Friday, April 30, 2010

የቄስ መስፍን ደምሴ ከቅዱስ ሚካኤል ስንብት!

እንደምታውቁት ቄስ መስፍን ደምሴ ባለፈው እሁድ መጽሃፍ ቅዱስ ለአማኙ ምእመን ለማስተማር ወጥተው የእየሱስ ክርስቶስና የመላእክት ስም የሚነሳበትን የቅዳሴ መድረክን ላይ የራሳቸውን እሮሮ እየዘረዘሩና ህዝቡን ለማራበሽ አይዟችሁ እያሉ ግብረአበሮቻቸው እንዲተባበሯቸው ጥሪ ሲያደርጉ አርፍደዋል። እኝህ አባት ቄስን የሚሾመው “ እግዜአብሄር እንጅ ሌላ ቄስ ወይም እግዜአብሄር በምስሉ የፈጠረው ስው አይደለም” ባሉበት አንደበታቸው በጥቂት ደቂቃ ውስጥ ያሉትን ዘንግተው ራሳቸውን ከባትሪ ጋር አመሳስለው ባትሪዬ አለቀ ብለው አሉ። እኔ የማስተምረው እዉነቱን የእግዚአብሔርን ቃል ነው በማለትም ተናገሩ። ታዲያ የባትሪዉን ማለቅ የማን ቃል ብለን እንውሰደው።
ቄስ መስፍን ደምሴ የማህበረ ቅዱሳን አባል ናቸው። ቅስና ሰጥቷቸው የሾማቸውና እኛ ቤተ ክርስትያን ላይም የመደባቸው ይሄው ማህበረ ቅዱሳን ነው። ቄስ መስፍን ለምን ራሳቸውን ከስራ ለማሰናበት ወሰኑ ብለን ብንጠይቅ? መልሱን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጥቅላይ ጽ/ቤት በ ቀን 27/01/2009 ዓ.ም በቁጥር ል/ጽ/55/2002 ያስተላለፈውን ውሳኔ ላይ ልናገኝ እንችላለን።
በ ገጽ 6 በማህበረ ቅዱሳን አባላት ላይ በማደራጃ መምሪያው የቀረበ ክስ እንጠቅሳለን “በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በወረዳ ቤተ ክህነትና በሃገረ ስብከት ሥራ ጣልቃ እየገባ ምስጢሩ ያልገባቸውን ንጹሓን ወጣቶች በማነሣሣት ሰላም የሚነሣ ችገር እንዲፈጠር ማድረጉ፤” “ማህበሩ በኢትየጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ ሥር ሆኖ መንቀሳቀስ ሲገባው በውጭ ዓለም ከሚገኙ ትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስና የቅዱስ ፓትርያርኩን አመራር ከማይከተሉ አባላት ጋር ሆኖ በመስራት ላይ የሚገኝ መሆኑ፤” በማለት ላቀረበው ክስ የተሰጠውን መመሪያ በ ገጽ 12 ላይ እንደገና እንጠቅሳለን “ 1. ማህበሩ ከዛሬ ጀምሮ ግንኙነቱ በመተዳደሪያ ደምቡ መሠረት ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ጋር ብቻ ይሆናል፤ ከመምሪያው እውቅና ውጨ የሚፈጽመው ክሦስተኛ ውገን ጋር ግንኙነት ሕገ ወጥ መሆኑን እንዲገነዘብ፤” በማለት ውሳኔ በመሰጠቱ ምክንያት;- የሚካኤል ቤተክርስቲያን በአባ ጳውሎስን የማይቀበል በሲኖዶሱ የማይተዳደር ገለልተኛ ቤተክርስትያን ስለሆነ የቄስ መስፍን በሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማገልገል ህጋዊና አግባብ አይደለም። ይህንኑ ተረድተው የወሰኑት ውሳኔ ነው ብለን እንገምታለን።
ሌላው ተአምር መላከ ሳህል አወቀ ሲደልል ባጠፉት ጥፋት ሲባረሩ የሚካኤልን ተአምር ያዩት ቄስ መስፍን እንዳሰቡት የሚካኤል ቤተክርስቲያን የቆመው ለምእመኑና ገለልተኛ እንጅ ለማህበረ ቅዱሳን አለመሆኑን ስለተረዱና የተጠነሰሰው ደባ ሁሉ እየከሸፈ መሄዱን በመመልከት በምንም ተአምር የሚካኤል ቤተክርስቲያን ለአባ ፓውሎስ እንደማይሄድ ስለተረዱ ነው።ሆኖም ግን በመጨረሻ ሰአትም ቢሆን በሰላም ከመሰናበት ይልቅ የተለመደውን የማህበረ ቅዱሳን ዘዴ በመጠቀም ህዝቡን ለማበጣበጥ ያቀዱት ሴራ ከሽፏል።
ውድ ምእመን ሆይ የማህበረ ቅዱሳን አባል የሆኑት ቄስ መስፍን ደምሴ እውነተኛ ቄስ ቢሆኑ ኖሮ እላይ እንደጠቀስነው ስጋውንና ደሙን ለሰው ለጅ የሰጠው የእየሱስ ክርስቶስ ስም በሚጠራበት መድረክ ላይ ቆመው የግል እሮሯቸውንና (call to arms) ጥሪ ባላደረጉ ነበር።
ይጅወትንና የልብወን አምላክ ይስጥልን ከማለት በቀር ሌላ የምናደርገው ነገር ስለሌለ ዛሬ በዚህ እንሰናበታለን።
ሃያሉ አምላካችን ቤተክርስቲያናችንን ከማናውቀው ጠላት ይጠብቅልን፤
አሜን!--

No comments:

Post a Comment