Thursday, February 25, 2010

ወያኔ ካድሬዎችን ለመመልመል ጉባኤ ጠራ!!!!

ውድ ምእመናን ሆይ!
ቀደም ሲል የወያኔ ተወካዮች የመተዳደርያ ደንባችንን ለውጠው ቤተ ክርስቲያናችንን ለአባ ጳውሎስ አሳልፎ ለመስጠት ያደረጉት ጥረት መክሸፉን አንዘነጋውም። ከዛም የሚካኤልን ታቦት ከሰው ፍርድ ቤት እያመላለሱን ይገኛሉ። ባንጻሩም ምእመናን ቦርድ ውስጥ የነበሩትን ተወካዮቻቸዉን በድምጽ ብልጫ ማስወገዳችን የሰሞኑ ትኩስ ዜና ነው።

በዚህ የተበሳጩት የወያኔ ካድሬዎች ደካማ ህሊና ያላቸውን ሰዎች መልምለው የቤተ ክርስትያን አባል ካደረጉ በኋላ በደምጽ ብልጫ ቤተክርስትያናችንን ለመውሰድ በድፍረት ጉባኤ ጠርተዋል። ወያኔ ለጀመረው ክስና ለአባላት ምልመላ መጠነ ሰፊ ብር መድቧል።

ይህንን ጉባኤ በግንባር ቀደምትነት የሚያስተባብሩት የከተማው ከበርቴዎች ቀደም ሲል ብዙ የዳላስ ነዋሪዎችን በሽርክና አብረን ንግድ እንክፈት እያሉ ሲዘርፉ የነበሩ ግለሰቦች መሆናቸውን እናውቃለን። ዛሬ አልማ (የአማራ የልማት ማህበር) የሚባል ድርጅት አቋቁመው ሁለተኛ ዙር ዘረፋ በህዝቡ ላይ ለማፋፋም ወያኔ ያሰባሰባቸው ግለሰቦች ናቸው።

እኛ ደሃዎቹና ደካሞቹ ለነዚህ ሃያላን አምላክ ቀና መንፈስ እንዲሰጣቸው በጸሎት እንትጋ!
አሜን!!

No comments:

Post a Comment