Tuesday, August 18, 2009

እውነትን በይፋ እናሳያለን!!

ዘግይቶ የደረሰን ዜና

ሰሞኑን በአባ ጳውሎስ ደጋፊዎች ሰላምና እርቅ እየተባለ ሲቦካ የነበረው ሴራ ግቡን ይመታ ዘንድ ከአቡነ ጳውሎስ የተላኩት ልዩ መልእክተኛ እና የማህበረ ቅዱሳን በጅሮንድ ባለፈው እሁድ ሰንበት በቤተክርስቲያናችን በመገኘት ስለሰላምና እርቅ ሲሰብኩ መደመጣቸው ይታወሳል። እኚህ ደፋር መልእክተኛ ምእመናኑን ከቅዳሴ በሁዋላ ከቤተክርስቲያን እንዳይውጣ አዘው ካህናቱን እና ከሳሾችን አስክትለው ወደቦርድ ጽህፈት ቤት በመሄድ የቦርድ አባላትን ማነጋገራቸው እና ጉዳያቸውም ፈር እንደያዘ ለምእመናኑ ማሳወቃቸው አይዘነጋም። ይህ ድፍረታቸው ሲደንቀን ዛሬ ኦገስት 18 ቀን 2009 ዓ/ም ምሽት ላይ የቤተክርስቲያናችንን ከሳሾችና ግለስቦችን እንዲሁም የቦርዱን ሊቀመንበር ጨምረው በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ሲዶልቱ አምሽተዋል።
ዋናው ጥያቄ የቦርዱ ሊቀመንበር የቦርድ አባላት ሳያውቁና ሳይፈቅዱ እኝህ አባት የማህበረ ቅዱሳን አባል እና የአባ ጳውሎስ ቆሞስ መሆናቸውን እያወቀ በተደጋጋሚ በቤተክርስቲያናችን ውስጥ እንደፈለጉ ገንዘብ እንዲሰበስቡ፤ ስብሰባ እንዲያካሄዱ እና ከከሳሾች ጋር አብረው እንዲዶልቱ የተባበረበትን ምክንያት ለሕዝቡ በአስቸክዋይ እንዲገልጽ እይጠየቅን በተጨማሪም በምንኖርበት ሀገር ሕግ መሠረት የተመስረተው ክስ ብያኔ ሳያገኝ፤ እንዲሁም ከሳሽ በተከሳሽ ቦታ ላይ መገኘት እንደማይገባው የሚያዘውን ሕግ ማስከበር (restraining order) ሲገባው በጎን ተደብቆ ከከሳሽ ጋር አብሮ መዶለት ለምን አስፈለገው? ይህ አድራጎቱ የግለስቡን ህቡዕ የተዛባና አወዛጋቢ አቅዋም ይፋ አውጥቶ እርቃኑን አስቀርቶታል።
በዚህ ስብስባ ላይ የተገኙ ግለሶቦች፤
1. ንቡረእድ (የአባ ጳውሎስ ቆሞስ)
2. አቶ ጌታቸው ወልደሚካኤል
3. አቶ በቀለ ተክሌ
4. አቶ መስፍን ወልደየስ
5. አቶ ኪዳኔ አለማየሁ (በቅርፍቡ የፍሎሪዳን ቤተክርስቲያን የበተኑ የአባ ጳውሎስ
ቀኝ እጅና የዳያስፖራ ቤተክርስቲያናት ብተና መሪ)
6. አቶ በትሩ ገብረእግዚአብሔር
7. ወ/ሮ ጥሩ አየር ፍስሀ
8. አቶ ኢዩኤል ነጋ እና ሌሎችም ግለሰቦች ይገኙበታል።

No comments:

Post a Comment