Friday, December 17, 2010

አስቸኳይ መልእክት ለደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል አባላት በሙሉ።

አስቸኳይ መልእክት ለደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል አባላት በሙሉ።

ቤተክርስቲያናችንን ለማፍረስ ካሁን ቀደም የነበርው ቦርድ ጋር ተጠግተው የቤተክርስቲያኑን ካዝና ሲያራቁቱና ምዕመኑን በዘር፤ በዚጋ፤ በጓደኝነት፤ በአበ ልጅነት፤ በአብሮ ማህበር ጠጭነት ሲከፋፍሉ የነበሩ ግለሰቦችና የድሮው የቦርድ አባላት የሚመለሱበትና አንደገና የሚመዘብሩበት ጥረታቸው በፍርድ ቤት እንዳልተሳካ ስላወቁ አንዳንድ ቀዳዳ እየፈለጉ በሚመጣው ሰንበት እንደገና ቤተክርስቲያን አረከሱ በሚል የተንኮል ተግባር ብጥብጥ አስነስተው ቤተክርስቲያን ሊያዘጉ መዘጋጀታቸውን ልናበስርላችሁ እንወዳለን። እነዚሁ ግለሰቦች ሰሞኑን በቦርዱ ጸሃፊያችን ላይ የደረሰውን አንዳንድ ውዥንብርና አለመግባባት አስመልክተው ገና ያልተፈጸመ ውንጀል ልክ እንደተፈጸመ አድርገው ቤተክርስቲያኑን አሁን ያለው ቦርድ አረከሰ በሚል ሠይጣናዊ ተንኮል በየ ቤቱ እየደወሉና ህዝቡን እያነሳሱ መሆኑን ሁላችንም እናውቃለን።
እነዚህ ሰይጣናዊ አወናባጆች እጃችንን ይዘው ለጥቅማቸው ሲሉ ወደ ገሃነም ሊያስወረውሩን እንጅ እውነት ለቤትክርስቲያኑም ሆነ ለኝ አስበው እንዳልሆነ እንድንረዳ የሚቀጥለውን የአየሱስን ትምህርት የዘንላችሁ ቀርበናል፤ አብረን እናንብበው፦
የዮሃንስ ወንጌል ቁጥር 8/1-11
“-----ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዝች ሴት ወደ አርሱ አመጡ፤በመካከልም አርስዋን አቁመው፤- መምህር ሆይ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በህግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት። ---- እየሱስ ግን ጎንበስ ብሎ በጣቱ ብምድር ላይ ጻፈ፤ መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ ፤-ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድጋይ ይውገራት አላቸው። ድግሞም በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ። እነሱም ይህን ሲሰሙ ህሊናቸው ወቀሳቸውና ክሽማግሌወች ጀምሮ አስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ እየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች። እየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ፤- አንቺ ሴት እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? አላት። እርስዋም ጌታ ሆይ አንድ ስንኳ አለች። እየሱስም፤- እኔም አልፈርድብሽም ሂጅ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትስሪ አላት።----”
በተጨማሪም፤-
የማርቆስ ወንጌል ቁጥር 7/20-23
“---ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፤ ዝሙት፤ መስረቅ፤ መግደል፤ ምንዝርነት፤ መጎምጀት፤ ክፋት፤ ተንኮል፤ መዳራት፤ ምቀኝነት፤ ስድብ፤ ትዕቢት፤ ስንፍና ናቸውና ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውንም ያረክሰዋል።”
ውድ የቤተክርስቲያን አባላት፤- እንኳን ገና ምንዝር ሲሰራ ያልተያዘ ግለሰብ ቀርቶ ምንዝር በግልጽ ስትሰራ የተያዘችውን ሴት ሳይፈርድባት ሁለተኛ ኃጢአት አትስሪ ብለ ሲያሰናብታት፤ እኛ የትኞቹ ሳድቃን ሆነን ነው የመጀመሪያውን ድንጋይ የምንወረውረው።
በእግዚአብሄር ፊት “ ---ሰውን የገደለንም ሆነ የሰረቀ፤ ምንዝርነት የፈጸመም ሆነ የተዳራ፤ ተንኮል ያዘለም ሆነ የተመቀኘ፤ በሃሰት የመሰከረም ሆነ በሃሰት የከሰሰ ሁሉም” ሃጢአት እኩል መሆኑንና አንዱ ካንዱ ያማይበልጥ መሆኑን ለማሳየት እየሱስ ክርስቶስ ከላይ በማርቆስ ውንጌል ቁጥር 7/20-23 የተናገረውን ተመልሰን እናንበብ።
ታድያ እነዙህ ተንኮለኞች እናንተው ፊት ሲዋሹ፤ በሃሰት ሲመሰክሩ፤ ንጹህ የቦርድ አባላትን ገንዘብ ሰረቁ ብለው በሃሰት ሲከሱ፤ ፍርድ ቤት ቀርበው ወንጌል ጨብጠው ሲቀጥፉ መናፍቃን እይሉ መእመኑን ሲሰድቡ በማርቆስ ውንጌል ቁጥር 7/23 መሰረት የረከሱ አይደሉምን። እኛስ የነሱን የስም ማጥፋትና የማወናበድ ዘመቻ ከተቀበልን መርከስ አይሆንብንም ይሆን? መልሱን ለናንተ ፈጣሪ ልቦናችሁን ከፍቶ እንድታስተውሉት ያደርጋችሁ ዘንድ ምኞታችንን እናቀርባለን። ምናልባት ተሳስታችሁ የመጀመሪያውን ድንጋይ ለመጣል ሳይሆን ለመወርወ ለምትመኙ ሁሉ ይሚቀጥለውን አስቡ። ዋናው ጸሃፊያችን ስራውን ቢለቅ የሚጎዳው ማነው? ቤተክርስቲያኑ ወይስ ጸሃፊው? እንድ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ገና ያልተረጋገጠና ያልተፈጸመ ወንጀል አስቧልና ቤተክርስቲያን አያገለግልም ማለት የመጀመሪያውን ድንጋይ መወርወርና በሃሰትም መፍረድ መፍረድ ስለሆነ ከመሳሳታችን በፊት ደግመን ደጋግመን ነገሩን በጥሞና እናሰላስል። የተንኮለኞችን ግፊት ተከትለን
 ን በችኮላ የምናደርገው አድራጎት ግን የሚጎዳው ቤተክርስቲያናችንን አንጅ አገልጋዩን እንዳልሆነም ማመዛዘን አለብን። የህ የተባለው የቤተክርስቲያናችን አገልጋይ አገልግሎቱን ቢያቋርጥ የሚጎድልበት ጉድለት ምን ይሆን?
1 አገልግሎቱን ስላቋረጠ የሚከፈለው ደመወዝ ይቀርበት ይሆን?
2 ከሃገር ይባረር ይሆን?
3 ጊዜውን የሚያሳልፍበት ቦታ ያጣ ይሆን?
4 ሌሊቱን ቤተክርስቲያኑ ለማሻሻል ሲከራከርበት የሚያድርበት ቦታ አያገኝ ይሆን?
5 ወይስ በምንለቅለት ጊዜወች አልጋው ላይ ተኝቶ እንቅልፍ አይወስደው ይሆን?
ባኳያውም ይዚህኑ ግለ ሰብ ቦታ ተክቶ ባስቸኳይ የሚገባ ጻድቅ የሆነ ሰው አዘጋችታችሁ ማቅረብ
ያለባችሁ ግዴታ መሆኑን እንዳትዘነጉ ይሁን። አለበለዚያ የምትበድሉት የራሳችሁን ቤተክርስቲያን
ነው።
በእኛ አስተሳሰብ ወደ ቤተክርስቲያን የሚሄድና የሚጸልይ ብሎም ቤተክርስቲያን አገልግል ትብሎ
የሚጠየቅ ንጽሃን ሳይሆን አውቆም ሆነ ሳያውቅ ሃጢያት የሚፈጽምና አባክህ አምላኬ በደሌን
ይቅር በለኝ አኔም የበደሉኝን ይቅር እል ዘንድ ወደ ፈተናም አታግባኝ የሚል ሁሉ
እቤተክርስቲያን በመድረሱና በመጸለዩ ይቀር ስለተባለ ማንም ሰው ንጽህ ነው።
“እኔም አልፈርድብሽም ሂጅ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትስሪ አላት” የሚለው
የእየሱስ ጥቅስ ሃጢአት የሰራ ሁሉ ይቅር እንደሚባልና ሃጢአቱም እንደሚደመሰስ ስለሚያስረዳን
ሃጢአትም ሰርቶ የተማረ ሁሉ ንጹህ ነው።
ይሄው ጸሃፊያችን ጥፋት አጥፍቷል ብላችሁ የምታምኑ ካላችሁ መልሳችሁ ክስራው ይባረር
ሳይሆን ንስሃ ይግባ ማለት ብቻ አንጅ በወደቀ ዛፍ ላይ ምሳር ይዞ መረባረብ አይገባም።
በ እግዚአብሄርም ፊትም ሆነ በምድር ያስጠይቃል።
በትዕግስት የአስተዳደር ቦርዱ የሚወስደውን እርምጃ መጠበቅ ግን አግባብ ያለው ይመስለናል።
ለሁላችንም እንደገና የምናመዛዝንበት ልቦና ይሰጠን ዘንድ አምላካችንን እንለምን! 0

አሜን! አሜን!

No comments:

Post a Comment