Wednesday, February 24, 2010

ከኛ ወድያ ክርስትና ለአሳር!!!!

የቤተ ክርስቲያን ቀማኞችና ማህበረ ቅዱሳን ጾም ማለት ዶሮ ወጥና ስጋ አለመብላት ይመስላቸዋል። ከአንዳንድ የዳላስ አካባቢ ነጋዴዎች ጋር በመሆን ቅዳሜ ቤተ ክርስቲያንን ለማዳን በሚል የሃሰት ተንኮል ለመሰብሰብ አስበዋል። እነዚህ አወናባጆች እውነተኛ ክርስቲያን ሳይሆኑ ለጥቅም የሚሯሯጡ ተስፈኞች መሆናቸውን ለመረዳት ችለናል።

በሁዳዴ ጾምና ጸሎት ላይ ያለ አማኝ ስነ ልቦናውን ከአለማዊ ነገር አርቆ ፈጣሪውን የሚማጸንበት ወቅት ነው። ችግሮች ቢኖሩ እንኳን አምላክ መፍትሄ እንዲሰጠው የሚጸልይበት ጊዜ ነው። የቤተክርስቲያን ከሳሾች ግን አድማ የሚመታበት ወቅት አድርገውታል። ከኛ ወድያ ክርስትና ለአሳር ብለው የሚመጻደቁት ከሳሾችና ግብረ አበሮቻቸው ጾም እስቲወጣ መታገስ ያቃታቸው ለምን ይሆን????

No comments:

Post a Comment