Wednesday, December 23, 2009

የክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች ነን? እስቲ እራሳችንን እንመርምር!!

ለእውነት ታማኝ መሆንህንና እውነትን ይዘህ መኖርህን ሲመሰክሩ በመስማቴ በጣም ደስ አለኝ። ምክንያቱም ልጆቼ እዉነትን ይዘው መኖራቸውን ከመስማት ይልቅ ሌላ ይበልጥ የሚያስደስተኝ ነገር የለም።
3ተኛው የዮኅንስ መለክት ቁጥር 3:4

እነሱ የወጡት ከኛ መካከል ነው። ይሁን እንጅ ድሮውንም ከኛ ወገን አልነበሩም። ከኛ ወገን ቢሆኑማ ኖሮ ከኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር። ነገር ግን ሁሉ ከኛ ወገን አለመሆናቸው እንዲታወቅ ከኛ መካከል ተለይተው ወጥተዋል።
1ኛ የዮሃንስ መለክት 2:19

እነዚህ ሰዎች በህልም እየተመሩ ስጋቸዉን ያረክሳሉ፡ የእግዚአብሄርንም ስልጣን ይንቃሉ። በሰማይ ክብር ያላቸውንም ይነቅፋሉ። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንኳ ስለ ሙሴ አስከሬን ከዲያብሎስ ጋር በብርቱ በተከራከረ ጊዜ “እግዚአብሄር ይገስጽህ” አለው እንጅ የስድብ ቃል በመናገር ሊፈርድበት አልደፈረም።
የይሁዳ መለክት ቁጥር 8

የክፉ ሰው ሃጢያት እንደ ወጥመድ ነው። ስለዚህ የገዛ ሃጢያቱ ወጥመድ ሆኖ ይይዘዋል።
ምሳሌ 5:22

እግዚአብሄር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ። እንዲያውም እርሱ የሚጸየፋቸው ሰባት ናቸው።እነሱም፦ በንቀት የሚመለከት ዓይን፤ ሃሰት የሚናገር ምላስ፤ ንጹሆች ሰዎችን የሚገድሉ እጆች፤ ክፉ ሃሳብ የሚያፈልቅ አዕምሮ፤ ወደ ክፋት ለመሮጥ የሚቸኩሉ እግሮች፤ በውሸት ላይ ውሸት እየጨመረ የሚናገር ምስክር፤ በወዳጆች መካከል ጠብ የሚያነሳሳ ሰው ናቸው።
ምሳሌ 6:16-19

አስተዋይ መሆን ያስከብራል። ከዳተኛነት ግን ወደ ጥፋት ያደርሳል። አስተዋይ ሰዎች ለሚሰሩት ስራ አስቀድመው እቅድ ያወጣሉ። ማስተዋል የጎደላቸዉ ስዎች ግን አላዋቂነታቸዉን ይገልጣሉ። የማይታመኑ መለክተኞች ሁከትን ይፈጥራሉ። ታማኞች ግን ሰላምን ያስገኛሉ።
ምሳሌ 13:15-17

የሃሰት እድሜ አጭር ነው። እውነት ግን ለዘላለም ትኖራለች።
ምሳሌ 12:19

ወዳጄ ሆይ! ደጉን ምሰል እንጂ ክፉውን አትምሰል። ደግ ስራ የሚሰራ ሁሉ የእግዚአብሔር ነው። ክፉ ስራ የሚሰራ ግን እግዚአብሔርን አላየውም።
3ተኛ የዮሓንስ መለክት ቁጥር 11

Tuesday, December 22, 2009

መልካም ዜና ለጌታችን ልደት !!!!!
ወዳጆቻችን በሙሉ እንኳን ደስ አለን !!
በኢትዮጵያ መንግስትና በማህበረ እርኩሳን መእመናኑን ለመከፋፈልና እርስበርሳችን ለማጋጨት
ሰንዝረዉት የነበረው ክስ እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ ከሸፈ።
ቅዱስ ሚካኤልን የሚዘርፉት ገንዘብ ሲታገድባቸው በንዴት ወደ ክስ የሄዱት ማህበረ ቅዱሳንና
ግብረ አበሮቻቸው የመሰረቱት ክስ ሁሉ በሙሉ በቅዱስ ሚካኤል ረዳትነት ካሽፏል።