Wednesday, August 26, 2009

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ርዕሰ አድባራት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አመሰራረቱ እና የአስተዳደር መዋቅሩ እንደሚከተለው ነው።

የዚህ ደብር ባለቤትና ዋና አካል የሆኑት የአባልነት ግዴታቸውን ያምዋሉ ምእመናን ሲሆኑ የእለት ተእለት አስተዳድራዊ ሥራዎች ደግሞ በመእምናኑ በተመረጡ ዘጠኝ የቦርድ አባላት ይከናወናሉ። እነዚህም ዘጠኝ የቦርድ አባላት ተጠሪነታቸው ለአባላቱ ነው።

ተጠሪነታቸው ለአስተዳደር ቦርድ የሆኑ የተለያዩ ንኡሳን ኮሚቴዎች በቦርዱ አማካኝነት ይቅዋቅዋማሉ፤ በቦርዱ አማካኝነትም ሊታጠፉ ይችላሉ።
የቦርድ አባላቱ የትመረጡበትን ኃላፊነት ለመወጣት በየአመቱ በፈረቃ እርስ በራሳቸው ተመራርጠውና የሥራ ድርሻ ተከፋፍለው ይሰራሉ።

ምሳሌ፡

ሊቀመንበር
ም/ሊቀመንበር
ዋና፡ ጸሐፊ
የሂሳብ ሹም
ገንዘብ ያዥ……ወዘተርፈ

በዚህ አይነት የሥራ ድልድል ካደረጉ በህዋላ የአስተዳደር ቦርድ አባላት እንደ አንድ ኮሚቴ በመሆን በአምላክና በምእመናን ፊት ቀርበው የገቡትን ቃል ኪዳን ለመፈጸም ይጥራሉ።

ሊቀመንበር ሆኖ የሚመረጠው ግለሰብ በቦርድና በአባላቱ የተላለፉትን ውሳኔዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን እየተከታተለ ማስፈጸም ካልሆነ በስተቀር የፍጹማዊ አምባገነንነት ስልጣን የለውም። የአስተዳደር ቦርዱ አባላት ያላቸውን ሃሳብ በአጀንድ አስይዘው በቦርዱ ጉባኤ ላይ አቅርበው ተቀባይነትን ካገኘ ሃሳባቸው በሥራ የሚተረጎምበትን መንገድ ቦርዱ በህብረት ይፈልጋል። ካልሆነም ሃሳቡ ውድቅ ይሆናል።

ይህ ደብር ማንም የቦርድ አባል ከቦርድ ጉባኤ እና ከአባላት ምእመናን ጉባኤ ውሳኔ ውጭ የራሱን ሃሳብ እና ምኞት የሚያንጸባርቅበትና በሥራ ላይ ለማዋል ጫና የሚያደርግበት ቤተክርስቲያን አይደለም። ከዚህ አሠራር ውጭ የሚፈጸሙ ድርጊቶች በሙሉ በኃላፊነት ያስጠይቃሉ።
የባለአደራው የአስተዳደር ቦርድ ሥራውን ከላይ እንደተገለጸው በአግባቡ በመሥራት ላይ ይገኛል? ወይስ በግድ የለሽነት እየዳኸ ነው?
ይቀጥላል።

No comments:

Post a Comment