Wednesday, December 22, 2010

የማቴዋስ ወንጌል መራፍ 13/24-30 
መንግሥተ ሰማያት በእርሻው ውስጥ መልካም ዘረን የዘራን ሰው ትመስላለች። ሰወቹ ሲተኙግን ጠላቱ መጣና በስንዴው መካከል ግን እንክርዳድን ዘርቶ ሄደ። ስንዴውም በቀለና ባፈራ ጊዜ እንክርዳዱ ደግሞ ያን ጊዜ ታየ። የባለቤቱም ባሮች ቀርበው ጌታ ሆይ መልካምን ዘር በ እርሻህ ዘርተህ አልነበርህምን አሉት፤- እርሱም ጠላት ይህን አደረገ አላቸው። ባሮቹም እንግዴህ ሄደን ብንነቅለው ትወዳለህን አሉት። እርሱ ግን እንክርዳዱን ስትለቅሙ ስንዴውን ከርሱ ጋር እንዳትነቅሉት አይሆንም። ተዋቸው እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ በመከር ጊዜም አጫጆችን፤- እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ ስንዴውን ግን በጎተራየ ክተቱ እላለሁ አላቸው።”
ውድ የሚካኤል ምእመን ሆይ ዛሬ የቤተክርስቲያናችን ትልቁ ችግር
1 የማህበረ ቅዱሳን
2 የማህበረ ካህናት
3 ከኋላ ሆነው የሚገፏፏቸው የወያኔ መንግስት ደጋፊወችና ጥቅመ ተስፈኞ
4 የክቡር ጠቅላይ ሚኒስተሩ ተቀዳሚ እመቤት ወ/ሮ አዜብ ጎላ ቤተሰብ የሆኑት እነ ወ/ሮ አዜብ፤አቶ ጌታቸው ትርፌ፤ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ጎላ፤ናቸው።
እንዚህ ግለ ሰቦች ቤተክርስቲያናቸን ውስጥ የሚጠነስሱትን ማወናበድና ማጋጨት ስንመለከት ከላይ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ያስተማረው ምሳሌ እንክርዳድ የተባሉት ይሆኑ? የሚል ጥያቄን በአ እምሮአችን መጣ፤
ዛሬ የምናቀርብላችሁ እንግዳ።
የሆለታው ወታደር የነበርው የተፈራ ወርቅና የአቶ በትሩ እንዲሁም የአቶ ኪዳኔ አለማየሁ ግንባር ቀደም ተናካሽ ውሻ በመሆን የዳላስ አካባቢ ተላላኪያቸው አቶ አምሃን ነው።
አኝሁ ግለ ሰብ ከራሺያዊቷ ባለቤታቸው ጋር ወደ ዳላስ ሲመጡ ዶክተር ነኝ በማለት እራሳቸውን አስተዋወቁ። ወዲያውም የማህበር ቅዱሳን ተከታይና አማኝ ነኝ በማለት ቤተክርስቲያናቸን ውስጥ ሰርገው በመግባት የማበጣበጥ ተግባራቸውን ማካሄድ ጀመሩ። ይህን የ! እዩኝ እዩኝ ባህሪያቸውን የተመከቱ ከላይ የተጠቀሱት የጥፋት መሪወች ወደ እነሱ ድርጅት እንዲገቡ አደረጓቸው። በወጣትነታቸውም ለመጠቀም እንዲያመቻቸው መለመሏቸው። ባስቸኳይም ከረሻዊቷ ባለቤታቸው አፋተው ያገራቸው ልጅ የህግ ባለሙያ የሆነች ልጅ ጋር አጋቧዋቸው። እነዚህኑ አዲስ ሙሽሮች ክስንዴው ማሳ ውስጥ እንክርዳድ አድርገው ዘሯቸው። ወዲያውኑም ከማህበረ ቅዱሳን ድርጅት ተገፍተው የወጡ አስመሰሉ። በሌላው በኩል ደግሞ ይሄው የማህበረ ካህናት ድርጅትና ተከታዮች የኢትዮጵያ ኮሙኒቴ ቦርድ እንዲሆኑ አስመረጧቸው። የስራ ዘመናቸውም አልቆ ለሁለተኛው ውድድር ሲቀርቡ እነዚሁ የከተማ አድመኞች እነ አት ኪዳኔ ዓለማየሁ ያለ ምንም ውድድር ያለምንም ድምጽ እንደገና ተመራጭ በማስመሰል ስራቸውን እንዳይለቁ አደረጓቸው። እኝሁ እንክርዳድ፤ ወጣቶች ተደራጅተው በማህበር በማቋቋም፤ በ ኢትዮጵያው ኮሚኒቴ ጥላ ስር እንደባለቅ የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ! የቦርዱ ግንባር ቀደም ተጠሪ በመሆን ድርጅቱ ኮሚኒቴው ውስጥ እንዳይገባ ያስደረጉ ግለ ሰብ ናቸው። የዚህ ደባ መነሻ የሆነው፤ የህግ ባለ ሙያ የሆነችው ባለቤቴ የድርጅቱ መሪ ትሁን በማለት ለጠየቁት ጥያቄ ተቀባይነት ባለማግኘቱ፤ የኔን ባላቤት የበላይነት የማይቀበልም ሆነ በእኛ በ እንክርዳዶቹ ያልታቀፈና ያልተደራጀ ስብስብ ኢትዮጵያ ኮሚኒቴ ወጥ አይገባም በሚል ተንኮልና ማን አለብኝነት የፈጸሙት የእብሪት እርምጃ ነው።
ዛሬም ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ክብዙ ሰወች ጋር ተጣምረው ቤተክርስቲያኑ በ ትረስቲ ቦርድ መተዳደር አለበት እያሉ ጸረ ክርስቲያናዊና ተንኮል የተሞላበት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ለዚሁ ለሚታገሉለት ትረስቲ ቦርድ ያቀረቧቸው ግለሰቦችን ትመለከቱ ዘንድ ዝርዝሩን ይዘንላቹ ቀርበናል።
1 ኪዳኔ አከማየሁ
2 ጌታቸው ትርፌ
3 ተፈራ ዎርቅ
4 በትሩ
5 ግርማቸው
6 ተኮላ
7 ፅሃይ ፅድቅ
7 ደም መላሽ
እና እንደነዚህ የመሳሰሉትን ነው።
እኝሁ ዶ/ር ነኝ ባዩ ግለሰብ ባለፈው ወር ውስጥ ካህናትን እናስታርቅ በሚል ተንኮል ቦርድ ፊት ቀርበው የማህበረ ካህናት ምልምል የሆኑ ቄስ ለማስቀጠር ጫና ሲያደሩ እንደነበረ ባለፈው እትማችን ላይ ስለተዘረዘረ እንደገና ተመልከቱት። ውድ ምእመን ሆይ አሁን ባለው ቦርድ፤ አምባ ገነናዊ ስርአት ተወግዷል፤ የጓደኛነትና
የዘመድነት ግፊትና ጫና ወድቋል፤ በምትኩም መልካም ትብብርና ለደብሩ መልካም ተግባር መፈጸም ተጀምሯል። ባኳያውም መንፈስ ቅዱስ የተመላባቸው መልካም ካህናትን አስተማሪና አስተባባሪዎች አቅርበዋል። እነዚህ እንክርዳዶች ግን መልካሙን ሰብል ለማበላሸት ጧትና ማታ እየታገሉ መሆኑን ተገንዝበን ከመልካሙ ምርት ውስጥ ለቅመን እንድንጥላቸው ቸሩ ፈጣሪ ይርዳን።
አሜን.

Saturday, December 18, 2010

ይህን የመጀመሪያውን ድንጋይ ለመወርወርና ለማስወርወር ግንባር ቀደም ሆነው የተነሱት
የቀድሞው የቦርድ አመራር አባላትና ተከታዮች፦

1 የቄስ ታደሰ ባለቤት ክህኑ ላይ ወዳጅ ይዘው ከቤታቸው በወጡበት ወቅት አንድም ቃል ያልተነፈሱ ናቸው
2 የቤተክርስቲያኑ ገንዘብ በማህበረ ቅዱሳን ሲዘረፍ አብሮ ዘራፊ የነበሩ ናቸው
3 እግዚአብሄር አንድ ያደረገውን ባልና ሚስት ማንም ሰው አንደማይለየው እየታውቀ ለማህበረ ቅዱሳን ይሄድ የነበረው ብር ሲቋረጥ፤ በዛ ተናደው ክስ የሄዱት ውይዘሮ ጥሩ አየርን እየደገፉ “ የከሰሰችው አሷ ነች እኔ አይደለሁም” እያሉ የሚያደናቁሩን
ግለ ሰብ ናቸው፤” ምናልባት ይህ አባባላቸው ው/ሮ ጥሩ አየር ዛሬ ግንባር ቀደም ከሳሽ ተብለው የሚሞገሱት ሴት ከመጀመርያ ባላቸው ተጣልተው ወደ ዳላስ ሲመጡ፤ አቶ ኪዳኔ ምስክር ለሽምግልና ቀርበው ካልጋ እንደወደቁ ያደባባይ ሚስጥር ነው።
ስለዚህ በወዳጅነት የተመሰረተው ይህ ጋብቻ ቀጣይ ዝሙት ስለሆነ አሷ ነች የከሰሰች  የሚለው አነጋገር አለመጋባታቸውን ያሳይ ይሆን? “
4 አቶ መስፍን ወልደየስ በማህበረ ቅዱሳን ስም የወሰደውን መቶ ሰላሳ ሰባት ሽህ ብር ማወራረድ አልቻለም። አሁን ከከሳሾች ጋር አድሞ ብሎግ ክፍቶ አድማ እየመታ የሚገኝ፡ በእግዚብሄር ስም ዳኛ ፊት ቀርቦ ሃሰት የመሰከረ።
5 አት ጸሃይ ጽድቅ (ሰን ሻይን) አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አገሬ አሰራለሁ ብሎ ከቤተክርስቲያን የውሰደውን ገንዘብ ላባ ጳውሎስ እጅ መንሻ በማቅረብ ከተባረከ በኋላ ተመልሶ ቤተክርስቲያናችንን ለ አባ ጳውሎስ ለማስረከብ በፍርድቤት ክርክር ላይ  ይገኛል;
6 አቶ እዩኤል ነጋ ከላይ የተጠቀሰው የቤተክርስቲያን ካዝና ብዝበዛ ሲካሄድ ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው በወንጀሉ የተባበሩና አብረው የመዘበሩ ናቸው። ሊቀ መንበር ሆነው በሚሰሩበት ወቅት፤ በአባ ጳውሎስ ተእዛዝ በአቡነ ቅወስጦስ ጉዳይ
አስፈጻሚነት እና በማህበረ ካህናት አስተባባሪነት ቄስ አወቀ ሲደልልን በሚስጥር  የቀጠሩ ናቸው።
እኝህም ካህን
1 በጾም ወራት ብር ተቀብለው የጋብቻ ስነ ስርአት ሲፈጸሙ፤-
2 እንግዳ ካህን ተጋብዘው መጥተው ሲያስተምሩ አድማ በመምታት ሽንት ቤት ቆልፈው የቅዳሴ ስርአት ሲያሳለፉ፤-
3 በተደጋጋሚ ኪዳን ለማድረስ ስለማይመጡ፤-
4 ቤተመቅደሱ ውስጥ ብጥብጥ ሲያካሂዱ፤ ከ ምእመኑም ሆነ ካስተዳደር ቦርዱ አቤቱታ ሲደርስ ቦርዱ ያስተላለፈውን
የማስጠንቀቂያ ሰነድ ለዚሁ ካህን እንዳይደርስ በተደጋጋሚ የጸደቀውን ሰነድ በመሸሸግ የአሰራር ግዴታቸውን ከ
1 ወ/ሮ ፈትለዎርቅ ጎላ
2 አት ሃይሉ አራጋው ጋር በመተባበር ለተከሳሹ እንዳይደርስ የደበቁ ናቸው። ይህን ሁሉ የማን አለብኝበት ስራ ከፈጸሙ በኋላም የመረጣቸውን አባል ሁሉ ረግጠው ከስራቸው የተሰወሩ ናቸው።
በዚሁ አቶ እዮኤልን በተመለከተ ግፊት ዋና ጸሃፊ ሆነው የሚያገለግሉበትን የማህበረ ክህነት ድርጂት አባሎች
1 አቶ ኪዳኔ አለማየሁ
2 ዶ/ር ሰለሞን አበበ
3 አቶ መሰረት አለነ
4 ዶ/ር ዓምሃን ወ ደ ቦርድ በመላክ፤ የተጣሉ ካህናትን እናስታርቃለን በሚል ዘዴ ሌላ አንደ የቄስ አዎቀ እይነት ካህን እንዲቀጥሩ የቦርዱን ጊዜ በማባከን ጫና ሲያደርጉ ከርመዋል።
8 አት ጊታቸው ትርፌም ክባለቤታቸው ከ ወ/ሮ ፈትለዎርቅ ጎላ ጋር በመሆን ቂስ  ታደሰ የቤተክርስቲያኑን አገልግሎት እለቃለሁ ብለው ሲያመለክቱ፡ ማማልከቻውን ደብቀው ሁለት አመት ሙሉ ያለ አገልግሎት ደመወዝ ሲያስከፍሉ የኖሩ ግለሰብ
ናቸው። ከዝህም በላይ የተጠቀሰው የቤተክርስቲያን ምዝበራና ወንጀል ሁሉ ሲካሄድ እያዩ እንዳላየ በመምሰል በደባው ሲተባበሩ ክመኖርም በላይ ሃሰተኛ ኦዲተር አምጥተው የቤተክርስቲያኑ ሂሳብ ምንም ያልጎደለው ለማስመሰል ሲታገሉና ሲያስፈጽሙ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ለቄስ አወቀ ሲደልልም የተጻፈባቸ ማስጥንቀቂያ ሰነድ ሁሉ እንዳይሰጥ ግፊት
ከባለቤታቸው ጋር ሲያደርጉ የኖሩ ናቸው።

እንግዲህ ምእመን ሆይ አሁን ያለው ቦርድ እንደቀድሞወቹ፤ ያወቅሁ የበቃሁ ቅዱስ ነን ብለው አልተመረጡም፤ እንደማንኛችንም ደካማ ግለሰቦች ናቸው። ከነዚህም ተመጻዳቂወች የሚለዩበት ቢኖር
1 ለተመረጡበት የሃላፊነት ስራ ለውሳኔ በሚቀርብላቸው መረጃ መሰረት በህብረት መልካም ውሳኔን ያሳልፋሉ፡
2 ጥፋት ሲያጠፉም ጥፋታቸውን ለመሸፈን አይሯሯጡም፡ ይልቅስ ጥፋታቸውን አምነው መፍትሄ ይሻሉ።
የድሮዎቹ ቦርዶች ክሁዋላ ያሰለፏቸውን የበይ ድርጅቶች በመተው ለቤተክርስቲያኑ በእውነትና በሃቅ ቢሰሩ ኖሮ እዚህ ውድቀት ውስጥ ባልገባን ነበር።
የሁላችንን ለብ የሚያውቀውና የሚመረምረው ፈጣሪያችን መልካም ትምህርቱን እንዳይነፍገን
ጸሎታችንን አናደርሳለን።
ወስብሃተ አምላክ አሜን!

Friday, December 17, 2010

አስቸኳይ መልእክት ለደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል አባላት በሙሉ።

አስቸኳይ መልእክት ለደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል አባላት በሙሉ።

ቤተክርስቲያናችንን ለማፍረስ ካሁን ቀደም የነበርው ቦርድ ጋር ተጠግተው የቤተክርስቲያኑን ካዝና ሲያራቁቱና ምዕመኑን በዘር፤ በዚጋ፤ በጓደኝነት፤ በአበ ልጅነት፤ በአብሮ ማህበር ጠጭነት ሲከፋፍሉ የነበሩ ግለሰቦችና የድሮው የቦርድ አባላት የሚመለሱበትና አንደገና የሚመዘብሩበት ጥረታቸው በፍርድ ቤት እንዳልተሳካ ስላወቁ አንዳንድ ቀዳዳ እየፈለጉ በሚመጣው ሰንበት እንደገና ቤተክርስቲያን አረከሱ በሚል የተንኮል ተግባር ብጥብጥ አስነስተው ቤተክርስቲያን ሊያዘጉ መዘጋጀታቸውን ልናበስርላችሁ እንወዳለን። እነዚሁ ግለሰቦች ሰሞኑን በቦርዱ ጸሃፊያችን ላይ የደረሰውን አንዳንድ ውዥንብርና አለመግባባት አስመልክተው ገና ያልተፈጸመ ውንጀል ልክ እንደተፈጸመ አድርገው ቤተክርስቲያኑን አሁን ያለው ቦርድ አረከሰ በሚል ሠይጣናዊ ተንኮል በየ ቤቱ እየደወሉና ህዝቡን እያነሳሱ መሆኑን ሁላችንም እናውቃለን።
እነዚህ ሰይጣናዊ አወናባጆች እጃችንን ይዘው ለጥቅማቸው ሲሉ ወደ ገሃነም ሊያስወረውሩን እንጅ እውነት ለቤትክርስቲያኑም ሆነ ለኝ አስበው እንዳልሆነ እንድንረዳ የሚቀጥለውን የአየሱስን ትምህርት የዘንላችሁ ቀርበናል፤ አብረን እናንብበው፦
የዮሃንስ ወንጌል ቁጥር 8/1-11
“-----ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዝች ሴት ወደ አርሱ አመጡ፤በመካከልም አርስዋን አቁመው፤- መምህር ሆይ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በህግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት። ---- እየሱስ ግን ጎንበስ ብሎ በጣቱ ብምድር ላይ ጻፈ፤ መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ ፤-ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድጋይ ይውገራት አላቸው። ድግሞም በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ። እነሱም ይህን ሲሰሙ ህሊናቸው ወቀሳቸውና ክሽማግሌወች ጀምሮ አስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ እየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች። እየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ፤- አንቺ ሴት እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? አላት። እርስዋም ጌታ ሆይ አንድ ስንኳ አለች። እየሱስም፤- እኔም አልፈርድብሽም ሂጅ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትስሪ አላት።----”
በተጨማሪም፤-
የማርቆስ ወንጌል ቁጥር 7/20-23
“---ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፤ ዝሙት፤ መስረቅ፤ መግደል፤ ምንዝርነት፤ መጎምጀት፤ ክፋት፤ ተንኮል፤ መዳራት፤ ምቀኝነት፤ ስድብ፤ ትዕቢት፤ ስንፍና ናቸውና ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውንም ያረክሰዋል።”
ውድ የቤተክርስቲያን አባላት፤- እንኳን ገና ምንዝር ሲሰራ ያልተያዘ ግለሰብ ቀርቶ ምንዝር በግልጽ ስትሰራ የተያዘችውን ሴት ሳይፈርድባት ሁለተኛ ኃጢአት አትስሪ ብለ ሲያሰናብታት፤ እኛ የትኞቹ ሳድቃን ሆነን ነው የመጀመሪያውን ድንጋይ የምንወረውረው።
በእግዚአብሄር ፊት “ ---ሰውን የገደለንም ሆነ የሰረቀ፤ ምንዝርነት የፈጸመም ሆነ የተዳራ፤ ተንኮል ያዘለም ሆነ የተመቀኘ፤ በሃሰት የመሰከረም ሆነ በሃሰት የከሰሰ ሁሉም” ሃጢአት እኩል መሆኑንና አንዱ ካንዱ ያማይበልጥ መሆኑን ለማሳየት እየሱስ ክርስቶስ ከላይ በማርቆስ ውንጌል ቁጥር 7/20-23 የተናገረውን ተመልሰን እናንበብ።
ታድያ እነዙህ ተንኮለኞች እናንተው ፊት ሲዋሹ፤ በሃሰት ሲመሰክሩ፤ ንጹህ የቦርድ አባላትን ገንዘብ ሰረቁ ብለው በሃሰት ሲከሱ፤ ፍርድ ቤት ቀርበው ወንጌል ጨብጠው ሲቀጥፉ መናፍቃን እይሉ መእመኑን ሲሰድቡ በማርቆስ ውንጌል ቁጥር 7/23 መሰረት የረከሱ አይደሉምን። እኛስ የነሱን የስም ማጥፋትና የማወናበድ ዘመቻ ከተቀበልን መርከስ አይሆንብንም ይሆን? መልሱን ለናንተ ፈጣሪ ልቦናችሁን ከፍቶ እንድታስተውሉት ያደርጋችሁ ዘንድ ምኞታችንን እናቀርባለን። ምናልባት ተሳስታችሁ የመጀመሪያውን ድንጋይ ለመጣል ሳይሆን ለመወርወ ለምትመኙ ሁሉ ይሚቀጥለውን አስቡ። ዋናው ጸሃፊያችን ስራውን ቢለቅ የሚጎዳው ማነው? ቤተክርስቲያኑ ወይስ ጸሃፊው? እንድ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ገና ያልተረጋገጠና ያልተፈጸመ ወንጀል አስቧልና ቤተክርስቲያን አያገለግልም ማለት የመጀመሪያውን ድንጋይ መወርወርና በሃሰትም መፍረድ መፍረድ ስለሆነ ከመሳሳታችን በፊት ደግመን ደጋግመን ነገሩን በጥሞና እናሰላስል። የተንኮለኞችን ግፊት ተከትለን
 ን በችኮላ የምናደርገው አድራጎት ግን የሚጎዳው ቤተክርስቲያናችንን አንጅ አገልጋዩን እንዳልሆነም ማመዛዘን አለብን። የህ የተባለው የቤተክርስቲያናችን አገልጋይ አገልግሎቱን ቢያቋርጥ የሚጎድልበት ጉድለት ምን ይሆን?
1 አገልግሎቱን ስላቋረጠ የሚከፈለው ደመወዝ ይቀርበት ይሆን?
2 ከሃገር ይባረር ይሆን?
3 ጊዜውን የሚያሳልፍበት ቦታ ያጣ ይሆን?
4 ሌሊቱን ቤተክርስቲያኑ ለማሻሻል ሲከራከርበት የሚያድርበት ቦታ አያገኝ ይሆን?
5 ወይስ በምንለቅለት ጊዜወች አልጋው ላይ ተኝቶ እንቅልፍ አይወስደው ይሆን?
ባኳያውም ይዚህኑ ግለ ሰብ ቦታ ተክቶ ባስቸኳይ የሚገባ ጻድቅ የሆነ ሰው አዘጋችታችሁ ማቅረብ
ያለባችሁ ግዴታ መሆኑን እንዳትዘነጉ ይሁን። አለበለዚያ የምትበድሉት የራሳችሁን ቤተክርስቲያን
ነው።
በእኛ አስተሳሰብ ወደ ቤተክርስቲያን የሚሄድና የሚጸልይ ብሎም ቤተክርስቲያን አገልግል ትብሎ
የሚጠየቅ ንጽሃን ሳይሆን አውቆም ሆነ ሳያውቅ ሃጢያት የሚፈጽምና አባክህ አምላኬ በደሌን
ይቅር በለኝ አኔም የበደሉኝን ይቅር እል ዘንድ ወደ ፈተናም አታግባኝ የሚል ሁሉ
እቤተክርስቲያን በመድረሱና በመጸለዩ ይቀር ስለተባለ ማንም ሰው ንጽህ ነው።
“እኔም አልፈርድብሽም ሂጅ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትስሪ አላት” የሚለው
የእየሱስ ጥቅስ ሃጢአት የሰራ ሁሉ ይቅር እንደሚባልና ሃጢአቱም እንደሚደመሰስ ስለሚያስረዳን
ሃጢአትም ሰርቶ የተማረ ሁሉ ንጹህ ነው።
ይሄው ጸሃፊያችን ጥፋት አጥፍቷል ብላችሁ የምታምኑ ካላችሁ መልሳችሁ ክስራው ይባረር
ሳይሆን ንስሃ ይግባ ማለት ብቻ አንጅ በወደቀ ዛፍ ላይ ምሳር ይዞ መረባረብ አይገባም።
በ እግዚአብሄርም ፊትም ሆነ በምድር ያስጠይቃል።
በትዕግስት የአስተዳደር ቦርዱ የሚወስደውን እርምጃ መጠበቅ ግን አግባብ ያለው ይመስለናል።
ለሁላችንም እንደገና የምናመዛዝንበት ልቦና ይሰጠን ዘንድ አምላካችንን እንለምን! 0

አሜን! አሜን!

Tuesday, December 14, 2010

እንዳይፈርድባችሁ አትፍረዱ

እንዳይፈርድባችሁ አትፍረዱ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፤ በምትሰፍሩበትም
መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል።
የማቴወስ ወንጌል ቁጥር 7/1

በዚህ በያዝነው ወር በ 13/2010 መረዋ የተባለው የቤተክርስቲያን ክሳሽና ቤተክርስቲያናችንን ላባ ጳውሎስ ለመሸጥ የተዘጋጀው በወያኔው ተዎካይ በ ሻለቃው የተቋቋመው ብሎግ(ጦማር) ስለ አንዱ የቤተክርስቲያናችን አገልጋይ የጻፉትን አንብበን ቆርጠው የተነሱበትን የቤተክርስቲያን ማዘጋት ትግል ለማካሄድ የማይፈነቅሉት ድንጋይና የማይጎረጉሩትን ጉድጓድ እንደሌለ ለማወቅ
አያዳግትም።
“በክርስትና ስምና በኢትዮጵያነታችሁ አሜሪካን አገር ያለውን ቤተክርስቲያን ሁሉ ብትችሉ ለኛ የምታስረክቡበትን ዘዴ ፈልጉ ባትችሉ አዘጉ” ተብለው የተለኩ የቀበሮ ለምድ ለብሰው በውስጣችን የሰረጉ ብዙ ተንኮለኞች እንዳሉ ሁላችንም እናውቃለን። የምንኖረው ህግና ደንብ የሚከበርበት ሃገር ላይ መሆኑን የዘነጉ እነዚህ ተኩላውች፡ አንድ ግለ ሰብ ፍርድ ቤት ቀርቦ ጥፋተኛ ነህ ተብሎ ገና አስታልተፈረደበት ድረስ የነጻነት መብቱ የተጠበቀ መሆኑን በመዘንጋት እንደጥፋተኛ ቆጥረው ማህበርተኛው በከፍተኛ ድምጽ
ብልጫ የመረጠውን የቤተክርስቲያን ነጻ አገልጋይ ከሃላፊነትህ ለማውረድ ቅስቀሳ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።
የዚህኑ የወያኔ ድረ ገጽ ቅስቀሳ ለማንጸባረቅ የምትመኙ ካላችሁ ልናሳስባችሁ ይምንመኘው፦
አንደኛ፤-በምድርም የግለሰብ መብት መግፈፍ ነው።
ሁለተኛ፤- በሰማእታትም “እንዳይፈርድባችሁ አትፍረዱ፡በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረዳችኋልና” ማቴወስ ቁ.7/1
ይሚለውን የየሱስ ክርስቶስን ትዕዛዝ መተላለፍ ነው።
“ታስረው እሑድ ከቤተክርስቲያን መጥተው የምእመናንን ዓይን እያዩ ማስታወቂያ መናገራቸው ቢገርመንም” ለሚለው መልስ በቀላሉ እናንተ ብሆዳችሁ ቂም ይዛችሁ “ዛሬ ምን ይባል ይሆን ቤተክርስቲያን ሄደን ምን እንደሚባል እንሰልል” በማለት ሃይማኖተኛ ለመምሰል የእግራችሁን ጫማ አውልቃችሁ የልባችሁን አሳት ይዛችሁ ወደተቀደሰው ቦታ መግባታችሁን የማያውቅ ም
እመን ይኖር ይሆን?
የጠቀሳችሁት ግለ ሰብ ሊያገለግሉ፤” የመጣውን ምእምን ዓይን እያየ የተናገረው” ላላችሁት አገልጋዩ በሆዳቸው ተንኮል ተሸክመው አለመሆኑን ተረዱ። ጥፋት ቢያጠፉም እንኳን፡ ፈጣሪይቸውን ሰው ነኝና ጥፋት አጥፍቻለሁ ማረኝ። የልቤን እምታውቀው አንተ ነህና ይቅር በለኝ ሳይሉ ወደ መድረክ እንደማይገቡ አንጠራጠርም። አምላካችንም እውነት ጥፋት አጥፍተው እንደሆነ አንደ ማራቸው እናምናለን። የናንተን ትንኮልና መርዝ መርጨት የቤተክርስቲያናችን ምእመን የለመደው ስለሆነ በእናንተ
ተንኮል አይበገርም። ለማለቱማ ድሮ ጀምሮ እኝሁን መልካም አስተዳዳሪ ያላላችኋቸው ስድብና
ዘገባ  ይኖር ይሆን?  
ለዛሬው ይሄን የመርዝ ማለስለሻ ይዘንላችሁ ቀርበናል። 
ሰሞኑን በዝርዝር ተፈጸመ የተባለውን አለመግባባት እስትናቀርብላችሁ ድረስ አወናባጆች እንዳያውናብዷችሁ አደራ እንላለን።
ዋናው መታወቅ ያለበት እኝሁ የተባሉት ግለሰብ ህዝቡ የጣለባቸውን እምነት ለመወጣት ሌት
ተቀን ደከመኝ ክስራ አስተጓጎለኝ ሳይሉ ጉልበታቸውን ጊዚያቸውንና ገንዘባቸውን በነጻ የሚሰጡ መልካም አገልጋያችን ስለሆኑ፤ እንኳን አሉ ባልታ ቀርቶ አዉነት አጠፉ ተብለው  ቢፈረድባቸውም ማስወጣት ቀርቶ ጊዜያቸውንም ሲጨርሱ ካገልግሎት እንዳይወርዱ
የምንማጠናቸው ግለሰብ መሆናቸውን የቤተክርስቲያኑ ምእመን ሁሉም ባንድ ድምጽ ደጋፊያቸው መሆኑን ለጠላቶቻችን እናበስራለን። በ መረዋ ብሎግ ላይ የተፍለጠፈው ተግባር እውነት አለመሆኑን ለመረዳት ከፈለጋችሁ በመጀፍመርያ መጠየቅ ያለባችሁ ነገር ቢኖር መረዋ “የመንገድ ሴተኛ አዳሪ ሲያነሱ ተገኝተው” ያለው የተባለችው ሴተኛ አዳሪ የተነሳችው ለግብረ ስጋ ነው? ወይስ ለሚያካሂዱት የእንጀራ ጋጋሪነት ስራ እንድትሰራላቸው ይሆን? ብሎ ማመዛዘን ተገቢ በሆነ ነበር። በፍርድ ቤት እውነቱ  ውጥቶ እስቲፈርድ ድረስ መታገስን አለመሻት ከዓምላካቸን ጋር እንደሚያጣላን አንጠራጥርም።
የቤተክርስቲያኑ አባላትም ይህንኑ አምኖ ቦርዱ በጊዜው የሚወስደውን እርምጃ በጥሞና
እንዲጠብቅ ጥሪአችን ይድረሳችሁ።
ለሁላችንም አምላካችን የሚያመዛዝን ልቦና እንዲሰጠን እንጸልይ።


አሜን!