Friday, August 21, 2009

ቤተክርስቲያናችንን የከሰሰው ቡድን ኦገስት 23 ቀን 2009 ዓ.ም. አባላቱ $20.00 ዶላር ስጦታ በመያዝ ተሰብስበው ስለክሱ ሪፖርት እንዲሰሙ ጋበዘ።
በሌላ በኩል ይህ ቡድን ኦገስት 19 ቀን 2009 ዓ.ም. በመልዕክተኞቹ በኩል ለቦርዱ ያቀረበው ቅድመ ዝግጅት ተቀባይነትን ካገኘ ቤተክርስቲያኑ ክሱን ለመከላከል ሲል ያወጣውን ወጭ ካሣ እንደሚከፍል ማሳወቁ ይታወሳል። እዚህ ላይ የራሳቸው ኪሣራ ሲታከልበት ወጭ የሚያደርጉት ገንዘብ ከፍተኛ እንደሚሆን ይጠበቃል። ሆኖም እኛ ቀደም ሲል የሰማነው ዜና ማህበረ ቅዱሳን እና ወያኔ ወጭያቸውን እንደሚሸፍኑ ነው። ይህ ሁሉ ብር እያለ $20.00 በስጦታ መልክ መሰበሰብን ምን አመጣው?
አብዛኛዎቹ ከሳሾች በተለያየ ወቅት የቦርድ አባል በመሆን ብር ያባከኑ እና ከማህበረ ቅዱሳን ጋር በማበር በበጎ አድራጎት ኮሚቴ ሥም ገንዘብ ሲዘርፉ የነበሩ ናቸው። ዛሬ ደግሞ ለየት ባለ መልክ አዲስ ዘዴ ቀይሰው ብቅ ብለዋል። ለእድምተኞቹ የእኛ ምክር ራሳችሁን ጠብቁ ነው። በከፋ ዘመን ዋለታችሁ ውስጥ ሊገቡ ነው የሚል ነው።
ከእናንተ አንዱ ክርስቲያን ከሆነው ወንድሙ ጋር ቢጣላ፣ ጉዳዩን የእግዚአብሔር ሰዎች በፍርድ እንዲያዩለት በማድረግ ፈንታ ለክስ ወደ አረማውያን የፍርድ ሸንጎ ለመሄድ እንዴት ይደፍራል? 1ኛ ቆሮ፡ 6፡1
ታዲያ አንድ ክርስቲያን ሌላውን ክርስቲያን ከሶ ወደ አረማውያን ፍርድ ቤት መውሰድ ይገባዋልን? 1ኛ ቆሮ፡ 6፡6

No comments:

Post a Comment