Friday, April 30, 2010

የቄስ መስፍን ደምሴ ከቅዱስ ሚካኤል ስንብት!

እንደምታውቁት ቄስ መስፍን ደምሴ ባለፈው እሁድ መጽሃፍ ቅዱስ ለአማኙ ምእመን ለማስተማር ወጥተው የእየሱስ ክርስቶስና የመላእክት ስም የሚነሳበትን የቅዳሴ መድረክን ላይ የራሳቸውን እሮሮ እየዘረዘሩና ህዝቡን ለማራበሽ አይዟችሁ እያሉ ግብረአበሮቻቸው እንዲተባበሯቸው ጥሪ ሲያደርጉ አርፍደዋል። እኝህ አባት ቄስን የሚሾመው “ እግዜአብሄር እንጅ ሌላ ቄስ ወይም እግዜአብሄር በምስሉ የፈጠረው ስው አይደለም” ባሉበት አንደበታቸው በጥቂት ደቂቃ ውስጥ ያሉትን ዘንግተው ራሳቸውን ከባትሪ ጋር አመሳስለው ባትሪዬ አለቀ ብለው አሉ። እኔ የማስተምረው እዉነቱን የእግዚአብሔርን ቃል ነው በማለትም ተናገሩ። ታዲያ የባትሪዉን ማለቅ የማን ቃል ብለን እንውሰደው።
ቄስ መስፍን ደምሴ የማህበረ ቅዱሳን አባል ናቸው። ቅስና ሰጥቷቸው የሾማቸውና እኛ ቤተ ክርስትያን ላይም የመደባቸው ይሄው ማህበረ ቅዱሳን ነው። ቄስ መስፍን ለምን ራሳቸውን ከስራ ለማሰናበት ወሰኑ ብለን ብንጠይቅ? መልሱን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጥቅላይ ጽ/ቤት በ ቀን 27/01/2009 ዓ.ም በቁጥር ል/ጽ/55/2002 ያስተላለፈውን ውሳኔ ላይ ልናገኝ እንችላለን።
በ ገጽ 6 በማህበረ ቅዱሳን አባላት ላይ በማደራጃ መምሪያው የቀረበ ክስ እንጠቅሳለን “በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በወረዳ ቤተ ክህነትና በሃገረ ስብከት ሥራ ጣልቃ እየገባ ምስጢሩ ያልገባቸውን ንጹሓን ወጣቶች በማነሣሣት ሰላም የሚነሣ ችገር እንዲፈጠር ማድረጉ፤” “ማህበሩ በኢትየጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ ሥር ሆኖ መንቀሳቀስ ሲገባው በውጭ ዓለም ከሚገኙ ትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስና የቅዱስ ፓትርያርኩን አመራር ከማይከተሉ አባላት ጋር ሆኖ በመስራት ላይ የሚገኝ መሆኑ፤” በማለት ላቀረበው ክስ የተሰጠውን መመሪያ በ ገጽ 12 ላይ እንደገና እንጠቅሳለን “ 1. ማህበሩ ከዛሬ ጀምሮ ግንኙነቱ በመተዳደሪያ ደምቡ መሠረት ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ጋር ብቻ ይሆናል፤ ከመምሪያው እውቅና ውጨ የሚፈጽመው ክሦስተኛ ውገን ጋር ግንኙነት ሕገ ወጥ መሆኑን እንዲገነዘብ፤” በማለት ውሳኔ በመሰጠቱ ምክንያት;- የሚካኤል ቤተክርስቲያን በአባ ጳውሎስን የማይቀበል በሲኖዶሱ የማይተዳደር ገለልተኛ ቤተክርስትያን ስለሆነ የቄስ መስፍን በሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማገልገል ህጋዊና አግባብ አይደለም። ይህንኑ ተረድተው የወሰኑት ውሳኔ ነው ብለን እንገምታለን።
ሌላው ተአምር መላከ ሳህል አወቀ ሲደልል ባጠፉት ጥፋት ሲባረሩ የሚካኤልን ተአምር ያዩት ቄስ መስፍን እንዳሰቡት የሚካኤል ቤተክርስቲያን የቆመው ለምእመኑና ገለልተኛ እንጅ ለማህበረ ቅዱሳን አለመሆኑን ስለተረዱና የተጠነሰሰው ደባ ሁሉ እየከሸፈ መሄዱን በመመልከት በምንም ተአምር የሚካኤል ቤተክርስቲያን ለአባ ፓውሎስ እንደማይሄድ ስለተረዱ ነው።ሆኖም ግን በመጨረሻ ሰአትም ቢሆን በሰላም ከመሰናበት ይልቅ የተለመደውን የማህበረ ቅዱሳን ዘዴ በመጠቀም ህዝቡን ለማበጣበጥ ያቀዱት ሴራ ከሽፏል።
ውድ ምእመን ሆይ የማህበረ ቅዱሳን አባል የሆኑት ቄስ መስፍን ደምሴ እውነተኛ ቄስ ቢሆኑ ኖሮ እላይ እንደጠቀስነው ስጋውንና ደሙን ለሰው ለጅ የሰጠው የእየሱስ ክርስቶስ ስም በሚጠራበት መድረክ ላይ ቆመው የግል እሮሯቸውንና (call to arms) ጥሪ ባላደረጉ ነበር።
ይጅወትንና የልብወን አምላክ ይስጥልን ከማለት በቀር ሌላ የምናደርገው ነገር ስለሌለ ዛሬ በዚህ እንሰናበታለን።
ሃያሉ አምላካችን ቤተክርስቲያናችንን ከማናውቀው ጠላት ይጠብቅልን፤
አሜን!--

Wednesday, April 28, 2010

የደጀን ለዲሞክራሲ አንጃዎች በዳላስ ሚካኤል ላይ ጥቃት እየሰነዘሩ ነው!!!!

ደጀን ለዲሞክራሲ የሚባለው የዳላስ የፖለቲካ ፎረም ከፍተኛ የአመራር አባላት ከ 04/25/10 ዓ.ም ጀምሮ ጸረ ቤተክርስቲያን ሰብሰባ እያደረጉ መክረማቸው ታወቀ። ሰብሰባውን የሚመሩት የደጀን ለዲሞክራሲ ከፍተኛ የአመራር አባላት፤-

1 የሆለታው ሻለቃ ተፈራወርቅ አሰፋ
2 አቶ በትሩ ገ/እግዚአብሔር የተባሉ ግለሰቦች ናቸው።

ይህንን ሰብሰባ በጅ መርጠው ከጠሯቸው ግለ ሰቦች ጋራ ማድረጋቸው ታውቋል። በዚህ ሰብሰባ ላይ ከተሳተፉት ግለ ሰቦች መሃል፤-

1 መላከ ሳህል አወቀ ሲደልል (በቅርቡ ከስራ የተሰናበቱ)
2 ቄስ መስፍን ደምሴ (04/25/10 ዓ.ም ምእመን ፊት ለማሰተማር ቀርበው ወንጌል ከማስተማር ይልቅ በመቅደሱ መድረክ ላይ ቆመው የስንብት ንግግር በማደረግ ሥራቸውን በፍቃዳቸው መልቀቃቸውን ያወጁ)
3 አቶ ተኮላ መኮንን (የወያኔ የአማራ ልማት ድርጅት አባል፤ቤተ ክርስቲያንን የከሰሱ ቡድኖች ግንባር ቀደም ደጋፊ በመሆን ሁልጊዜ ፍርድ ቤት የሚቆሙ፤ ብዙ ህዝብ አስተባብሬ የሚካኤል አባል እንዳይሆኑና ብር እንዳይሰጡ እስተባብሬአለሁ እያሉ የሚመጻደቁ፤
ባይሎው ለውጨ ላባ ጳውሎስ ካላስረከብኩ ብሎ የሚታገሉ፤ በአሁኑ ሰዓት ቦዘኔ የሆኑ LOOSER) እነዚህን የመሳሰሉ ገለሰቦች ይገኙበታል።

እነዚህ አንጃ የደጀን አመራር አካላት በ04/25/10 ዓ.ም ቄስ መስፍን የስንብት ንግግር አደርገው እንዳበቁ፤ ለቡራኬ ሳይቀርቡ ጸበል ስይቀምሱ በሆለታው ሻለቃ መሪነት ተከታትለው ክቤተክርስቲያን ዉስጥ በመውጣት ፓርኪን ሎት ላይ ተገናኝተው ሲመካከሩ ታይተዋል። የጥቃቱን መጀመርያ ዱላ እንደ ሪሞት ኮንትሮል ኦፍ ኤንድ ኦን በሚያደርጉት የሬድዮ ሰራተኛቸው በአቶ ዘውገ ቃኘው አማካኝነት፤ ጸጥታ ለማስከበር ቤተክርስቲያን በተገኙ ፓሊሶች ላይ የተዛባ ሃተታ በማቅረብ ከፈቱ።

ላዛሬ እንድታውቁት የምንፈልገው እነዚህ ግለ ሰቦች የኢትዮጵያን ኮሙኒቲ ራዲዮ ተገን በማድረግ ቤተክርስቲያን ላይ ደባ መጀመራቸውን እና በየቦታው ስብሰባ እያካሄዱ መሆናቸውን እንድትረዱ ነው።
ወደፊት የስብሰባቸውን አጀንዳና የነዚህን አንጃ ወዶ ገብ ወያኔዎች የህይወት ታሪክ እናቀርብላችኋለን።

ፈጣሪያችን ከነዚህ ሃያላን ፍላጻ እንዲጠብቀን እንጸልይ!
አሜን! አሜን! እንላለን።

-

Friday, April 23, 2010

እንደምን ከረማችሁ!!
 ይህን ግጥም አብረን እናንብብ።
            ማነህ አንተ የቅርባችን እሩቅ?
            እኛማ እኛ ነን ያንተስ ከየት ይሆን?
            ያስተሳሰብህ መደቡ? ማነህ አንተ?
            ሳጥናኤል ነህ ከንቱኤል? ዳንኤል ነህ ዋሾኤል?
           “ጋሼ!” በሉኝ የምትል፤የአዛውንት ቅምጥል፤
           ያለባበስና የንግግር ሊቅ! የት ነህ አንተ የቅርባችን ሩቅ?
           ሆደ ባሻ ነህ! ወንድም ውሻ? ወንድም ጋሻ ነህ የተስፋ እርሻ?
          ባለ ራእይ ነህ ወይስ ተልካሻ?
                   እባክዎ “እርሶ” ማኖት አንቱ? እውነቱ ወይስ ክህደቱ?
                  ቃሎት የሆነብን ከንቱ? ማኖት እርሶ?
                  ለተስፋና ለፍቅር፤ ፍጻሜው ሆነብን እንጂ - ቃል ብቻ የቃል ክምር!
                  አንተኛውስ ማነህ?
        ጆሮጠቢ ነህ የገንዘብ ወፍጮ?
        መቀጮ ነህ ወይስ መዋጮ?
       ማነህ አንተ? ማነሽ አንቺ? የት ነሽ አንቺ?
       እና እኔ ደግሞ ለማን እንደሆነ ባላውቅም!
       “እባክህ ማነህ አንተ?” ብዬ ጠየቅሁ።
                እንደሆዱ ነህ እንዳንጎሉ? የት ነው ያስተሳሰብህ ክልሉ?
                የራእይ ኮከብ ቃሉ? የት ነው? ማነህ አንተ? የት ነህ አንተ?
                ምነው የህሊናህ ባንዴራህ ተደበቀ?
               ምነው ክብርህና ኩራትህ ተሳቀቀ?
    ማነህ አንተ? ጀብደኛ ነህ ቀልደኛ? ወይስ ተመጻዳቂ ህልመኛ?
    እና የት ነህ አንተ? ማነህ አንተ? ወንድም ውሻ? ወይስ ወንድም ጋሻ? 
                                           ከደራሲ ተስፋየ ገብረአብ የተወሰዱ ግጥሞች።

Friday, April 16, 2010

የቤትክርስትያናችን ችግሮች!! 

የቤተክርስቲያናችንን ችግሮች በተመለከተ ዛሬም ይዘን ቀርበናል። የቤተክርስትያን አባላት የሆኑት አቶ ኪዳኔ ምስክርና አቶ ኢዮኤል ነጋ ከሌሎች ተባባሪዎቻቸው ጋር በመሆን ላቋቋሙት መንፈሳዊ ድርጅቶች ያወጡትን የስራ ፈቃዳቸውን አብረን እንመልከት።

Saturday, April 10, 2010

የቤተክርስቲያናችን ችግሮች!!!

ውድ ምእመናን የቤተክርስቲያናችንን ችግሮች በተመለከተ ያቀረብናቸውን ጽሁፎች ስላነበባችሁ ክልብ እናመሰግናለን። ዛሬ ማህበረ ቅዱሳን ከቤተ ክህነት ጠቅላይ መምሪያ ተእዛዝና ተልኮ ውጭ በአምባ ገነንነት ወደ ምድረ አሜሪካ በመምጣት በሰበካ ቤተክርስቲያኖች ላይ ካደረሷቸው ጥቃቶች መሃል በሎስ አንጀሎሱ የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ላይ ያደረሱትን ምእመናንን የመከፋፈልና የስም ማጥፋት ዘመቻ ይዘንላችሁ ቀርበናል። የእኛ ቤተክርስቲያን ላይ እያደረሱ ካለው ጥፋት ጋር ተመሳሳይ ሆኖ አግኝተነዋል።
አብረን እናንብበው። ምናልባት አስፈላጊ ትምህርት እናገኝበታለን ብለን እናምናለን።`

Thursday, April 1, 2010

የቤተክርስትያናችን ችግሮች!!!

ውድ አንባብያን ሆይ የቤተክርስትያናችንን ችግሮች በተመለከተ እስከዛሬ ድረስ ያቀረብነውን መረጃወች ስላነበባችሁ እናመሰግናለን። ዛሬ ደግሞ ማህበረ ቅዱሳን፦ 
1 በራሳችን ደብር ላይ ሲፈጽመው ከነበርው ዳባዎች መሃከል ጥቂቱን፦
2 ኢትዮጵያ ውስጥ የማህበሩ አባል አልሆንም ባሉ ካህን ላይ የድርጂቱ መሪ የሆኑት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ያደረሰውን የስም ማጥፋት ዘመቻ ፍርድ ቤት ደርሶ የተሰጠውን የፍርድ ብያኔ፡-
3 ይህ ድርጅት ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ትእዛዝ ውጭ ሲያደርግ የነበረውን እንቅስቃሴ ለአብነት ያህል ይዘን ቀርበናል።
አብረን እናንብበው።-