Friday, February 26, 2010

የቤተ ክርስትያናችን ችግር!!!

በአቶ ኢዮኤል ነጋና በአቶ ጌታቸው ትርፌ የበላይ አቀነባባሪነት የሚንቀሳቀሰው ቡድን ምርጫዉን አክብሮ መቀበል አቅቶታል። እነዚህ ቡድኖች ነጻ አገልግሎት የሚስጥበትን ስራ ላለመልቀቅ ህዝብን ግራ አስቲገባው ድረስ ሙጥኝ ብለው የሚታገሉት ለምን ይሆን? በተከታዮቻቸው አማካኝነት ዶክተር ግርማና አቶ አበራ የቤተክርስቲያኑን ገንዘብ ለመዝረፍ ሲሉ በጦር መሳርያ ሃይል ተደግፈው ኩዴታ ፈጥረው ራሳቸውን ቦርድ ብለው የሰየሙ ሰዎች ናቸው ብለው ሊያሳምኑን እየሞከሩ ነው።

ቤተክርስቲያናችን ችግር ውስጥ የገባችው በነዚህ ሁለት ግለሰቦች ምክንያት ነው ብላችሁ እመኑ እያሉን ነው። ተረት ተረቱን ለነሱ እንተወውና እነዚህ ግለሰቦች ቦርድ ውስጥ የገቡት መች ይሆን? ሁላችሁም እንደምታስታውሱት March 2008 ላይ ነው።

Thursday, February 25, 2010

ወያኔ ካድሬዎችን ለመመልመል ጉባኤ ጠራ!!!!

ውድ ምእመናን ሆይ!
ቀደም ሲል የወያኔ ተወካዮች የመተዳደርያ ደንባችንን ለውጠው ቤተ ክርስቲያናችንን ለአባ ጳውሎስ አሳልፎ ለመስጠት ያደረጉት ጥረት መክሸፉን አንዘነጋውም። ከዛም የሚካኤልን ታቦት ከሰው ፍርድ ቤት እያመላለሱን ይገኛሉ። ባንጻሩም ምእመናን ቦርድ ውስጥ የነበሩትን ተወካዮቻቸዉን በድምጽ ብልጫ ማስወገዳችን የሰሞኑ ትኩስ ዜና ነው።

በዚህ የተበሳጩት የወያኔ ካድሬዎች ደካማ ህሊና ያላቸውን ሰዎች መልምለው የቤተ ክርስትያን አባል ካደረጉ በኋላ በደምጽ ብልጫ ቤተክርስትያናችንን ለመውሰድ በድፍረት ጉባኤ ጠርተዋል። ወያኔ ለጀመረው ክስና ለአባላት ምልመላ መጠነ ሰፊ ብር መድቧል።

ይህንን ጉባኤ በግንባር ቀደምትነት የሚያስተባብሩት የከተማው ከበርቴዎች ቀደም ሲል ብዙ የዳላስ ነዋሪዎችን በሽርክና አብረን ንግድ እንክፈት እያሉ ሲዘርፉ የነበሩ ግለሰቦች መሆናቸውን እናውቃለን። ዛሬ አልማ (የአማራ የልማት ማህበር) የሚባል ድርጅት አቋቁመው ሁለተኛ ዙር ዘረፋ በህዝቡ ላይ ለማፋፋም ወያኔ ያሰባሰባቸው ግለሰቦች ናቸው።

እኛ ደሃዎቹና ደካሞቹ ለነዚህ ሃያላን አምላክ ቀና መንፈስ እንዲሰጣቸው በጸሎት እንትጋ!
አሜን!!

Wednesday, February 24, 2010

ከኛ ወድያ ክርስትና ለአሳር!!!!

የቤተ ክርስቲያን ቀማኞችና ማህበረ ቅዱሳን ጾም ማለት ዶሮ ወጥና ስጋ አለመብላት ይመስላቸዋል። ከአንዳንድ የዳላስ አካባቢ ነጋዴዎች ጋር በመሆን ቅዳሜ ቤተ ክርስቲያንን ለማዳን በሚል የሃሰት ተንኮል ለመሰብሰብ አስበዋል። እነዚህ አወናባጆች እውነተኛ ክርስቲያን ሳይሆኑ ለጥቅም የሚሯሯጡ ተስፈኞች መሆናቸውን ለመረዳት ችለናል።

በሁዳዴ ጾምና ጸሎት ላይ ያለ አማኝ ስነ ልቦናውን ከአለማዊ ነገር አርቆ ፈጣሪውን የሚማጸንበት ወቅት ነው። ችግሮች ቢኖሩ እንኳን አምላክ መፍትሄ እንዲሰጠው የሚጸልይበት ጊዜ ነው። የቤተክርስቲያን ከሳሾች ግን አድማ የሚመታበት ወቅት አድርገውታል። ከኛ ወድያ ክርስትና ለአሳር ብለው የሚመጻደቁት ከሳሾችና ግብረ አበሮቻቸው ጾም እስቲወጣ መታገስ ያቃታቸው ለምን ይሆን????

Thursday, February 4, 2010

የሰሞኑ ዚና፤
ሰንበቲን የመሰለ ብሎግ በየአቅጣጫው በዳላስ አካባቢ መከፈቱን ሰምተን በታላቅ ምርምር
ከደረስንበት በኋላ ለናንተ ለማቅረብና በየጊዚው ምን እንደሚወራ እንድታውቁ ለማድረግ ከዚህ
በታች የብሎጎቹን ስምና አድራሻ እናቀርብላችኋለን።
http://selam-tewahedo.blogspot.com/

http://merewametta.blogspot.com/

http://selam-tewahdo.blogspot.com/
ይሄ ብሎግ የተቋቋመው ሰላም ተዋሄዶ
የሚለዉን ብሎግ ለመቃወም ይመስለናል ።
በደንብ ብታዩት አንድኛው ሰላም ትዋሄዶ ሲል ሊላው ሰላም ተዋህዶ የሚል ይመስላል ስለዚህ
ሰላም ተዋሄዶ ከሚለው ላይ ከ (H) ብኋላ ያለዉን (e) አጥፍታችሁ (enter) የሚለዉን
ብትረግጡ ወደ ሰላም ተዋህዶ ትሂዳላችሁ።
ለዛሪ ያቀረብንላችሁ ይሄ ነው።
እግዚአብሄር የዳላስ አካባቢ ይሆኑትን ክርስቲያኖች ይባርክለን፡
ስምምነቱን ይዳርግልን።
አሜን አሜን እንላለን!!!!!