Wednesday, August 26, 2009

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ርዕሰ አድባራት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አመሰራረቱ እና የአስተዳደር መዋቅሩ እንደሚከተለው ነው።

የዚህ ደብር ባለቤትና ዋና አካል የሆኑት የአባልነት ግዴታቸውን ያምዋሉ ምእመናን ሲሆኑ የእለት ተእለት አስተዳድራዊ ሥራዎች ደግሞ በመእምናኑ በተመረጡ ዘጠኝ የቦርድ አባላት ይከናወናሉ። እነዚህም ዘጠኝ የቦርድ አባላት ተጠሪነታቸው ለአባላቱ ነው።

ተጠሪነታቸው ለአስተዳደር ቦርድ የሆኑ የተለያዩ ንኡሳን ኮሚቴዎች በቦርዱ አማካኝነት ይቅዋቅዋማሉ፤ በቦርዱ አማካኝነትም ሊታጠፉ ይችላሉ።
የቦርድ አባላቱ የትመረጡበትን ኃላፊነት ለመወጣት በየአመቱ በፈረቃ እርስ በራሳቸው ተመራርጠውና የሥራ ድርሻ ተከፋፍለው ይሰራሉ።

ምሳሌ፡

ሊቀመንበር
ም/ሊቀመንበር
ዋና፡ ጸሐፊ
የሂሳብ ሹም
ገንዘብ ያዥ……ወዘተርፈ

በዚህ አይነት የሥራ ድልድል ካደረጉ በህዋላ የአስተዳደር ቦርድ አባላት እንደ አንድ ኮሚቴ በመሆን በአምላክና በምእመናን ፊት ቀርበው የገቡትን ቃል ኪዳን ለመፈጸም ይጥራሉ።

ሊቀመንበር ሆኖ የሚመረጠው ግለሰብ በቦርድና በአባላቱ የተላለፉትን ውሳኔዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን እየተከታተለ ማስፈጸም ካልሆነ በስተቀር የፍጹማዊ አምባገነንነት ስልጣን የለውም። የአስተዳደር ቦርዱ አባላት ያላቸውን ሃሳብ በአጀንድ አስይዘው በቦርዱ ጉባኤ ላይ አቅርበው ተቀባይነትን ካገኘ ሃሳባቸው በሥራ የሚተረጎምበትን መንገድ ቦርዱ በህብረት ይፈልጋል። ካልሆነም ሃሳቡ ውድቅ ይሆናል።

ይህ ደብር ማንም የቦርድ አባል ከቦርድ ጉባኤ እና ከአባላት ምእመናን ጉባኤ ውሳኔ ውጭ የራሱን ሃሳብ እና ምኞት የሚያንጸባርቅበትና በሥራ ላይ ለማዋል ጫና የሚያደርግበት ቤተክርስቲያን አይደለም። ከዚህ አሠራር ውጭ የሚፈጸሙ ድርጊቶች በሙሉ በኃላፊነት ያስጠይቃሉ።
የባለአደራው የአስተዳደር ቦርድ ሥራውን ከላይ እንደተገለጸው በአግባቡ በመሥራት ላይ ይገኛል? ወይስ በግድ የለሽነት እየዳኸ ነው?
ይቀጥላል።
የቤተክርስቲያናችን አመሠራረትና አወቃቀር ለሚለው ጽሁፍ ተከታይ ሆኖ የቀረበ።

ቤተክርስቲያናችንን
ከቀበሌ የፍርድ ሸንጎ ወደ ተቀደሰ ደብር ለመለወጥ የተደረገ ጉዞ፡

ቀደም ሲል የዳላስ እና አካባቢው ምእመናን በአንድ ደብር ጥላ ሥር ተሰባስቦ ያመልክ ስለነበር የአባላት ቁጥር ከፍተኛ ነበር። ከአባላቱ የሚሰበሰበውም ብር ጠርቀም ያለ ነበር። ብር አዋጡ ተብለው ሲጠየቁ በኪሳቸው ውስጥ ያለውን እርግፍ አድርገው ሲሰጡ አይተናል። የዓይን ምስክሮችም ነን። የዚህ ደብር ምዕመናን ለአብነት የሚጠቀሱ ብዙ አኩሪ ሥራዎችን ሰርተዋል። ወርቃማ ታሪክ ያለው ትልቅ ደብር ነው። ዛሬ ግን ይህ ሁሉ ተረስቶ ቤተክርስቲያናችን በውጭና በውስጥ በክስ ተወጥራ ትገኛለች። ምዕመናን ተሰብስበው የሚያመልኩበት ሥፍራ መሆኑ ቀርቶ የቀበሌ የፍርድ ሸንጎ ካስመሰልነው ብዙ ዓመታት አስቆጥረናል። ያለው ችግር ተባብሶ እንዴት እዚህ ደረጃ ሊደረስ ቻለ?
በአጭር ጊዜ ውስጥ ተሰባስበን ከተጠበቀው በላይ አድገን ብዙ በጎ ሥራዎች እና ዕርዳታዎችን በሰፊው ሰጠን። ይህንን ፈጣን እድገት ከዳር ሆኖ ይመለከት የነበረው ወያኔ ሁለት ዕቅዶችን አውጥቶ ዘመተብን።
ዕቅድ አንድ ፤ ደብሩን በራሱ ቁጥጥር ሥር ማዋል።
ዕቅድ ሁለት ፤ ይህ ካልተሳካ ምዕመኑን መበተን እና ሀይሉን መስበር ናቸው።
እነዚህን ዕቅዶች ተግባራዊ ለማድረግ የዛሬ ስድስት ዓመት በተደረገው የቦርድ ምርጫ አባ ጳውሎስ እና ወያኔ በማህበረ ቅዱሳን አማካኝነት የቦርድ አባላትን አስመረጡ። ለረጅም ዘመን ምዕመናኑ ለልጆቻችን አስተማሪ ይቀጠርልን ብሎ ያቀረበውን ጥያቄ የተቀበ በማስመሰል በወቅቱ የነበረው ቦርድ የማህበረ ቅዱሳን መሪ የሆነውን ግለሰብ የቅዱስ ያሬድ ት/ቤት ኮኦርዲኔተር ብሎ ከቀጠረ በህዋላ ሕዝቡ ሳያውቅ በስውር “የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ” የሚል ሹመት ሰጡት።
በወቅቱ የነበሩት ርዕሰ ደብር ሞገስ እጅጉ እና መምህር ሰብስቤ ውሳኔው የነርሱን የሹመት ተዋረድ የሚጋፋ መሆኑን ሲረዱ ማህበረ ቅዱሳንን የሚቃውሙ መዘምራንን እና ምዕመናንን አሰባስበው መቅደስ ላይ በፈጠሩት እውከት ደብራችን ለሁለት ተከፈለ። ውስጥ ውስጡን በቀሳውስቱ፣ በማህበረ ቅዱሳን እና በተመራጭ የቦርድ አባላት መካከል ታምቆ የቆየው ቅራኔ ጊዜውን ጠብቆ ፈነዳ። ቤተክርስቲያናችን ችግር ላይ መውደቅዋም ይፋ ወጣ።
ርዕሰ ደብር በስማቸው ቀደም ብለው የቤተክርስቲያን ፍቃድ አውጥተው ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ስንረዳ ምዕመናን አዘንን፣ ተቆጣን። ከመቶ ሰላሳ በላይ የምንሆን ምዕመናን ተሰብስበን ድርጊታቸውን አወገዝን፣ የመረጥነውንም ቦርድ መደገፍ እንዳለብን ተስማማን፤ በውስጣቸው አለመግባባትና ችግር ካለ ጉዳዩ በሥነ ሥርዓት መታየት አለበት እንጂ መቅደስ ላይ ሁከትን መፍጠር መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል ገልፀን ለቦርዱ የድጋፍ ደብዳቤ አስገባን። ሌቦች ናችሁ፣ የቤተክርስቲያን ብር አባክናችሁአል፤ ከሥልጣን መውረድ አለባችሁ ተበለው ማጣፊያው አጥሮአቸው የነበሩትን የውቅቱን የቦርድ አባላት አረጋግተን ሥራቸውን እንዲቀጥሉ አደረግን።
ቦርድና ማህበረ ቅዱሳን ብር እያባከኑ ነው ብለው የተቃወሙ ወገኖች ራሳቸውን ከርዕሰ ደብር ለይተው ጥያቄአቸውን ማስረዳት ስለተሳናቸው ከቤተክርስቲያን ሲወጡ፤ በወቅቱ ውስጥ ለውስጥ ታምቆ የነበረውን ችግር በቅጡ ያልተረዳነው ወገኖች ቦርዱን አጠናክረን ከማህበረ ቅዱሳን ጋር ቤተክርስቲያን ቀረን።
ማህበረ ቅዱሳንም መድረኩን ተቆጣጥሮ ብቻውን በግላጭ መጋለብ ያዘ። የበጎ አድራጎትን ገንዘብ እንዳለ ተቆጣጠረ። ለድርጅቱ ፕሮጄክቶች ሥራ ማስፈጸሚያ ብር እንደፈለገ ያወጣ ጀመር፤ ታዋቂ መምህሮቻቸውን በየሦስት ወሩ ጉባኤ በሚል ሽፋን ወደ ዳላስ ማጉረፍ ጀመሩ። Video እና CD ቀርጸው ለአለም ማሰራጨት ጀመሩ። ለጉባኤ ከአዲስ አበባ ድረስ መምህራኖቻቸውን ማስመጣትን ሥራዬ ብለው ተያያዙ። ይህ ሁሉ የሚሠራው በደብራችን ገንዘብ ነበር።
ከዚህም በተጨማሪ በዚያኑ ሰሞን ባስቀጠሩአቸው ካህናቸው በኩል ያለቁርባን ጋብቻ እንደማይፈፀም አወጁ፤ ቀደም ብለን የተጋባነውንም ምዕመናን ዝሙተኞች መሆናችንን ማስተማር በሰፊው ተያያዙ። ይህንን ለመቕቕም ስንንቀሳቀስ ከማህበረ ቅዱሳን ጋር ግጭት ተፈጠረ። ይህንን አክራሪ ጥያቄያቸውንም እንዲያነሱ ተወሰነ። በሌላ በኩል የቤተክርስቲያን ሕግ ማሻሻያ (Amendment) አጥንታችሁ አቅርቡ ተብለው የተመረጡ ወገኖች፤ ሕጉን እንዳለ ለውጠው አዲስ ሕግ ይዘው ብቅ አሉ። ከነሱም ጋር ፍጥጫው ቀጠለ። ተንኮላቸውም ተኮላሸ።
የቦርድ አባላት ምርጫ ጊዜው ደርሶ ሲካሄድ፣ በማህበረ ቅዱሳን ቁጥጥር ሥር የነበረውን ቦርድ መለወጥ እንዳለብን አምነን ተነሳን።፡በተለይ ሁለተኛው ዙር የቦርድ ምርጫ ከተደረገ በሁአላ ማህበረ ቅዱሳን አድማ መምታትን ተቀዳሚ ሥራቸው አደረጉት። የቤተክርስቲያኑን ንዑሳን ኮሚቴዎች እኛ ካልተቆጣጠርን ለማንም አሳልፈን አንሰጥም አሉ። የደረሱበት፣ ያዩት፣ የነኩት በሙሉ የራሳቸው ይመስላቸዋል። በየቦታው ችግር መፍጠርን ሥራዬ ብለው ተያያዙ። የሥም ማጥፋት ዘመቻ፣ ሐሜት፣ ውሸት፣ ነገር ፈጥሮ ማውራት፣ ማስወራት የተካኑበት እንዲያውም እነርሱ የፈጠሩት እስከሚመስል ድረስ ተራቀውበት ለማየት ችለናል።
በወጣቶችና፣ በልጆች ፕሮግራም ውስጥ ማህበረ ቅዱሳን ካልሆነ ማንም ሊሳተፍ አይችልም በማለት ሽብር መንዛት ሥራዬ ብለው ተያያዙ። እሁድ አልፎ እሁድ ሲተካ ያለማቁአረጥ ረብሻቸውን አጥዋጥዋፉ። በአጠቃላይ ለቤተክርስቲያን ጉድይ ሳይሆን ጠባብ ለሆነው ለማህበራቸው ዓላማ መቆማቸውን እና ያላቸውን የዓላማ ፅናት በግልጥ በእውነት አየነው። ሆኖም ሥራቸውን እንደስማቸው ሙሉ ለሙሉ መንፈሳዊ ሆኖ አላገኘነውም። ይልቅስ በወጣትነታችን የምናውቀውን የፖለቲካ ድርጅት አስታወሱን።
ውድ ምዕመናን፤ ጠላቶቻችን ሊቆጣጠሩን፣ ካልሆነም ሊያፈርሱን እና ሊበታትኑን ያደረጉትን ሙከራ ከሞላ ጎደል ለመመልከት ችለናል። ለዚህ ሴራ በሩን ክፍት አድርገን ስለሰጠናቸው በዚያ ገብተው የሚፈልጉትን እየሠሩ ነው። ክፍት ሆኖ ያለው የጥፋት በርም የቤተክርስቲያኑ ልቅ የሆነና ቁጥጥር የሌለው የአስተዳደር ሥርዓት ነው። ላለፉት አሥራ ስምንት ዓመታት የተጠቀምንበት የአስተዳድር ስርአት ቤተክርስቲያናችን ልትወጣው የማትችለው አዙሪት ውስጥ ጨምሮአታል። በተሰበረና በማይሠራ ሥርዓት መልሰን ለመገልገል የሚደረገው ዕርምጃ መልሶ መላልሶ ስህተት ውስጥ ይጥለናል እንጂ አንድ እርምጃ ወደፊት አይወስደንም።
እኛ የኦርቶዶክስ አማኞች የምናውቀው ሚስጥረ ቤተክርስቲያን ሰባት ነው። የደብራችን ቦርድ ግን ስምንት ሚስጥራት አሉት። ሰባቱን ሚስጥራት አባቶች አስተምረውን አበጥረን እናውቃቸዋለን። ቦርዱ የፈጠረውን ተጨማሪ ሚስጥር ግን ምዕመናን አያውቁትም። ስምንተኝው ሚስጥር የቦርዱ አባላት ተመርጠው ሥራቸውን ሲጀምሩ መቅደስ ላይ በአባቶች ተባርከው ፀሎት ተደርጎላቸው ይሰናበታሉ። ከዚያ በሁአላ ጽሕፈት ቤት ውስጥ በር ዘግተው መጽሐፍ ቅዱስ ጨብጠው የሚሠሩትን ሥራ፤ የሚወስኑትን ማንኛውንም ውሳኔ፤ ሠራተኛ እንዴት እንደሚቀጥሩ፤ የቤተክርስቲያን ጥገናም ሆነ የተለያዩ ወጭዎችን በተመለከተ እርስ በራሳቸው ካልሆነ በስተቀር ለማንም እንዳይነግሩ ይማማላሉ።
እንግዲህ ቦርዱ ተጠሪነቱ ለመረጠው ሕዝብ መሆኑ ቀርቶ ተጠሪነታቸውን እርስ በራሳቸው አደረጉት። አሠራሩ በዚህ ዓይነት ለዘመናት የተዋቀረ ስለሆነ ደብራችን ዛሬ ያለችበት አስከፊ ችግር ውስጥ ልትወድቅ ችላለች።
በዚህ ምክንያት ይህን የመሳሰሉትን አስተዳደራዊ ችግሮችን ብንፈታ ዘላቂ ሠላምና መተማመን ይመጣል ብለን አሰብን። ግልፅ አሠራርን በቤተክርስቲያናችን ውስጥ መለማመድ አለብን ብለን ቆርጠን ተነሳን። በቅድሚያ መለወጥ ያለበት የሂሳብ አያያዝ ነው ብለን ወሰንን። ምክንያቱም ሕዝቡ ገንዘብ እንደሚባክን በይፋ መናገር ከጀመረ ቆይቶአል። የቀድሞ የቦርድ ተመራጮችን ሌቦች! ሌቦች! እያለ ያወገዘው በአደባባይ ነበር። እኛም ማህበረ ቅዱሳን የቤተክርስቲያኑን ገንዘብ ያለአግባብ ከተጠቀመባቸው መረጃዎች መካከል ጥቂቶቹን ለማየት ችለናል። ሂሳባቸውን ያላወራረዱ የቀድሞ የቦርድ አባላትን ሁሉ እናውቃለን። በ2006 ዓ/ም ቤተክርስቲያኑ ከ1.2 ሚሊዮን እስከ 1.5 ሚሊዮን ብር እንደነበረው በሰማንበት ጆሮአችን 2007 ወይም 2008 ላይ ያለው ብር አሽቆልቁሎ ስምንት መቶ ሺህ ብቻ እንደተቆጠረም ተነግሮናል። በምዋቹ በአቡነ ይስሐቅ ሥም በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ውስጥ የነበረውም $450 ሺህ ብር በፍጥነት እንደተነነ ሰምተናል።
እነዚህን ሀቆች በመንተራስ አዲሱ የሂሳብ አሠራር ዘዴ ለቦርድ አባላት ቀረበ። የቀረበለትን አዲስ አሠራር መርምሮ በሥራ ላይ እንዲውል ከማድረግ ፈንታ የአስተዳደር ቦርዱ ይህንን ሀሳብ በጥንስሱ ማኮላሸት ፈለገ። ቀደም ሲል ከገንዘብ ጋር ንክኪ የነበራቸውን ሰዎች ሰብስበው የጋራ ግንባር ፈጠሩ። ይህን ሃሣብ ባቀረቡና ሃሣቡን በደገፉ የቦርድ አባላት ላይ የሥም ማጥፋት ዘመቻ አፋፋሙ። ሥማቸውን እየጠቀሱ በደረሱበት ቦታ ሁሉ የተመረጥንበትን ሥራ አላሠራ አሉን ብለው ማውራት ጀመሩ። ለስብሰባ ሲጠሩ አንመጣም እያሉ ያስቸግሩናል በማለት የሀሰት ወሬ መንዛት የዕለት ተዕለት ተግባራቸው ሆነ።
ቤተክርስቲያናችን ግልፅ የሆነ አስተዳደራዊ ሥርዓት መከተል አለባት ብለን የተነሳነውን ምዕመናን የደብራችን እንቅፋትና ችግር ፈጣሪዎች ናቸው፤ ምዕመናኑን እየበጠበጡት ነው፤ መመከር አለባቸው፤ ደብሩን ችግር ላይ ጥለውታል፤ ቤተክርስቲያናችን ውድቀት ላይ ያለችው በእነዚህ ግለሰቦች እና በከሳሾች ምክንያት ነው ብለው አወሩ። መፍትሔውም ሰላምና እርቅ የሚያመጣ ኮሚቴ መፍጠር ነው ብለው ተነስተዋል። እንግዲህ ፍርዱን ለአምላክና ለእናንተ ለምዕመናን እንተወዋለን። የቤተክርስቲያናችን የበላይ አካል አባላት ምዕመናን ናቸው። ቦርዱም ሥራውን ሪፖርት ማድረግ ያለበት ለምዕመናኑ ነው። የምዕመናኑንም ውሳኔ በሥራ ላይ ማዋል የቦርዱ ግዴታ ነው።
እሩቅ ሳንሄድ በዚህ በያዝነው ዓመት መጀመሪያ ላይ በተደረገው አጠቃላይ ጉባኤ የተላለፉት ውሳኔዎች ተፈጻሚነት አገኙ ወይ? ችግሩን የተለያየ ምክንያት በመፍጠር፤ ለምሳሌ፤ ፍርድ ቤት ስለተከሰስን ጌዜ ስጡን፤ ባይሎው እስከሚስተካከል ታገሱን በማለት የተመረጡበትን ሥራ በማግዋተትና የተወሰኑ ውሳኔዎችን እንክዋን በተግባር እንዳይተረጎሙና በስራ ላይ እንዳይውሉ አድርገዋል። ይህ ድርጊት ቤተክርስቲያኑን ከከሱት ግለሰቦች ይበልጥ እንደሆነ እንጂ አያንስም። ሕዝቡን ደግሞ ደጋግሞ ማሞኘት አይቻልም።
ውድ ምእመናን ስለ ግልጽ አሠራር (TRANSPARENCY) ለቦርዱ ያቀረብነው ጽሁፍ ከዚህ በፊት በድህረ ገጻችን ላይ ስላወጣን እንዳነበቡት ተስፋ እናደርጋለን። ካላነበቡትም “ጁን 16, 2009 ዓ/ም ስለመተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ሃሳብ” ተብሎ የተጻፈውን ያንብቡ።

Saturday, August 22, 2009

አንደምን አደራቸሁ፣
ዛሬ ደግሞ ተኩላዎች የበግ ለምድ ለብሰዉ በመካከላችን ገብተው እንዲበጠብጡን አሁን ያለዉ
ቦርድ መልምሎ የቀጠረልን ቀሳዉስትና ዘማሪዎች በዋሸንግተን ዲሲ ያደረጉትን ስብሰባ ይመለከቱ ዘንድ ይህን ሊንክ ይክፈቱ.
እንደፈረንጅ አቆጣጠር ባዲሱ አመት መጀመርያ አጠቅላይ ጉባኣ
ላይ ስለ ማህበረ ቅዱሳን ያለፈዉን ዉሳኔ ቦርዱ በቦርዱ ዋና አላፊና ቦርዱ ዉስጥ
ባሉት ደጋፊዎቻቸው ተግባር ላይ እንዳይዉል እየተከላከሉ መሆናቸዉን ይረዱ።
ተግባር ላይ አንዲያዉሉ መጠየቅና ማስገደድ የያንዳንዱ አባላት መብት መሆኑን
አትዘንጉ።
ቦርዱ ባጭር ጊዜ ዉስጥ ይህን ጥያቄ ካላምዋላልን ኮቦርዱ ዉስጥ ማን ማን መሆናቸዉንና
ለምን የሚለዉን ጥያቄ ዘርዝረን እናቀርባለን።


http://www.mahiberekidusan.org/documents/MK%2011%20Tekelala%20Gubae/album/index.html

እንደተለመደው ኮፒ እና ፐስት አድርጉ.

Friday, August 21, 2009

ቤተክርስቲያናችንን የከሰሰው ቡድን ኦገስት 23 ቀን 2009 ዓ.ም. አባላቱ $20.00 ዶላር ስጦታ በመያዝ ተሰብስበው ስለክሱ ሪፖርት እንዲሰሙ ጋበዘ።
በሌላ በኩል ይህ ቡድን ኦገስት 19 ቀን 2009 ዓ.ም. በመልዕክተኞቹ በኩል ለቦርዱ ያቀረበው ቅድመ ዝግጅት ተቀባይነትን ካገኘ ቤተክርስቲያኑ ክሱን ለመከላከል ሲል ያወጣውን ወጭ ካሣ እንደሚከፍል ማሳወቁ ይታወሳል። እዚህ ላይ የራሳቸው ኪሣራ ሲታከልበት ወጭ የሚያደርጉት ገንዘብ ከፍተኛ እንደሚሆን ይጠበቃል። ሆኖም እኛ ቀደም ሲል የሰማነው ዜና ማህበረ ቅዱሳን እና ወያኔ ወጭያቸውን እንደሚሸፍኑ ነው። ይህ ሁሉ ብር እያለ $20.00 በስጦታ መልክ መሰበሰብን ምን አመጣው?
አብዛኛዎቹ ከሳሾች በተለያየ ወቅት የቦርድ አባል በመሆን ብር ያባከኑ እና ከማህበረ ቅዱሳን ጋር በማበር በበጎ አድራጎት ኮሚቴ ሥም ገንዘብ ሲዘርፉ የነበሩ ናቸው። ዛሬ ደግሞ ለየት ባለ መልክ አዲስ ዘዴ ቀይሰው ብቅ ብለዋል። ለእድምተኞቹ የእኛ ምክር ራሳችሁን ጠብቁ ነው። በከፋ ዘመን ዋለታችሁ ውስጥ ሊገቡ ነው የሚል ነው።
ከእናንተ አንዱ ክርስቲያን ከሆነው ወንድሙ ጋር ቢጣላ፣ ጉዳዩን የእግዚአብሔር ሰዎች በፍርድ እንዲያዩለት በማድረግ ፈንታ ለክስ ወደ አረማውያን የፍርድ ሸንጎ ለመሄድ እንዴት ይደፍራል? 1ኛ ቆሮ፡ 6፡1
ታዲያ አንድ ክርስቲያን ሌላውን ክርስቲያን ከሶ ወደ አረማውያን ፍርድ ቤት መውሰድ ይገባዋልን? 1ኛ ቆሮ፡ 6፡6
እውነትን በይፋ እናሳያለን

ኦገስት 18 ቀን 2009 ዓ.ም. ባቀረብነው ሪፖርት ላይ ከዘረዘርናቸው ሥሞች መሐከል አቶ በትሩ ገብረእግዚአብሔር በምሽቱ ስብሰባ ላይ አለመገኘታቸውን ሪፖርቱን ያነበቡ ምዕመናን ገልፀዋል። እኛም አቶ በትሩ ገብረእግዚአብሔርን ስለፈጸምነው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን።
የአባ ጳውሎስ መልዕክተኛ ቡድን ኦገስት 19 ቀን 2009 ዓ.ም. ምሽት ላይ በድጋሚ ከቦርዱ ጋር ተሰብስቦ ነበር። በስብሰባው ላይ የተካፈሉ ቡድኖች፤
1፣ ከአዲስ አበባ የተላኩ ቆሞስ፤
2፣ ከአባ ጳውሎስ እና ከማህበረ ቅዱሳን ጋር በቅርብ የሚሠሩ ግለሰቦች፤
3፡ ስለቤተክርስቲያኑ ችግር የተሙዋላ መረጃ ሳይዙ የራሳቸውን የተደበቀ ዓላማ ለማስፈጸም ሽምግልና ውስጥ የገቡ ግለሰቦች ናቸው።
እነዚህ የአባ ጳውሎስ መልዕክተኞች ቦርዱ ቤተክርስቲያኑን የከሰሱ ሰዎች ክሳቸውን እንዲያነሱ ከፈለገ በቅድሚያ መፈጸም አለባቸው ብለው ያቀረቡትን ቅድመ ሁኔታ አስረድተዋል። ይኸውም ኤፕሪል ላይ የተሻሻለው (amended የሆነው) የቤተክርስቲያን ሕግ ተሽሮ የቀድሞው ሕግ እንዳለ በሥራ ላይ እንዲውል ነው።
ቦርዱ የቀድሞውን ሕግ መልሶ ሥራ ላይ ሲያውል ከሳሾችም ክሳቸውን እንደሚያነሱና ቤተክርስቲያኒቱ በዚህ ክስ ሳቢያ ያወጣችውን ወጭ ካሣ እንደሚከፍሉ የሚል ነበር።
ውድ አንባቢያን፤ ከዚህ ስብሰባ ላይ ይፋ ሆኖ የወጣ ነገር ቢኖር ቦርዱ ውስጥ ውስጡን ከአባ ጳውሎስ እና ከማህበረ ቅዱሳን ጋር እንደቀድሞው ተመልሶ ለመሥራት ደጅ ሲጠና መክረሙ ነው። ለዚህም ነው ከሳሾች እንድንመለስ ከፈለጋችሁ ሕጉን ወደ ቀድሞው ሥፍራ መልሱት ብለው መልዕክት የላኩባቸው።
ጃንዋሪ 2009 ዓ.ም. በተደረገው አጠቃላይ ስብሰባ ላይ ቤተክርስቲያናችን ገለልተኛ መሆኑዋ፣ ከማህበረ ቅዱሳንም ጋር እንደማንሠራ መወሰኑ አይዘነጋም።
ይህ የምዕመናን ውሳኔ ተግባራዊ ያልሆነበት ምክንያት አሁን ግልፅ እየሆነ ነው። ከቤተክርስቲያኑዋ አቁዋም ጋር ተፃራሪ የሆኑ ቀሳውስትን አቅፈው ደግፈው የምዕመኑን ቆሽት ማሣረር የዕለት ተዕለት ተግባራቸው ለምን እንዳደረጉት ልንገነዘብ ችለናል። የማህበረ ቅዱሳንን መምህራን እያስመጡ ማስተናገድ የጀመሩበት ምስጢር በዚህ ስብሰባ ምክንያት ግልፅ ሆኖ ወጥቶዋል።
እየመጣ ካለው አደጋ አምላክ ይጠብቀን።
ከከሀዲዎች ፍላፃ አምላክ ይታደገን

Thursday, August 20, 2009

በሰላም አሳድሮ በሰላም ያዋለንን አምላክ እያመሰገንን ለዛሬ ደግሞ
ይሀንን ሊንክ አናቀርባለን.

http://ethiomedia.com/adroit/yezare_sinodos.pdf

በደህና ያሳድረን.


አንደተለመደው ኮፕ አና ፐስት ያድርጉት

Wednesday, August 19, 2009

ለዛረ የሚከተለዉን (ሊንክ) ይክፈቱና ይመልከቱ.

http://ethiomedia.com/adroit/qumsina.pdf

ሊንኩን ለመክፈት ኮፒ ያድርጉና ብራዉዘሩ ላይ ፐስት ያድርጉ.

በሚቀጥለዉ ጊዘ እስንገናኝ

አምላክ ይጠብቀን

Tuesday, August 18, 2009

የሚቀጥለውን አድራሻ ይመልከቱ.


http://www.mahiberekidusan.org/Default.aspx?tabid=36&ctl=Details&mid=371&ItemID=236
ስአሉን ይጫኑ.

http://www.youtube.com/watch?v=SIDZpjwKTTk
እውነትን በይፋ እናሳያለን!!

ዘግይቶ የደረሰን ዜና

ሰሞኑን በአባ ጳውሎስ ደጋፊዎች ሰላምና እርቅ እየተባለ ሲቦካ የነበረው ሴራ ግቡን ይመታ ዘንድ ከአቡነ ጳውሎስ የተላኩት ልዩ መልእክተኛ እና የማህበረ ቅዱሳን በጅሮንድ ባለፈው እሁድ ሰንበት በቤተክርስቲያናችን በመገኘት ስለሰላምና እርቅ ሲሰብኩ መደመጣቸው ይታወሳል። እኚህ ደፋር መልእክተኛ ምእመናኑን ከቅዳሴ በሁዋላ ከቤተክርስቲያን እንዳይውጣ አዘው ካህናቱን እና ከሳሾችን አስክትለው ወደቦርድ ጽህፈት ቤት በመሄድ የቦርድ አባላትን ማነጋገራቸው እና ጉዳያቸውም ፈር እንደያዘ ለምእመናኑ ማሳወቃቸው አይዘነጋም። ይህ ድፍረታቸው ሲደንቀን ዛሬ ኦገስት 18 ቀን 2009 ዓ/ም ምሽት ላይ የቤተክርስቲያናችንን ከሳሾችና ግለስቦችን እንዲሁም የቦርዱን ሊቀመንበር ጨምረው በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ሲዶልቱ አምሽተዋል።
ዋናው ጥያቄ የቦርዱ ሊቀመንበር የቦርድ አባላት ሳያውቁና ሳይፈቅዱ እኝህ አባት የማህበረ ቅዱሳን አባል እና የአባ ጳውሎስ ቆሞስ መሆናቸውን እያወቀ በተደጋጋሚ በቤተክርስቲያናችን ውስጥ እንደፈለጉ ገንዘብ እንዲሰበስቡ፤ ስብሰባ እንዲያካሄዱ እና ከከሳሾች ጋር አብረው እንዲዶልቱ የተባበረበትን ምክንያት ለሕዝቡ በአስቸክዋይ እንዲገልጽ እይጠየቅን በተጨማሪም በምንኖርበት ሀገር ሕግ መሠረት የተመስረተው ክስ ብያኔ ሳያገኝ፤ እንዲሁም ከሳሽ በተከሳሽ ቦታ ላይ መገኘት እንደማይገባው የሚያዘውን ሕግ ማስከበር (restraining order) ሲገባው በጎን ተደብቆ ከከሳሽ ጋር አብሮ መዶለት ለምን አስፈለገው? ይህ አድራጎቱ የግለስቡን ህቡዕ የተዛባና አወዛጋቢ አቅዋም ይፋ አውጥቶ እርቃኑን አስቀርቶታል።
በዚህ ስብስባ ላይ የተገኙ ግለሶቦች፤
1. ንቡረእድ (የአባ ጳውሎስ ቆሞስ)
2. አቶ ጌታቸው ወልደሚካኤል
3. አቶ በቀለ ተክሌ
4. አቶ መስፍን ወልደየስ
5. አቶ ኪዳኔ አለማየሁ (በቅርፍቡ የፍሎሪዳን ቤተክርስቲያን የበተኑ የአባ ጳውሎስ
ቀኝ እጅና የዳያስፖራ ቤተክርስቲያናት ብተና መሪ)
6. አቶ በትሩ ገብረእግዚአብሔር
7. ወ/ሮ ጥሩ አየር ፍስሀ
8. አቶ ኢዩኤል ነጋ እና ሌሎችም ግለሰቦች ይገኙበታል።