብቃል አሜን!!!
የእዉነት ያለህ
ቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተሰነዘረው ጥቃት የተቀነባበረው በኢሃድግ መንግስት
ነው፡
በደካማ ጎናችን ገብቶ እያጠቃንም ነው፡ ይሕም ሊሆን የቻለው አስተዳደሩ ስራት
ያለምንም ማዕቀብና ቁጥጥር የተዋቀረ በመሆኑ ነው፡ በዚህም ምክንያት ከዉስጥና
ክዉጭ የተሞከረውን አደጋ መቋቋም አቅቶት ሲንገዳገድ ይታያል።
ባለፉት 19 አመታት የተከትልነው አስተዳደራዊ አስራር ተንዶ ለፍርድ ሸንጎ
ዳርጎናል።
ዎደፊት ለመጓዝና ይህን ብልሹ አስተዳደር ለመለዎጥ መፍትሄው፡ ግልጥ! ያለ
የአስዳደር (ትራንስፓረንሲ) ያለው አሰራር መዘርጋት ነው።
የህም ግልጥ አሰራር በሂሳብ መዝገብ አያያዛችን መጀመር አለበት የሚል ሃሳብና
ዕቅዱ ላስተዳደር ቦርዱ ቀረበ። ቦርዱ ግን ይህ የአሰራር ዘዴ ከቀረበለት ቀን ጀምሮ
ይህን እቅድ መቃዎሙን ተቀዳሚ ስራው አደረገ። ይባስ ብሎም ሃሳቡን ያቀረቡ
አባላትን ስም እየጠሩ ስራ አላሰራ አሉን በማለት የስም ማጥፋት ዘመቻን ስራየ
ብለው ተያያዙ። ለምን?
በ2007 ዓ.ም በበጎ አድራጎት ኮሚቲ አማካኝነት ዎጭ የሆነውንና እስከ ዛሪ ድረስ
ይህ ኮሚቲ ደረሰኝ ሊያቀርብበት ያልቻለውን ሰነዶች በ2008 ዓ.ም ላይ
ለመዕመናኑ መበተኑ ይታዎሳል። በዚህ ሰነድ ላይ ስማቸዉ የተዘረዘረው ግል ሰቦች
በሙሉ የዎሰዱትን ገንዘብ አባከኑት ተብሎ ክስ አልቀረበም? ይልቁንም የሰነዱ
መሰራጨት ዋና አላማ የነበረው ማህበረ ቅዱሳን በስሩ የሚተዳደሩ ቤተ
ክርስቲያናትና የራሱን የግል ስራ ለማስፈጸም በአንድ አመት ውስጥ ብቻ ስንት ብር
አንደዎሰደ ለማሳየት የተደረገ ሙከራ ነበር። ዓላማዉ በብዙ ዉጣ ዉረድ ግቡን
ሊመታ ችሏል፡ በዓንጻሩም የህ ሰነድ ዛሬ ይፋ ሆኖ ለመጣዉ ችግር ምክንያት
ሆኗል።
የአስተዳደር ቦርዱ በየሶስት ዓመቱ በሂሳብ አጣሪ (CPA) አስመርምሮ ለመዕመናኑ
የሚያሳዉቀዉን የሂሳብ ዝርዝር (ኦዲት) ማቅረብ ያቃተዉ በዚህ ለሕዝብ
በተበተንዉ ሰነድ ምክንያት ነው።
የኦዲተሩ አቀጣጠር ከመተዳደሪያ ደንቡ ዉጭ ያለምንም ጨረታ በትዉዉቅ መጥቶ
የተቀጠረ ሂሳብ ተቆጣጣሪ ነዉ። ይሄው ተቆጣጣሪ ቀደም ሲል ለቤተ ክርስቲያኑ
ተመሳሳይ አገልግሎት መስጠቱ አይዘነጋም። የሂሳብን መዝገቡ እንደምንፈልገው
በማቀነባበር አቅርብልን (COOK THE BOOK) ማለትም ዋሽልን ተብሎ ሴጠየቅ?
ሳያመነታ የደንበኞቹን ፍላጎት እንጅ የጠራ የሂሳብ የመቆጣጠር ስራ የሰራ
እይደለም።
ይኄዉ ግለስብ ባለፈዉ የአስተዳደር ቦርድ የዎጭ ሰነዶችን ደምረህ በምታገኘዉ
ቅምር ሂሳቡ እንደተዎራረደ አድርገህ አቅርብልን ብለው ቀጥረዉ እንደተጠየቀዉ
ሰርቶ በማቅረብ ኦዲት በ (C P A) ተደረገ ምንም የጎደለ ሂሳብ የለም ተብሎ
በጭብጨባ ሪፖርቱን መዕመናኑ እንዲቀበል ተደርጎ በሽፍንፍን መታለፉን
ሁላችንም እናውቃለን።
የዛሬዉም ቦርድ ይህንኑ አሰራር ለመድገም ቀና ደፋ ሲል ተደርሶበት፡ የለም ይህ
አሰራር ዖዲት ሳይሆን የዎጭ አጠቃላይ ድምር ዉጤት ነው ሲባል ልስራው
መጓተት ምክንያት ሆነ።
ዉድ መዕመናን አንድ ሰነድ ይህን ያህል የሰዉ ዓይን ክገለጸ ዎደ ኋላ የ አስር
ዓመት ሂሳብ ዖዲት ይደረግ ቢባል ዉጤቱ ምን የሚሆን ይመስላችኋል?
እኛ አባላቱ ይህን የመጠየቅ መብት የለንም ይሆን? ዎይስ ጥቅማቸዉ የተነካ
የዘራፊዎች ቡድን እንደሚያሰራጩት ዎሬ ይህን “ የፍሚጠይቁና የሚጽፉ የኛ
ሰዎች አይደሉም “ እየተባለ የኛ ሰዎች አይናቸዉን የከፈቱ አይደሉም
“ያደረግነውን ብናደርጋቸዉ የኛ የሆኑ አይቃዎሙንም” ገንዘባችንና አቅማችንን
አዋጥተን የጀመርነውን ቤት ክርስቲያን መበዝበዝ ቀርቶ መሸጥም እንችላለን እያሉ
ስለሚፎክሩ ከበይ ክፍል ያልሆነ ሁሉ የነሱ ሰዉ አይደለም ለማለት ይሆን?
እንድታዉቁልን የምንፈልገው እኛ አንዳዶቻችን ይሄ ዲርጊት በዛ ይቅር ሳያዋርደን
እናቁመዉና ዎደ መልካም ተግባር እንመለስ የምንል ነን ይሄንንም ያደረግነው
እናንተን ዘመዶቻችንና ጓደኞቻችን ትለቅ የሃፍረት ካባ እንዳትጎናጸፉ ነዉ።
በዚሁ ማስታዎሻ አማካይነት ግለጥ (ትራንስፓረንሲ) አሰራርን አብዛኛቹ የቦርድ
አስተዳደር አባላት የቀድሞዎቹም ሆኑ አሁን ያሉትና ደጋፊዎቻቸዉ ሽንጣቸዉን
ገትረው እየተቃዎሙ መሆናቸዉን እንድታዉቁ ለናንተ ለመዕመናኑ ማስረዳቱ ተገቢ
ነው፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት እንደ ድሮው እንደፈለግን እናደርጋለን እንጅ
ማንም እንዲቆጣጠረን አንፈልግም፡ አንዳንድ እነዙህ የኛን ሰዎች የሚነካ ጥያቄ
ሲነሳ አፍንጫ ሲነካ ዓይን ያለቅሳል እንደተባለው እኛዉ በኛዉ ተጠራርተን
እናፈርሰዋለን እንጅ ከ ዱሮው አሰራር አንዎጣም፡ ዘላለም እንደበዘበዝን አንኖራለን
እንደሚሉ ነዉ።
በሚቀጥለው እስትንገናኝ ደህና ሁኑልን።
ዎስብሃት ለዓምላክ።

Thursday, October 29, 2009

በሽምግልና ስም አይን ያወጣ ድርቅና!!!!
የፊታችን ቅዳሜ ኦክቶበር 31 2009 ዓ.ም ከቅዳሴ በኋላ ራሱን የሽማግሌ ኮሚቴ ነኝ ብሎ
የተሰባሰበዉ ቡድን ከቤተ ክርስቲያኑ የአስተዳደር ቦርድ ጋር ስብሰባ ይቀመጣል።
ስለ ቤተ ክርስቲያኑ ችግር ማወቅ የምትፈልጉ በችግሩ ዙሪያ ማን ከማን ዎገን ሆኖ
እንደሚታገልና የሽማግሌዎቹን አቋም ለማወቅ የምትሹ ሁሉ በዚህ ስብሰባ ላይ መገኘት
ይኖርባችኋል።
ማንም አባል በቦርድ ስብሰባ ላይ ተገኝቶ የመስማት መብቱ በቤተ ክርስቲያኑ መተዳደሪያ ደንብ
3፤ 8፤1 መሰረት የተጠበቀ ነዉ።
በዚህ ስብሰባ ላይ መገኘት አስፈላጊ የሚሆንበት ምክንያት ምንድን ነዉ?
1 ይህ የሽማግሌዎች ስብስብ የሚያቀርበዉን የማስታረቂያ ሃሳብ ቦርዱ ተቀብሎ ማህበርተኛዉን
ሳያማክር በስራ ላይ ለማዋል የግዴታ ዉል እንዲፈርም የጠየቀ ስለሆነ!
2 ከኦርቶዶክስ ሃይማኖት ስነ ስርአስት ዉጭ “ገለልተኝነት” የሚለዉን ሃሳብ አፍልቀዉ ዛሬ
ያለንበት ችግር ዉስጥ ያሰገቡን ስዎች ስለሚገኙበት!
3 “ገለልተኞች” የሚለዉ ሃሳባቸዉን ስራ ላይ ካዋሉ በኋላ “የካህናት እና የምእመናን ማህበር”
የሚል ድርጂት ያቋቋሙ ግለ ስቦች ስለሚሳተፉበት!
4 ይህ የካህናትና የምእመናን ማህበር የሚባለዉ ድርጅታቸዉ ቀደም ብለዉ ገለልተኞች ብለዉ ከ
አባቶች ያገለሉአቸዉን ቤተ ክርስቲያናት ባዲሱ ድርጅታቸዉ ስር አስገብቶ ለማስተዳደር ቅድመ
ዝግጅቱን የሰሩ ሰዎች ስለሆኑ!
5 የዚህ ድርጅት የዘንድሮ ስብሰባ ወጭ በመሸፈንና በማስተናገድ ሃላፊነቱን ቤተ ክርስቲያናችን
እንድትወስድ ያደረጉ ሰወች ስለሚገኙበት!
6 የዳላስ የኢትዮፕያዉያን ኮሚኒቲ ማህበር የቀድሞዉ የአመራር አባላት ስለሚሳተፉበት!
7 እነዚህ ግለሰቦች በኮሚኒቲዉ አመራር ላይ በነበሩበት ወቅት በነሱ ቁጥጥር ስር ያለዉን የሬዲዮ
ጣቢያ የኮሚኒቲዉን ችግሮች ህዝቡ እንዳያዉቅና እንዳይወያይበት ብሎም መፍትሄ እንዳያገኝ
አፍነዉ የያዙ ስለነበሩ !
8 በኮሚኒቲዉ አመራር ላይ በነበሩበት ወቅት የተለያዩ የኮሚኒቲዉን ችግሮች ከመፍታት ይልቅ
ማህበሩን የግል ስራቸዉን ማስፋፊያና የተሻለ ስራ ለመያዣ መሸጋገሪያ ድልድይ አድርገዉ
የተጠቀሙ ስወች ስለሆኑ!
9 ይህ ደብር ችግር ላይ ወድቆ ለሁለት ሲከፈል የተገነጠለዉን ቡድን ለማቋቋም በገንዘባቸዉና
በጉልበታቸዉ የረዱ ግለሰብ ስለሚገኙበት!
10 የፍሎሪዳንና የደንቨርን ቤተ ክርስቲያናት ላባ ጳዉሎስ ያስረከቡ ግለሰብ ስላሉበት!
11 ከከሳሾች ጋር ምኞትና አላማቸዉ አንድ ስለሆነ ለሽምግልና ብቃት ስለሌላቸዉ!
በኛ ግምት እነዚህ ሽማግሌወች ነን ባዮች ራሳቸዉን ተብትቦ የያዘዉን ችግርና ሃፍረት ከላያቸዉ
ለመቅረፍ ሌላ ሽማግሌ ያስፈልጋቸዋል እንላለን።
ስለዚህ ነዉ በስብሰባዉ ላይ መገኘትና የሚሉትን መስማት አለባችሁ የምንለዉ።

Friday, October 23, 2009

ዛሬ በተጨማሪ የኛ ቤተ ክርስቲያን አዎናባጆች እየሰሩ ያለዉን ትረዱ ዘንድ ይህን ጽሁፍና ትንተና እናቀርብላችኋለን.

http://www.quatero.net/pdf/Erim.pdf


%"$A? BÅ (asteraye@gmail.com)

በጥሞና ተመልከቱት

Thursday, October 22, 2009

ለቦርዱ ሊቀ መንብርና ሽምግልና እንቀመጥ እያሉ ሽር ጉድ ለሚሉት ግብረ አበሮቹቢተ
ክርስቲያናችንን ወዲት እንደሚወስዱት እንድትረዱት ከ ኢትዮሚዲያ ያገኘነዉን እናቅርብላችሁ።
http://ethiomedia.com/course/zeregnanet_bebete_kihnet.pdf


በአሜሪካ የፓትርያርኩ ዯጋፊ ካህናት ምሥጢራዊ የስልክ ስብሰባ ማዴረግ ጀምረዋል
ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በገባበት ምስቅልቅል እና ቅደስ ፓትርያርኩ “ተጠሪነቴ ሇቅደስ ሲኖድስ አይዯሇም፣ ሕጉንም አሻሽላሇሁ” ካለ ወዱህ እና ይህንን አንቀበልም ያለ ጳጳሳት ቤቶች የመሰበር አዯጋ ከገጠማቸው ወዱህ የወንበራቸው ነገር ያሰጋቸው ብፁዕ ወቅደስ አቡነ ጳውሎስ አዱስ ስትራቴጂ ነዴፈው በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን ምንጮቻችን አስታወቁ።
በምግባራቸውና ኦርቶድክሳዊ ባልሆነ አስተዲዯራቸው ከምዕመኑና ከአባቶች ፍቅርን የተነፈጉት ቅደስ ፓትርያርኩ ቤተ ክርስቲያንን የሚመዘብሩ “የማፊያ” ቡዴን አባላትንና ዘመድቻቸውን በመያዝ ተቃውሞ እየገጠማቸው ያሇው በዘራቸው ምክንያት መሆኑን ሇማሳየትና የትግራይን ክርስቲያን ሕዝብ ዴጋፍ ሇማግኘት በመጣር ላይ ናቸው። አባ ሰረቀ ብርሃን ወልዯ ሳሙኤል በተባለትና በአሜሪካን ሀገር “በትግርኛ ብቻ ነው ማገልገል የምፈልገው” በሚል ዘዬ ትግርኛ ተናጋሪው በሌላው ሕዝበ ክርስቲያን እንዱጠላ ካዯረጉት ሰዎች አንደ በሆኑት ግሇሰብ ተባባሪነት በመንቀሳቀስ ላይ ባሇው በዚህ አዱስ ታክቲክ በአሜሪካ ያለ የፓትርያርኩ ዯጋፊ መነኮሳት፣ ካህናትና አንዲንዴ በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ያለ ሰዎች ሇብቻቸው በስልክ ኮንፈረንስ እንዱሰበሰቡና አቋም እንዱይዙ እየተዯረገ መሆኑ ታውቋል።
ከዚህ በፊት በጠቅላይ ቤተ ክህነት ይሠሩ በነበሩ ሰው አስተባባሪነትና መሪነት እየተካሄዯ ባሇው በዚህ “የፓትርያርኩ ዯጋፊ ካህናት ልዩ ምሥጢራዊ ስብሰባ” ላይ እየተወሳ እንዲሇው ከሆነ ፓትርያርኩ ተቃውሞ እየገጠማቸው ያሇው በአስተዲዯራቸው ዯካማነት እንዲልሆነ ስምምነት አሇ። ከዚህ ተቃውሞ ጀርባ ያሇው ዯግሞ በዚያው በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ውስጥ ያሇው ማህበረ ቅደሳን የተባሇው ማህበር በመሆኑ በተሇይ በአሜሪካ ዯረጃ የዚህ ማህበር አባላት የሆኑትን ሰዎች ጠራርጎ ማስወጣት እንዯሚገባ ውይይት ተዯርጎበታል።
ማህበረ ቅደሳን “ፓትርያርክ ጳውሎስን በማውረዴ የራሱን ሌላ ፓትርያርክ መሾም ይፈልጋል” የሚለት እነዚሁ ግሇሰቦች ቀዯም ብሎ በአንዲንዴ የአሜሪካ አብያተ ክርስቲያናት በነ አባ ወልዯ ትንሳኤና ተከታዮቻቸው እንዯተዯረገው ዓይነት “የማህበረ ቅደሳን አባላትን የማባረር ዘመቻ” መጀመር እንዯሚገባ ተወያይተዋል። በስብሰባው ላይ ከነበሩት መነኮሳት መካከል ጥቂቶቹ (ሇጊዜው ስማቸውን መጥቀስ አልፈሇግንም) “አሁን ይህንን ሇማዴረግ እንቸገራሇን፣ ባይሆን ሇወዯፊቱ እናስብበታሇን” ያለ ሲሆን በተቃውሞ የቀረቡ ግን አሇመኖራቸው ታውቋል። አንዴ ካህን ብቻ “እስካሁን አብራችሁዋቸው ኖራችሁ አሁን ሇምን ታባርራችሁዋላችሁ። ስንት አገልግሎት የሰጧችሁ እነርሱ አይዯለም ወይ?” ሲለ መጠየቃቸው ተሰምቷል።
ማህበረ ቅደሳን በአሜሪካ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን “ወዯ እናት ቤተ ክርስቲያን ካልገባችሁ” እያሇ ሲወተውት በመኖሩ ከብዙዎች ቂም ማትረፉ ይታወቃል። ሀገር ቤት ያሇው አስተዲዯር “ገነት” የሆነ ይመስል “ሀገር ቤት ያሇው አስተዲዯር ወይም ሞት” ሲል የነበረው ማህበረ ቅደሳን አሁን እርግጫና ደላ ሲገጥመው አቋሙን ይቀይር ይሆናል የሚል አስተያት አሇ። ግማሹን ገሇልተኛ፣ ግማሹን ስዯተኛ እያሇ ከአቡነ ጳውሎስ አስተዲዯር ጋር የሙጥኝ ብሎ የከረመው ማህበረ ቅደሳን አሁን አባላቱ “በሀገር ቤቱ አስተዲዯር ሥር ካለ አብያተ ክርስቲያናት የሚባረሩ ከሆነ ከሁሇት ያጣች ጎመን” የመሆን ክፉ ዕጣ ይገጥመዋል ማሇት ነው።
ማህበረ ቅደሳን ሕዝብ ገሇል ያዯረጋቸውንና “የወያኔ አብያተ ክርስቲያናት” የሚባለ አብያተ ክርስቲያናት የሁለም ሕዝበ ክርስቲያን መሆናቸውን ሇማሳየት አባላቱን በውዳታ ግዳታ ወዯነዚህ ቦታዎች እንዱሄደ ሲመራ መቆየቱ ታውቋል።
ከነዚህም አብያተ ክርስቲያናት መካከል በሎስ አንጀሇስ የቅዴሰት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን፣ በዱሲ የአቡነ ማቲያስ መዴሃኔዓሇም፣ በአትላንታ ጽዮን ማርያም፣ በሜኖሶታ ማርያም፣ በሲያትል የቅደስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እና በዲላስ የተ/ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን እንዯሚገኙበት ተጠቁሟል። ይህንን ሁለ አዴርጎ፣ አባላቱ በገንዘባቸው ቦታዎቹን ካቋቋሙ በኋላ አሁን እንዯ ወንጀሇኛ እንዱወጡ ምክር መጀመሩ በጣም እንዯሚዯንቅ ነገሩን የመረመሩ ምንጮቻችን ተናግረዋል።

Wednesday, October 21, 2009

ቤተ ክርስቲያናችንን እናድን እያልን እንማጠናለን!!!!
የዚህ ደብር መዕመን እግዚአብሄርን የምንፈ-ራ ዓምላካችንን የምንወድና የምንታዘዝ ነን! ትሁት
ልቦናችንን አይቶ በጥገኝነት ከምናመልክበት ቤት አዉጥቶ ዛሬ ይህን ትለቅ ሕንጻ የሰጠን
አምላካች ስሙ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን።
መዕመኑ በመላእክትና በጻድቃን ስም ዙሪያ ተሰብስበዉ ይዘክራሉ ይጽልያሉ የበረከቱ ተሳታፊ
ለመሆን እንሽቀዳደማለን ደስ የሚል የክርስትና ሕይወት ነዉ።
በዚህ መንፈስ ለረጅም ዘመን አብሮ ዓማላክን በማምለክ በተመሰረተ ግንኙነት ብዙወቻችን
በጋብቻ በአበልጅነት ዝምድና ፈጥረናል ከሌሎቻችንም ጋር ጥለቅ ወዳጅነትን መስርተናል።
የዚህ ሁሉ መሰረት እያንዳንዱ ግለሰብ ለዓምላኩና ልኃይማኖቱ ባለዉ ፍቅር ሳቢያ የተፈጠረ
ወዳጅነት ነዉ። የተቀረዉ ግንኙነት በዚህ ጽኑ ዓላማ ዙሪያ የተገነባ ክርስቲያናዊ ማሕበራዊ
ህይወት ነዉ።
ከኅዋሪያት መሃል ይሁዳ ጌታን ክዶ እንደሸጠዉ እናዉቃለን። ከኛም መሃከል ለአገልግሎት
መርጠናቸዉ ለጥቅማቸዉ ሲሉ እኛ ዎደማንፈልገዉ አቅጣጫ ልወስዱን እየሞከሩ ያሉትን
ዎንድሞቻችንና እህቶቻችን የመጨረሻዉን ጥፋት ክመፈጸማቸዉ በፊት ማቆም አለብን።
እምነታችን ክማንም በላይ መሆኑን የምናሳይበት ሰዓት ዛሬ ነዉ።
አባ ፓዉሎስ ወያኔ ናቸዉ። ስለዚህም ነዉ ሓገር ቤት ያለዉ ወገናችን ያልተቀበላቸዉ። ባገኘዉ
አጋጣሚ ሁሉ ተቃዉሞዉን እየገለጸ የሚገኘዉ። እርሳቸዉም ክዚህ የተነሳ እንደ አንድ አምባ
ገነን መሪ በደረሱበት ሁሉ በመከላከያ ሰራዊት አባላት የሚጠበቁት።
ሥራቸዉንም የሚሰሩት በሕዝብ ደህንነት ዓባላት ታጅበዉ ነዉ።
ነጻነቱን የተነጠቀዉ መብቱ የተረገጠዉ የሃገራችን ጀግና ህዝብ ይህ ሁሉ ችግር ሳይገታዉ እኝህን
አባት ጥግ ይዘው እንዲንቀሳቀሱ አድርጓል።
እኛ በነጻነት የምንኖር ያለምንም ስጋት ሃሳባችንን መናገር የምንችል ወገኖች ግን የኛዉ ናቸዉ
ይምንላቸዉ ጉዶች ለዚህ አባት አሳልፈዉ ሊሰጡን በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ በግልጽ እየታየ
በፈጠርነዉ ማህበራዊ ኑሮ እርምርጃ ላንወስድ በይሉኝታ ታስረን እንገኛለን።
ከዕምነታችን ይልቅ ወዳጅነታችንን አስቀድመን ወደ ጥፋት ጎዳና እየተጓዝን ነዉ።
ይህ ዝምታችን የሚያበቃዉ መቸ ነዉ?
የቦርዱ ሊቀ መንበር ሰሞኑን ላባ ፓዉሎስ የጻፈዉን ደብዳቤ እንዳነበባችሁ እርግጠኞች ነን፡
ጥቂቶቻችሁም ለሰላም ሲባል የተጻፈ ጥሩ ደብዳቤ ነዉ ስትሉ ተሰምቷል።
ዉድ መዕመን ሆይ! ፋሽስት ሙሶሎኒ ሃገራችንን ሲወር ትምህርት ቤት እከፍታለሁ ሆስፒታል
አቋቁማለሁ መንገድ እዘረጋለሁ ህዝቡን ነጻ እደርጋለሁ ብሎ ነበር ሲከራከር የነበረዉ፡
እንድም ቀን ባሪያ አድርጌ ቀጥቅጨ ልገዛ ነው ብሎ አልተነፈሰም።
ዲያብሎስም ጌታን ሲፈታተን የዓለምን መንግስት ሁሉ ከነ ክብራቸዉ እሳየዉና “ ተንበርክከህ
ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ” አለዉ ማቴዎስ 4፡8-9 ይሁዳ አሳልፎ ሲሰጠዉ ሰይፍ
የያዙት ሰራዊት ክኋላ ተደበቀዉ እርሱ ግን “መምሕር ሆይ! ሰላም ላንተ ይሁን” በማለት ነበር
የቀረበዉ ማቴዎስ 26፡49
የኛም ሊቀ መንበር የጻፈዉ ደብዳቤ ዉስጡ ሲታይ ጉዱ ብዙ ነዉ “እኛ በዓለሙ ሁሉ
ተሰራጭተን የምንገኝ ተባባሪዎች” እያለ የሳቸዉ ተወካይ መሆኑን በደብዳቤዉ መግቢያ ላይ
ገልጾታል።
501፡ c ፈቃድ ያለው ድርጂት አቋቁመዉ ገንዘብ እየሰበሰቡ ነዉ።
ቤተ ክርስቲያናችን ዛሬ ከፍተኛ አደጋ ላይ ነች፡ ሁሉም ሊቀራመትዋት ክበዋታል! የዓምላክን
ጥሪ ተቀብሎ የሚመራ ሰዉ ትፈልጋለች።
ነገሩ ካለቀ በኋላ መጸጸት ፋይዳ የለዉም!
በህብረት ተነስተን ቤተ ክርስቲያናችንን ከነዚህ ቡድኖች መንጋጋ እናዉጣ!!!
እግዚአብሄር ይርዳን።

Monday, October 19, 2009

ዘግይቶ የደረሰን አብይ ዜና
የቦርዱ ሊቀ መንበር በአባ ፓዉሎስ ለሚመራዉ ሲኖዶስና ለወያኔው ፓትሪያርክ ላባ ፓዉሎስ
የጻፈዉን ደብዳቤ እንድታነቡት እናቀርብላችኋለን።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዓለም አቀፋዊ የምእመናን ማሕበር
WORLD ASSOCIATION OF PARISHIONERS OF THE ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO CHURCH
10107 Branwood Circle, Dallas, TX 75243, U.S.A. WWW.eotcipc.org
Tel: (469)855 8488 (214)697 8928; (813)312 1502; e-mailmiimenan@yahoo.com
መስከረም 18 ቀን 2002 ዓ/ም
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ አሐዱ አምላክ፤ አሜን።
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ፤
ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ
ለብፁዓን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት
አዲስ አበባ።
ጉዳዩ፤ በቤተክርስቲያናችን፤ ሰላም፤ አንድነትና ዘላቂ እድገት እንዲገኝ ስለ ማድረግ፤
በመጀመሪያ፤ ለቅዱስ ሲኖዶሱ ያለንን እጅግ ከፍ ያለ አክብሮት እየገለጽን፤ ለብፁዓን የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት
የእግዚአብሔር ሰላምታችንን በትሕትና እናቀርባለን።
እኛ በዓለሙ ሁሉ ተሰራጭተን የምንገኝ ተባባሪዎች የቤተክርስቲያናችን ምእመናን በቅርቡ በቅዱስ ሲኖዶሱ
አባላት መሀል በተከሰተው ውዝግብና ባጋጠሙት ድርጊቶች እጅግ ተሳቅቀናል፤ አዝነናልም። ሆኖም፤ በጥቅምት
ወር 2002 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሰባ ስለሚከናወን ጉባኤው ለቤተክርስቲያናችን የተሙዋላ ሰላምና አንድነት
እንዲያስገኝና የዘለቄታ እድገት የሚያመቻች ስልት እንዲተልም የበኩላችንን ግንዛቤና ማሳሰቢያ ከዚህ በታች
በአክብሮት እናቀርባለን። የቅዱስ ሲኖዶሱ ጉባኤም በቤተክርስቲያናችን ላይ ተጋርጠው የሚገኙትን እጅግ ከባድ
ችግሮች ለማስወገድ ተገቢ የሆኑ መፍትሔዎችን እንደሚያስገኝ ያለንን ፅኑ ተስፋ በቅድሚያ እንገልጻለን። ስለዚህ፤
ቅዱስ ሲኖዶሱ፤ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት፤ ከዚህ በታች የምናቀርባቸውን ሀሳቦች በጥሞና ተመልክቶ ቅድስት
ቤተክርስቲያናችንን ለዘለቄታ በሚያጠናክርና በሚያስፋፋ ስልት ተገቢውን ውሳኔ እንዲያደርግ እንማጸናለን።
1. ስለ ቅዱስ ሲኖዶሱ ሥልጣን፤
እንደሚታወቀው፤ በ1991 ዓ/ም በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የተደነገገው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 5 የቅዱስ ሲኖዶስን ሥልጣን እንደሚከተለው በግልጽ አስቀምጦታል፤
“1. በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው ቅ/ሲኖዶስ የመንበረ ሐዋርያት ወራሽ ስለሆነ በቤተ ክርስቲያኒቱ
የመጨረሻው ከፍተኛው ሥልጣን ባለቤት ነው።
2. ከማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥልጣን መዋቅር ሁሉ የበላይ አካል ቅዱስ ሲኖዶስ ስለሆነ
ሕጎችን፤ ልዩ ልዩ ደንቦችንና መመሪያዎችን የማውጣትና የዳኝነት ሥልጣን አለው።”
2
ከላይ በሁለቱ ንኡስ አንቀጾች እንደተገለጸው፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ሥልጣን በማያሻማ ሁኔታ በግልጽ የተደነገገ ስለሆነ
በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ወቅት በወገናዊነትም ሆን በዓለማዊ ጥቅም ፍለጋ ምክንያት በማንም የውጪም ሆነ የውስጥ
አካል ተጽእኖ እንዳይሸረሸርና እንዳይዛባ በእግዚአብሔር ስም ከፍ ባለ ትሕትና እንጠይቃለን።
2. ስለ ሰላምና አንድነት፤
በአባቶቻችን መካከል የተፈጠረው አለመግባባትና መከፋፈል አደባባይ ወጥቶ መዘባበቻ በመሆኑ በአባቶቻችን ላይ
በቀላሉ የማይፋቅ ታሪካዊ ትዝብት ያተረፈላቸው መሆኑ ግልጽ ነው። ይህ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያናችንን እጅግ
በሚያሰጋና በሚያሳስብ ሁኔታ አደጋ ላይ ጥልዋታል። ይህ በአባቶች መካከል የተከሰተው መከፋፈል፤ መኖቆርና
አንድነት ማጣት፤ በአመራር ደረጃ የሚታየው ግዴለሽነትና ብቃት ማጣት፤ ምእመናንን ግራ ያጋባው ስደተኛ
ሲኖዶስ በመባል ያስከተለው መወጋገዝና የቤተ ክርስቲያናችን መከፋፈል አዝማሚያ መታየት እነዚህና ሌሎችም
ሁኔታዎች ለቤተ ክርስቲያናችን ጠላቶች መጠናከርና መስፋፋት አመች ሁኔታ ፈጥሮላቸዋል። ስለዚህ የቅዱስ
ሲኖዶስ አባላት እነዚህን ለቤተ ክርስቲያናችን በጣም አደገኛ የሆኑትን ክስተቶች በማጤንና በማሰላሰል፤
በክርስቲያናዊ አስተሳሰብና ይቅር ባይነት በመካከላችሁ የተፈጠረውን አለመግባባትና መከፋፈል አስወግዳችሁ
በፍጹም ፍቅርና ሕብረት በመወያየት ቤተ ክርስቲያናችንን ከተጋረጡባት አደጋዎች እንድታድኑዋት በጌታችን፤
በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስና በእናቱ በቅድስት ድንግል ማርያም ስም ከፍ ባለ ትሕትና እንማጸናችሁዋለን።
3. ስለ አስተዳደር ጉድለት፤
በባለሙያ የተጠና መዋቅር፤ ግልጽና የማያሻማ የአስተዳደር ደንብ፤ ዓላማው ግልጽ የሆነ የአጭር፤ የመካከለኛና
የረዥም ጊዜ እቅድ የሌለው ማንኛውም ተቁዋም፤ ብክነት፤ ሙስና፤ አድልዎ፤ የሥራ ቅልጥፍና ማጣትና
የመሳሰሉት የአስተዳደር ብልሹነት የሚታይበት መሆኑ አያጠራጥርም። ቤተ ክርስቲያናችንንም እዚህ ምስቅልቅልና
አደጋ ላይ ጥሎ ለውድቀት ከዳረጉዋት ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ይህ ሁኔታ መሆኑ እውነት ነው። በተለይ እንደ
ቤተ ክርስቲያናችን ያለ ግዙፍ ተቁዋም በየመስኩ በሚገኙ ባለሙያዎች የተጠና መዋቅር፤ በመዋቅሩ ላይ
የተመሠረተ ግልጽና የማያሻማ የአስተዳደር ደንብ፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ዓላማዎች ላይ የተመሠረተ የአጭር፤
የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ጥርት ያሉ እቅዶችና በእቅዶቹ ላይ የተመሠረቱ ምእመናንንና ምእመናትን በሰፊው
የሚያሳትፉ የሥራ ፕሮግራሞች በባለሙያዎች ተጠንተው እንዲዘጋጁ ማድረግ ቤተ ክርስቲያናችንን ከውድቀት
ለማዳን አማራጭ የማይገኝለት ጉዳይ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ስለዚህ ቤተ ክርስቲያናችን ትክክለኛውን አቅጣጫ
ይዛ በመጉዋዝ እየተስፋፋችና እየተጠናከረች በመሔድ በሕገ ቤተክርስቲያናችን በአጠቃላይ የተደነገጉትን
መንፈሳዊውንና ዓለማዊውን ዓላማዎቹዋን ግብ ለማድረስና ከገጠሙዋት ችግሮች መላቀቅ እንድትችል እላይ
በጠቀስናቸው አማራጭ በማይገኝላቸው ጉዳዮች ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ሥርነቀል
ውሳኔ እንዲያስተላልፍ
በማክበር እናሳስባለን።
4. ስብከተ ወንጌልን ስለ ማጠናከርና ስለ ማስፋፋት፤
በሕገ ቤተ ክርስቲያናችን እንደሚከተለው ተደንግጉዋል፤
አንቀጽ 7 ቁጥር 7 “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት በአገር ውስጥና በውጭ አገር እንዲስፋፋ
ያደርጋል።”
ነገር ግን፤ ከላይ በተጠቀሰው ሕገ ቤተ ክርስቲያን መመሪያ መሠረት የተወሰደው እርምጃ እጅግ አነስተኛ ነው።
እንደሚታወቀው፤ በአገራችን በኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያናችን ምእመናንና ምእመናት ስለ እምነታቸው በቂ
ትምሕርት ስለማያገኙ በብዛት ወደ ሌሎች እምነቶች እየፈለሱ በመሔዳቸው የቤተ ክርስቲያናችን እምነት
ተከታዮች ቁጥር እየቀነሰ ከመሔዱም በላይ በተለይ በገጠሩ የሚኖሩት ምእመናን ስለ ወንጌልም ሆነ ስለ
እምነታችን ያላቸው ግንዛቤ እጅግ አነስተኛ መሆኑ የታወቀ ነው። በአንጻሩ፤ የሌሎች እምነት ተከታዮች ቁጥር
እየጨመረ መሔዱ ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ የሌላው እምነት ተከታይ እምነቱን እንዲቀበል በስልት ተምሮ
የተቀበለውን እምነት በጣፈጡ ቃላት ለእኛው እምነቱን ያስተማረው ለሌለውና ለማያውቀው ምእመን እየሰበከ
ባል ሚስቱን፤ ሚስት ባልዋን ሲያስኮበልሉ ይታያሉ። ከኢትዮጵያ ውጪ በመላው ዓለም ተሰራጭተው በሚገኙ
ኢትዮጵያውያን ጥረትና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ፕሮግራም በውጭ ሐገሮች በብዛት
3
በተቁዋቁዋሙት አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙ ካሕናት የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን እምነት በይፋ ለሌሎች ዜጎች
ስለማያስተምሩ ቤተ ክርስቲያናችን ብዙ የሌሎች ዜጎች ምእመናንንና ምእመናትን አባል ማድረግ ስትችል
የሚያስተምራቸው ስለሌለ እምነታችንን የተቀበሉ የውጭ ሐገር ዜጎች በጣም ጥቂት ናቸው። ስለሆነም፤ ከላይ
የተጠቀሰውን ችግር ቀስ በቀስ ማስወገድና ስብከተ ወንጌልን በስፋት እያሰራጩ ኢትዮጵያውያንና የውጭ ዜጎች
ምእመናንና ምእመናትን ቁጥር ማብዛት የሚቻልበት ዘዴዎች በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ዘንድ የሚታወቁ ቢሆንም
ለመጠቆም ያህል የወንጌል መልእክተኞቻችን በሐገራችን ቁዋንቁዋዎችና በሌሎች ዜጎች ልዩ ልዩ ቁዋንቁዋዎች
በብዛት ማሠልጠንና እንደ ሌሎቹ እምነት አስተማሪዎች በየገጠሩ በቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን በየመንደሩ
እየተዘዋወሩ እንዲያስተምሩ ማድረግ፤ በመጻሕፍት ብቻ ሳይሆን በቀላሉ የሚነበቡ በራሪ ወረቀቶችን በልዩ ልዩ
ቁዋንቁዋዎች በብዛት እያዘጋጁ ማሰራጨት፤ በመገናኛ ብዙኅን ማለት በሬዲዮ፤ በቴሌቪዥን፤ በድረገጽና
በመሳሰሉት ትምሕርተ ወንጌልን፤ እምነታችንና ቀኖናችንን ማሰራጨት ስለሚቻል ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ አስፈላጊና
አሳሳቢ ጉዳይ ላይ ውይይት አድርጎ አመርቂ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ እናምናለን።
5. ደብሮችንና ገዳሞችን ስለ መርዳት፤
ከደርግ ዘመን ጀምሮ፤ ቤተክርስቲያናችን አብዛኛውን ንብረቷን ስለ ተዘረፈች ብዙ ደብሮችና ገዳሞች ችግር ላይ
ይገኛሉ። በብክነት ምክንያት፤ ከምእመናን የሚገኘውም በትክክሉ እንዲደርሳቸው አልተደረገም። በተከሠተው
መናቆር ምክንያትም፤ ውጪ ሐገሮች ያሉት ምእመናንም በሚችሉት መርዳት አልቻሉም። በተጨማሪም፤ እጅግ
አሳሳቢ ሆኖ የቆየው፤ ታሪካዊው የኢየሩሳሌሙ “ዴር ሡልጣን” (1) ገዳማችን የሚያስፈልገው ጥገና
ስላልተከናወነለት የመፍረስ አደጋ ላይ ነው። ስለዚህ፤ ቤተክርሲቲያናችን ካላት ገቢ፤ ደብሮችና ገዳሞች ተገቢውን
ድርሻቸውን እንዲያገኙ፤ ለዘለቄታውም ራሳቸውን እንዲችሉ ተገቢ በሆነ ሥልት እንዲጠቀሙና፤ ከውጪም
የሚገኘው ድጋፍ እንዲዳብር፤ የእሥራኤል መንግሥትም የኢየሩሳሌም ገዳማችን እንዲጠገን ፈቃዱ እንዲሆን፤
ቅዱስ ሲኖዶሱ ተገቢ የሆነ ጠንካራ ሥልት አዘጋጅቶ ሥራ ላይ እንዲያውል በማክበር እናሳስባለን።
6. ስለ ትምህርት ማስፋፋትና ማጠናከር፤
ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ የወጣው ሕገ ቤተክርስቲያን፤ አንቀጽ 7 ስለ “የቅዱስ ሲኖዶስ ሥልጣንና ተግባር”½
እንደሚከተለው ደንግጓል፤
ቁጥር 8፤ “የክርስቶስን ወንጌለ መንግሥትና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ያስተምራል ያስፋፋል።”
ሆኖም፤ ቤተክርስቲያናችንን ካጋጠሟት እጅግ ከባድ ችግሮች አንዱ የአብነት ትምሕርት ቤቶች መዳከም ነው።
ቀድሞም ሆነ በአሁኑ ዘመን፤ የአብያተ ክርስቲያናችን ሕልውና መሠረት የአብነት ትምህርት ቤቶች መሆናቸው
ይታወቃል። ገዳማትንና አድባራትን የሚያገለግሉት ካህናት ምንጭ የአብነት ትምህርት ቤቶች ናቸው። የብፁአን
ወቅዱሳን ፓትሪያርኮች፤ የብፁአን ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስ ቆጶሳት ምንጭ የአብነት ትምሕርት ቤቶች ናቸው።ስለዚህ
የእነዚህ አብነት ትምህርት ቤቶች መዳከም ማለት የቤተ ክርስቲያን መዳከም ማለት መሆኑ እውነት ነው።
ከአስተዳደር ችግሩ በተጨማሪ የገጠሬው ምእመን በከፋ ድሕነት ስለሚሰቃይ ለቆሎ ተማሪውና ለአስተማሪው
የተለመደ ቸርነቱን ሊያበረክትለት አልቻለም። ለጋሽ የነበረው የኢትዮጵያ ገበሬ ተመጽዋች በመሆኑ የቆሎ
ተማሪዎችና መምህራኖቻቸው የእለት ጉርሳቸውንና የዓመት ልብሳቸውን ከገበሬው በምጽዋት ማግኘት ስላልቻሉ
ወደየከተማው በመሰደድ ላይ ናቸው። በዚህ ምክንያት፤ የቤተክርስቲያናችን ምንጭ የሆኑት የአብነት ትምሕርት
ቤቶች አስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። ውጪ ሀገሮች ላሉት ምእመናንም ተገቢ የሆኑ የሥልጠና ማእከሎች
(1) ማሕበራችን ስለ ታሪካዊው የኢየሩሳሌም ገዳማችን ለእስራኤል መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር የሚያቀርበውን
አቤቱታ በዓለምአቀፍ
ደረጃ በማስፈረም ላይ መሆኑን የሚያሳየውንና ያሰራጨውንም መግለጪያ በድረገጹ
በwww.eotcipc.org½ይመልከቱ።
4
ስላልተቋቋሙላቸው በቤተክርስቲያናችን ትምሕርት የጠለቀ እውቀት ሊያገኙ አልቻሉም። ስለዚህ፤ የአብነት
ት/ቤቶች እንዲጠናከሩና ውጪ ሐገሮችም የቤተክርስቲያናችን ት/ቤቶች እንዲቋቋሙ፤ ቅዱስ ሲኖዶሱ ለጉዳዩ ልዩ
ትኩረት በመስጠት በባለሙያዎች ጥናት ላይ የተመሠረት ዘላቂ መፍትሔ እንዲያስገኝለት በትሕትና እናሳስባለን።
7. አክራሪዎች ስላደረሱት ጥቃት፤
ቤተክርስቲያናችንን ካጋጠሟት እጅግ መራርና አስቆጪ ጥቃቶች አንደኛው አክራሪ እስላሞች ካሕናትንና
ምእመናንን አሰቃቂ በሆነ መንገድ መጨፍጨፋቸው፤ ደብሮችንና ገዳሞችን ማቃጠላቸውና ከጠላት ሐገሮች
በሚያገኙት ገንዘብ ቤተክርስቲያናችንን በብዙ መንገድ መፈታተናቸውን መቀጠላቸው ነው። በተለይ በ1997 እና
1998 ዓ/ም ከምሥራቅ ሐረርጌ ክፍለ ሐገር ጋራሙለታ ጀምሮ በምዕራብ እስከ ኢልባቦርና ከፋ ክፍላተ ሐገራት
ባሉት አገሮች በባሌና አርሲ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት የፈረሱና የተቃጠሉ፤ ብዙ ካህናት የተሰየፉ፤ እንደ እንስሳ
የተቀሉ፤ ተገድደው የሰለሙ መሆናቸው ያደባባይ ምሥጢር ነው። ስለዚህ ሁሉ ግፍ፤ በቤተክርስቲያናችን አመራር
ምን እንደ ተከናወነና ምን ክትትል በመደረግም ላይ እንዳለ የሚታወቅ ነገር የለም። የተከናወነው አሰቃቂ ግፍ
ተጀመረ እንጂ ያበቃለት አለመሆኑን፤ እንዲያውም የባሰ ጥቃት ሊከሰት እንደሚችል አውቆ፤ ነቅቶ እንዲጠብቅ
ለቤተ ክርስቲያናችን ምእመናን በሰፊው ማስገንዘብ ያስፈልጋል። ስለዚህ፤ ቅዱስ ሲኖዶሱ ይህን ከባድ ጉዳይ
በዝርዝር በማጥናት ተገቢው ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ እንዲሁም ቤተክርስቲያናችን ለራሷ ብቁ፤ ለዘመኑ አመች
የሆነ ሕጋዊ መከላከያ እንዲኖራት ለማድረግ የሚያስችል ሥልት አዘጋጅቶ ሥራ ላይ ማዋል የሚያስፈልግ መሆኑን
በአክብሮት እናሳስባለን።
8. ስለ ድሕነት፤
ከላይ በተጠቀሰው ሕገ ቤተክርስቲያን፤ አንቀጽ 6 ቁጥር 6 አንደኛው የቅዱስ ሲኖዶስ ዓላማ እንደሚከተለው
ተገልጿል፤
“የሰው ዘር ሁሉ ከርሃብ፤ ከእርዛት፤ ከበሽታና ከድንቁርና ተላቆ በሰላምና በአንድነት በመተሳሰብና
በመረዳዳት በመንፈሳዊ ሕይወት እንዲኖር ማስተማርና መጸለይ፤”
የሐገራችን ሕዝብ እጅግ በከፋ የድሕነት አረንቋ ፍዳውን እያየ መሆኑ የታወቀ ነው። ቤተክርስቲያናችንንም
ለእምነቱ መጠጊያ፤ ለረሐቡም ማስታገሺያ እንድትሆንለት ይፈልጋል። በዚህ ረገድ፤ ቤተክርስቲያናችን ለደኸየውና
ለታረዘው ወገናችን በበለጠ ሁኔታ ደራሽ እንድትሆን ተገቢ ሥልት እንዲቀየስና ሥራ ላይ እንዲውል፤ ቅዱስ
ሲኖዶሱ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ በትሕትና እናሳስባለን።
9. መደምደሚያ፤
ከላይ የዘረዘርናቸው ጉዳዮች የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኩዋይ ትኩረት የሚገባቸው መሆኑ ቢታወቅም፤ ምእመናን
መፍትሔ የሚሹባቸው ሌሎች ችግሮችም አሉ። ከነዚህ ውስጥ ጥቂቱን ለመጥቀስ፤ (ሀ)ቃለአዋዲውን
ስለ
ማሻሻል፤ (ለ) መጠናት ስለሚገባቸው ድርሳናት፤ ገድላት፤ ውዳሴያትና ታምራት፤ (ሐ) የምእመናትን ተሳትፎ ስለ
ማጠናከር፤ (መ) ቅዱስ ቁርባኑን ባለመቀበል፤ አብዛኛዎቹ ምእመናንና ምእመናት በቅዳሴያችን በግልጽ እንደ
ተቀመጠው፤ የእግዚአብሔርን ሕግ አፍራሾች ሆነን ስለ መገኘታችን፤ ወዘተ ይገኙበታል።
ቅዱስ ሲኖዶሱ መልካም ፈቃዱ ሆኖ፤ ከላይ የዘረዘርናቸውን ጉዳዮች በጥሞና ተመልክቶ አስፈላጊውን መመሪያ
እንዲሰጥና ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ሰላምና አንድነት የሰፈነባት፤ በተሟላ ሥልት፤ አቅድና፤ ፕሮግራም
የምትንቀሳቀስ፤ በቅልጥፍና፤ በግልጽነትና በአስተማማኝ ቁጥጥር የምትሠራ፤ ስብከቷና ትምሕርቷ ለዓለም ሕዝብ
ሁሉ የሚዳረስ፤ የማትደፈር፤ ራሷን የቻለች፤ ምእመኖቿም በእምነታቸው የጸኑ የብዙ ሐገሮች ዜጎች እንዲሆኑ
እንዲያደርግ የሁልጊዜም ጸሎታችን ነው።
ቅዱስ ሲኖዶሱ፤ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት፤ ባሁኑ ጊዜ በቤተክርስቲያናችን ላይ የተጋረጡትን ከባድ ችግሮች
በሚገባ እንዲወጣ ለቸሩ የኢትዮጵያ አምላክ ተንበርክከን እንጸልያለን። አሜን።
እጅግ ከፍ ካለ የአክብሮት ሰላምታ ጋር፤
ኢዮኤል ነጋ
የማሕበሩ ዋና ጸሐፊ።
ቅሌት
ሰሞኑን “ትኩረት” በሚል ርዕስ ዉስጥ የተጻፈ በራሪ ዎረቀት አንብበናል ። ቀደም ሲል “ “ደዎል” በሚል ርዕስ
ይቀርብ ከነበረዉ ጽሁፍ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ አግኝተነዋል።
ስለ ቤተ ክርስቲያን ችግር “ትኩረት” ልትጠቁመን ሞክራ አልተሳካላትም።
ይልቁንም በዎያኔ አፈ ቀላጤዎችና ቦርድ ዉስጥ ባሉ ተወካዮቻቸዉ በኩል የተዋቀረዉ አዲሱ “ የቀድሞ የዕኛ
ሰዎች” ድርጅት ልሳን መሆኑን ተረድተናል።
ቦርድና ድርጂቱ በ”ትኩረት” አማካኝነት የቤተ ክርስቲያናችን ችግር በግለሰብና በጥቂት ሰዎች የተፈጠረ ነዉ ብለዉ
ልያሳምኑን ይሞክራሉ። በአባ ፓዉሎስ ቀሳዉስትና ዲያቆናት አማካይነት ሰፊ ቅስቀሳ እያደረጉ ነዉ፡ ለማዉገዝም
እየቃጣቸዉ ነዉ።
ከዚህም አልፎ ይህ የዎያኔና የአባ ፓዉሎስ ቡድን በከተማዉ ዉስጥ የታዎቁ የኮሚኒቲ መሪዎችን በማሳመንና
በሚቀጥለው ምርጫ የቦርድ አባል ሆነው እንዲመረጡ ቃል በመግባት የዚህ እኩይ ሃሳብ ተባባሪ አድርገዋቸዋል።
በተደረሰዉ ስምምነት መሰረት እነዚህ ግለሰቦች በከተማችን ዉስጥ በሚገኙት ሕቡዕ የማህበራዊና የፖለቲካ ፎረሞች
ላይ ዛሬ “ትኩረት” የሚያሰራጨዉን ሃሳብ አቅርበዉ ተሰብሳቢዉን ለማሳመን እየታገሉ መሰንበታቸዉ የአደባባይ
ሚስጢር ነዉ።
ከዚህም አልፈዉ ጁን ላይ በተደረገዉ አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ጉባዒ ላይ ይሄንኑ ሃስብ እነዚሁ የኮሚኒቲዉ ግለ
ሰቦች አቅርበዉና ችግሩን በሽምግልና መልክ የሚያይ ኮሚቴ ለማስመረጥ መሞከራቸዉ አይዘነጋም።
ሕዝቡ መገንዘብ ያለበት ዎያኔ በተለያየ መልክና ይዘት ሊያጠፋን የሸረበዉን ተንኮል ነዉ። ስለ መሠረታዊ ችግራችን
ከዚህ በፊት ቤተ ክርስቲያናችንን ከቀበሌ የፍርድ ሸንጎ ወደ ተቀደሰ ደብር ለመለወጥ የተደረገ ጉዞ በሚል ርዕስ ስር
የተጻፈዉን እንድታነቡት እንጋብዛለን
የኽዉም በ “ብሎጉ” መጨረሻ ገጽ ላይ “Older posts” የሚለውን ስትጫኑ ክምታገኟቸዉ ጽሁፎች አንዱ ነው።
ቸር ወሬ ያሰማን!!!!!.

Wednesday, October 14, 2009

የቤተ ክርስቲያናችን ችግሮች በአስተዳደር ቦርዱ እይታ፡
የተመረጣችሁት፦
ተበላሽቶ የነበረዉን የቀድሞ አስተዳደር ለማስተካከል ነበር፡ በማስተካከል ፋንታ እያበላሻችሁ ነዉ
አይደል?
ዛሪ ያን አደራ ረስታችሁ ከቀድሞ የእኛ ሰዎች ከምትሏቸዉ ጋር እየተባበራችሁ በዱሮው አመራር
ያለ ምንም ለዉጥ እየሰራችሁ ነው አይደል?
ማህበረ ቅዱሳን መለካት የማይችል ፍዳ ላይ ጥሎን አሁንም የቢተ ክርስቲያን አባል ልታደርጉ
እየታገላችሁ ነው አይደል?
ይህንንም ባሳተማችሁት የቀን መቁጠሪ አና በይፋ ባፋአችሁም ገልጣችኋል አይደል?
የማህበረ ቅዱሳን አባል እና የ አባ ፓዉሎስ ተጠሪ ቀሳዉስት ቀጥራችሁ ህዝቡን እያስበጠበጣችሁ
ነው አይደል?
ይኅዉ ተጠሪ ካህን በጾም ዎቅት ብር ተቀብሎ ሲያጋባ ዝም አላችሁ አይደል?
ሕዝቡን ሲያዉኩ በመቅደስ ቆመዉ ሲሳደቡ እና ስለማህበረ ቅዱሳን ድርጅት በትምህርት መልክ
ሲያስተላልፉ ሰምታችሁ እንዳልሰማ ሆናችሁ አይደል?
የማህበረ ቅዱሳን አባል ለትምህርት ጋብዛችሁ አስመጣችሁ አይደል?
እነዚሁ ቀሳውስት ሕዝቡ ገንዘብ እንዳያዋጣ ሲቀሰቅሱ ዝም አላችሁ አይደል?
“ሕዝብ ለቢተ ክርስቲያን ገንዘብ እንዲሰጥ ለማስተማር መንፈስ ቅዱስ አላሳሰበንም” ብለዉ
በጉባኤ ላይ ስናገሩ ሰምታችሁ ምን አደረጋችሁ?
የማህበረ ቅዱሳን ቄሶቻችሁ እንግዳ ቄስ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ዎረቀት ሲበትኑ ምን
አደረጋችሁ? ዚም ብላችሁ አያችሁ አይደል?
የአባ ፓዉሎስና የማህበረ ቅዱሳን ቄሶች አድማ መትተዉ መቅደስ ዉስጥ ተደብቀዉ ሲዉሉ ዝም
አላችሁ አይደል?
ቄሶቹም እናንተም ቂም ይዞ ያለንስሃ መቀደስም መጸለይም ይቻላል ብላችሁ ታምናላችሁ
አይደል?
ማህበረ ቅዱሳን አገልግሎት የሚሰጡትን የነሱ ያልሆኑ አባላት ሰድበዉ ሲያባርሩ አይታችሁ ዝም
አላችሁ አይደል?
የሂሳብ አያያዝና የአስተዳደር ሥራት ይለዎጥ ቢባል አሻፈረን አላችሁ አይደል?
ግለጽ አሰራርን አትዎዱም አትቀበሉም አይደል?
ገቢዉን እንደፈለጋችሁ ማዉጣት እንጅ ባጀት አዉጥታችሁ በባጀት መስራትን አትዎዱም
አይደል?
ቤት ክርስቲያኑን እየጎዱ ያሉትን ቀሳዉስት ገንዘብ ባይኖርም ተበድራችሁ ደመዎዝ መክፈል
ታስባላችሁ አይደል?
ከሳሾች ጋር አብራችሁ መዶለታችሁን አትክዱም አይደል?
እነሱ ከዉጭ እናንተ ከዉስጥ ሆናችሁ ቤተ ክርስቲያኑን ለማዉደም እያሰባችሁ አይደል?
ካስዎጡኝ ዎይም እንደገና ካልመረጡኝ ይህን ቤተ ክርስቲያን አዎድመዋለሁ የሚል የቦርድ አባል
እንዳለ ታዉቃላችሁ አይደል?
መጠነ ሰፊ የሆነዉን የቤተ ክርስቲያኑን ችግር ከ መዕመኑ ጋር ስብሰባ ጠርታችሁ መላ መፈለጉን
አትፈልጉም አይደል?
ተቀዳሚ ዓላማችሁ እንደገና ካልተመረጣችሁ ይሄ ቤተ ክርስቲያን የሚደክምበትን እና
የሚዎድቅበትን መንገድ እያዘጋጃችሁ አይደል?
እንደገና በተደጋጋሚ ተመርጣችሁ የዱሮ ግብራችሁን (ብዝበዛችሁን) ለመቀጠል በምታደርጉት
ዘመቻ ይህን ቤተ ክርስቲያን ያለኛ በቀር ማስተዳደር የፍሚችል የለም በሚል ሽፍን ቅስቀሳ በ
አፈ ቀላጤያችሁ እያስዎራችሁ ነዉ አይደል?
ምርጫዉ ካልተሳካላችሁ የእኛ ዎገኖች የምትሏቸዉን ሰዎች አዘጋጅታችሁ ለማስመረጥ ቅስቀሳ
ጀምራችኋል አይደል?
ደብራችን ላይ ይህን ሁሉ ደባ እየፈጸማችሁ ለምን ተብላችሁ ስትጠየቁ ስማችሁ ስለተጠቀሰ
እንደ እብድ አደረጋችሁ ( እዉነቱን ሲነግሩት እንደ ኮለኮሉት ያህል ይስቃል) እንደሚባለዉ
እዉነቱ ሲዎጣባችሁ አሳበዳችሁ አይደል?
የዚህ ሁሉ ጥያቄ መልሱ አዎን ነዉ፡
ማሳሰቢያ፦
በዚሕ አትም አባልና ተቆርቋሪ የሆናችሁ የሚካኤል ዎዳጆች በሙሉ ከላይ የተጠቀሱትን
መንደርደሪያ አድርጋችሁ ቤተ ክርስቲያናችን አደጋ ላይ መሆኑን ተረድታችሁ የሚጠነሰሰዉን
የሃሰት ተንኮል እንድትረዱ ነዉ፡
ለምሳሌ ያህል የቦርዱ ሊቀ መንበር የሚያሰራጨዉ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ የማይፈለጉ ቄሶች
የማይዎጡት ከሳሾቻችን ጋር እንዳይተባበሩ ነው የሚል አሳሳች ሃሳብ የሚያሰራጭ መሆኑን
ነግሯችኋል፡
የህግ ሰርቲፊኬት እንዳለዉ ሊያሳየን ይሆን?
ዎይስ ጠበቃ አነጋግሮ ይሆን?፡ ከከሳሾችህ ጋር ይተበበራል ያለዉ?
ይህ አዎናባጅ ግለሰብ ቤተ ክርስቲያኑን ክመበዝበዝ አልፎ ተርፎ የማን አለብኝ ስራ አየሰራ
መሆኑን መዘንጋት የለብንም።
ዉድ ሊቀ መንበራችንና ግብረ አበሮቹ ህዝቡ እንዳልተደሰተ በየቀኑ የሚደርሳቸዉን እሮሮ
እየሰሙ የመረጣቸዉን ሕዝብ በማገልገል ፋንታ የተለየ አጀንዳ እንዳላቸው ያሳያል፡
የቄሱን አቀጣጠር ባለፈው እትማችን ገልጸናል።
እኝሁ ቄስ ህዝቡን እንዲካፋፈሉ የተቀጠሩበትን ስራ እየሰሩ መሆኑን ለማንም ግልጽ ነዉ፡
እኝሁ ቄስ ”የአስተዳደር ቦርዶች እግሬ ላይ ዎድቀው ተማጥነዉኝ ነው እንጅ እኔ ለማገልገላል
ፍላጎት አልነበረኝም” ማለትም ማንነቴን አዉቀዉ ነው የቀጠሩኝ ማለታቸዉን ብዙ ሰው
ስምቶታል፡
ዪሄዉ ለቀ መንበር የማን አለብኝ ስራ እየሰራ መሆኑ ግለጽ ስለሆነ ከ ቦርዱ እንዲባረር መጠይቅ
የሁላችንም መብት መሆኑን አንዘንጋ።
ይሄው ሊቀ መንበር ካሁን ቀደም ካባረሩኝ፡”ይሄን ቤተ ክርስቲአን አዉድሜው ነው የምዎጣዉ
ማለቱን መዘንጋት የለብንም።
በሰላም ክዎጣም በኋላ የዎያኔ መንግስት ተጣሪ የሆነው ጓደኛዉ የኢትየፕያ መንግስት ደጋፊህ
ስለሆነ ተመለስ ብሎሃል ብሎ እንደመለሰዉ ለማንም ግልጽ ነዉ.
ከዎያኔ መንግስት ነጻ መሆናችንን ለማሳየት የምንችለው ይሄን ግለሰብ እስከጓደኛዉ በሰላም
ስናሰናብት ብቻ መሆኑን እዎቁ።
በሚቀጥለዉ እትም መልካም ዎሬ እንዲያሰማን እንጸልይ።