Friday, April 23, 2010

እንደምን ከረማችሁ!!
 ይህን ግጥም አብረን እናንብብ።
            ማነህ አንተ የቅርባችን እሩቅ?
            እኛማ እኛ ነን ያንተስ ከየት ይሆን?
            ያስተሳሰብህ መደቡ? ማነህ አንተ?
            ሳጥናኤል ነህ ከንቱኤል? ዳንኤል ነህ ዋሾኤል?
           “ጋሼ!” በሉኝ የምትል፤የአዛውንት ቅምጥል፤
           ያለባበስና የንግግር ሊቅ! የት ነህ አንተ የቅርባችን ሩቅ?
           ሆደ ባሻ ነህ! ወንድም ውሻ? ወንድም ጋሻ ነህ የተስፋ እርሻ?
          ባለ ራእይ ነህ ወይስ ተልካሻ?
                   እባክዎ “እርሶ” ማኖት አንቱ? እውነቱ ወይስ ክህደቱ?
                  ቃሎት የሆነብን ከንቱ? ማኖት እርሶ?
                  ለተስፋና ለፍቅር፤ ፍጻሜው ሆነብን እንጂ - ቃል ብቻ የቃል ክምር!
                  አንተኛውስ ማነህ?
        ጆሮጠቢ ነህ የገንዘብ ወፍጮ?
        መቀጮ ነህ ወይስ መዋጮ?
       ማነህ አንተ? ማነሽ አንቺ? የት ነሽ አንቺ?
       እና እኔ ደግሞ ለማን እንደሆነ ባላውቅም!
       “እባክህ ማነህ አንተ?” ብዬ ጠየቅሁ።
                እንደሆዱ ነህ እንዳንጎሉ? የት ነው ያስተሳሰብህ ክልሉ?
                የራእይ ኮከብ ቃሉ? የት ነው? ማነህ አንተ? የት ነህ አንተ?
                ምነው የህሊናህ ባንዴራህ ተደበቀ?
               ምነው ክብርህና ኩራትህ ተሳቀቀ?
    ማነህ አንተ? ጀብደኛ ነህ ቀልደኛ? ወይስ ተመጻዳቂ ህልመኛ?
    እና የት ነህ አንተ? ማነህ አንተ? ወንድም ውሻ? ወይስ ወንድም ጋሻ? 
                                           ከደራሲ ተስፋየ ገብረአብ የተወሰዱ ግጥሞች።

No comments:

Post a Comment