Friday, August 21, 2009

እውነትን በይፋ እናሳያለን

ኦገስት 18 ቀን 2009 ዓ.ም. ባቀረብነው ሪፖርት ላይ ከዘረዘርናቸው ሥሞች መሐከል አቶ በትሩ ገብረእግዚአብሔር በምሽቱ ስብሰባ ላይ አለመገኘታቸውን ሪፖርቱን ያነበቡ ምዕመናን ገልፀዋል። እኛም አቶ በትሩ ገብረእግዚአብሔርን ስለፈጸምነው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን።
የአባ ጳውሎስ መልዕክተኛ ቡድን ኦገስት 19 ቀን 2009 ዓ.ም. ምሽት ላይ በድጋሚ ከቦርዱ ጋር ተሰብስቦ ነበር። በስብሰባው ላይ የተካፈሉ ቡድኖች፤
1፣ ከአዲስ አበባ የተላኩ ቆሞስ፤
2፣ ከአባ ጳውሎስ እና ከማህበረ ቅዱሳን ጋር በቅርብ የሚሠሩ ግለሰቦች፤
3፡ ስለቤተክርስቲያኑ ችግር የተሙዋላ መረጃ ሳይዙ የራሳቸውን የተደበቀ ዓላማ ለማስፈጸም ሽምግልና ውስጥ የገቡ ግለሰቦች ናቸው።
እነዚህ የአባ ጳውሎስ መልዕክተኞች ቦርዱ ቤተክርስቲያኑን የከሰሱ ሰዎች ክሳቸውን እንዲያነሱ ከፈለገ በቅድሚያ መፈጸም አለባቸው ብለው ያቀረቡትን ቅድመ ሁኔታ አስረድተዋል። ይኸውም ኤፕሪል ላይ የተሻሻለው (amended የሆነው) የቤተክርስቲያን ሕግ ተሽሮ የቀድሞው ሕግ እንዳለ በሥራ ላይ እንዲውል ነው።
ቦርዱ የቀድሞውን ሕግ መልሶ ሥራ ላይ ሲያውል ከሳሾችም ክሳቸውን እንደሚያነሱና ቤተክርስቲያኒቱ በዚህ ክስ ሳቢያ ያወጣችውን ወጭ ካሣ እንደሚከፍሉ የሚል ነበር።
ውድ አንባቢያን፤ ከዚህ ስብሰባ ላይ ይፋ ሆኖ የወጣ ነገር ቢኖር ቦርዱ ውስጥ ውስጡን ከአባ ጳውሎስ እና ከማህበረ ቅዱሳን ጋር እንደቀድሞው ተመልሶ ለመሥራት ደጅ ሲጠና መክረሙ ነው። ለዚህም ነው ከሳሾች እንድንመለስ ከፈለጋችሁ ሕጉን ወደ ቀድሞው ሥፍራ መልሱት ብለው መልዕክት የላኩባቸው።
ጃንዋሪ 2009 ዓ.ም. በተደረገው አጠቃላይ ስብሰባ ላይ ቤተክርስቲያናችን ገለልተኛ መሆኑዋ፣ ከማህበረ ቅዱሳንም ጋር እንደማንሠራ መወሰኑ አይዘነጋም።
ይህ የምዕመናን ውሳኔ ተግባራዊ ያልሆነበት ምክንያት አሁን ግልፅ እየሆነ ነው። ከቤተክርስቲያኑዋ አቁዋም ጋር ተፃራሪ የሆኑ ቀሳውስትን አቅፈው ደግፈው የምዕመኑን ቆሽት ማሣረር የዕለት ተዕለት ተግባራቸው ለምን እንዳደረጉት ልንገነዘብ ችለናል። የማህበረ ቅዱሳንን መምህራን እያስመጡ ማስተናገድ የጀመሩበት ምስጢር በዚህ ስብሰባ ምክንያት ግልፅ ሆኖ ወጥቶዋል።
እየመጣ ካለው አደጋ አምላክ ይጠብቀን።
ከከሀዲዎች ፍላፃ አምላክ ይታደገን

No comments:

Post a Comment