Monday, October 19, 2009

ቅሌት
ሰሞኑን “ትኩረት” በሚል ርዕስ ዉስጥ የተጻፈ በራሪ ዎረቀት አንብበናል ። ቀደም ሲል “ “ደዎል” በሚል ርዕስ
ይቀርብ ከነበረዉ ጽሁፍ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ አግኝተነዋል።
ስለ ቤተ ክርስቲያን ችግር “ትኩረት” ልትጠቁመን ሞክራ አልተሳካላትም።
ይልቁንም በዎያኔ አፈ ቀላጤዎችና ቦርድ ዉስጥ ባሉ ተወካዮቻቸዉ በኩል የተዋቀረዉ አዲሱ “ የቀድሞ የዕኛ
ሰዎች” ድርጅት ልሳን መሆኑን ተረድተናል።
ቦርድና ድርጂቱ በ”ትኩረት” አማካኝነት የቤተ ክርስቲያናችን ችግር በግለሰብና በጥቂት ሰዎች የተፈጠረ ነዉ ብለዉ
ልያሳምኑን ይሞክራሉ። በአባ ፓዉሎስ ቀሳዉስትና ዲያቆናት አማካይነት ሰፊ ቅስቀሳ እያደረጉ ነዉ፡ ለማዉገዝም
እየቃጣቸዉ ነዉ።
ከዚህም አልፎ ይህ የዎያኔና የአባ ፓዉሎስ ቡድን በከተማዉ ዉስጥ የታዎቁ የኮሚኒቲ መሪዎችን በማሳመንና
በሚቀጥለው ምርጫ የቦርድ አባል ሆነው እንዲመረጡ ቃል በመግባት የዚህ እኩይ ሃሳብ ተባባሪ አድርገዋቸዋል።
በተደረሰዉ ስምምነት መሰረት እነዚህ ግለሰቦች በከተማችን ዉስጥ በሚገኙት ሕቡዕ የማህበራዊና የፖለቲካ ፎረሞች
ላይ ዛሬ “ትኩረት” የሚያሰራጨዉን ሃሳብ አቅርበዉ ተሰብሳቢዉን ለማሳመን እየታገሉ መሰንበታቸዉ የአደባባይ
ሚስጢር ነዉ።
ከዚህም አልፈዉ ጁን ላይ በተደረገዉ አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ጉባዒ ላይ ይሄንኑ ሃስብ እነዚሁ የኮሚኒቲዉ ግለ
ሰቦች አቅርበዉና ችግሩን በሽምግልና መልክ የሚያይ ኮሚቴ ለማስመረጥ መሞከራቸዉ አይዘነጋም።
ሕዝቡ መገንዘብ ያለበት ዎያኔ በተለያየ መልክና ይዘት ሊያጠፋን የሸረበዉን ተንኮል ነዉ። ስለ መሠረታዊ ችግራችን
ከዚህ በፊት ቤተ ክርስቲያናችንን ከቀበሌ የፍርድ ሸንጎ ወደ ተቀደሰ ደብር ለመለወጥ የተደረገ ጉዞ በሚል ርዕስ ስር
የተጻፈዉን እንድታነቡት እንጋብዛለን
የኽዉም በ “ብሎጉ” መጨረሻ ገጽ ላይ “Older posts” የሚለውን ስትጫኑ ክምታገኟቸዉ ጽሁፎች አንዱ ነው።
ቸር ወሬ ያሰማን!!!!!.

No comments:

Post a Comment