Thursday, October 29, 2009

በሽምግልና ስም አይን ያወጣ ድርቅና!!!!
የፊታችን ቅዳሜ ኦክቶበር 31 2009 ዓ.ም ከቅዳሴ በኋላ ራሱን የሽማግሌ ኮሚቴ ነኝ ብሎ
የተሰባሰበዉ ቡድን ከቤተ ክርስቲያኑ የአስተዳደር ቦርድ ጋር ስብሰባ ይቀመጣል።
ስለ ቤተ ክርስቲያኑ ችግር ማወቅ የምትፈልጉ በችግሩ ዙሪያ ማን ከማን ዎገን ሆኖ
እንደሚታገልና የሽማግሌዎቹን አቋም ለማወቅ የምትሹ ሁሉ በዚህ ስብሰባ ላይ መገኘት
ይኖርባችኋል።
ማንም አባል በቦርድ ስብሰባ ላይ ተገኝቶ የመስማት መብቱ በቤተ ክርስቲያኑ መተዳደሪያ ደንብ
3፤ 8፤1 መሰረት የተጠበቀ ነዉ።
በዚህ ስብሰባ ላይ መገኘት አስፈላጊ የሚሆንበት ምክንያት ምንድን ነዉ?
1 ይህ የሽማግሌዎች ስብስብ የሚያቀርበዉን የማስታረቂያ ሃሳብ ቦርዱ ተቀብሎ ማህበርተኛዉን
ሳያማክር በስራ ላይ ለማዋል የግዴታ ዉል እንዲፈርም የጠየቀ ስለሆነ!
2 ከኦርቶዶክስ ሃይማኖት ስነ ስርአስት ዉጭ “ገለልተኝነት” የሚለዉን ሃሳብ አፍልቀዉ ዛሬ
ያለንበት ችግር ዉስጥ ያሰገቡን ስዎች ስለሚገኙበት!
3 “ገለልተኞች” የሚለዉ ሃሳባቸዉን ስራ ላይ ካዋሉ በኋላ “የካህናት እና የምእመናን ማህበር”
የሚል ድርጂት ያቋቋሙ ግለ ስቦች ስለሚሳተፉበት!
4 ይህ የካህናትና የምእመናን ማህበር የሚባለዉ ድርጅታቸዉ ቀደም ብለዉ ገለልተኞች ብለዉ ከ
አባቶች ያገለሉአቸዉን ቤተ ክርስቲያናት ባዲሱ ድርጅታቸዉ ስር አስገብቶ ለማስተዳደር ቅድመ
ዝግጅቱን የሰሩ ሰዎች ስለሆኑ!
5 የዚህ ድርጅት የዘንድሮ ስብሰባ ወጭ በመሸፈንና በማስተናገድ ሃላፊነቱን ቤተ ክርስቲያናችን
እንድትወስድ ያደረጉ ሰወች ስለሚገኙበት!
6 የዳላስ የኢትዮፕያዉያን ኮሚኒቲ ማህበር የቀድሞዉ የአመራር አባላት ስለሚሳተፉበት!
7 እነዚህ ግለሰቦች በኮሚኒቲዉ አመራር ላይ በነበሩበት ወቅት በነሱ ቁጥጥር ስር ያለዉን የሬዲዮ
ጣቢያ የኮሚኒቲዉን ችግሮች ህዝቡ እንዳያዉቅና እንዳይወያይበት ብሎም መፍትሄ እንዳያገኝ
አፍነዉ የያዙ ስለነበሩ !
8 በኮሚኒቲዉ አመራር ላይ በነበሩበት ወቅት የተለያዩ የኮሚኒቲዉን ችግሮች ከመፍታት ይልቅ
ማህበሩን የግል ስራቸዉን ማስፋፊያና የተሻለ ስራ ለመያዣ መሸጋገሪያ ድልድይ አድርገዉ
የተጠቀሙ ስወች ስለሆኑ!
9 ይህ ደብር ችግር ላይ ወድቆ ለሁለት ሲከፈል የተገነጠለዉን ቡድን ለማቋቋም በገንዘባቸዉና
በጉልበታቸዉ የረዱ ግለሰብ ስለሚገኙበት!
10 የፍሎሪዳንና የደንቨርን ቤተ ክርስቲያናት ላባ ጳዉሎስ ያስረከቡ ግለሰብ ስላሉበት!
11 ከከሳሾች ጋር ምኞትና አላማቸዉ አንድ ስለሆነ ለሽምግልና ብቃት ስለሌላቸዉ!
በኛ ግምት እነዚህ ሽማግሌወች ነን ባዮች ራሳቸዉን ተብትቦ የያዘዉን ችግርና ሃፍረት ከላያቸዉ
ለመቅረፍ ሌላ ሽማግሌ ያስፈልጋቸዋል እንላለን።
ስለዚህ ነዉ በስብሰባዉ ላይ መገኘትና የሚሉትን መስማት አለባችሁ የምንለዉ።

No comments:

Post a Comment