Tuesday, December 14, 2010

እንዳይፈርድባችሁ አትፍረዱ

እንዳይፈርድባችሁ አትፍረዱ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፤ በምትሰፍሩበትም
መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል።
የማቴወስ ወንጌል ቁጥር 7/1

በዚህ በያዝነው ወር በ 13/2010 መረዋ የተባለው የቤተክርስቲያን ክሳሽና ቤተክርስቲያናችንን ላባ ጳውሎስ ለመሸጥ የተዘጋጀው በወያኔው ተዎካይ በ ሻለቃው የተቋቋመው ብሎግ(ጦማር) ስለ አንዱ የቤተክርስቲያናችን አገልጋይ የጻፉትን አንብበን ቆርጠው የተነሱበትን የቤተክርስቲያን ማዘጋት ትግል ለማካሄድ የማይፈነቅሉት ድንጋይና የማይጎረጉሩትን ጉድጓድ እንደሌለ ለማወቅ
አያዳግትም።
“በክርስትና ስምና በኢትዮጵያነታችሁ አሜሪካን አገር ያለውን ቤተክርስቲያን ሁሉ ብትችሉ ለኛ የምታስረክቡበትን ዘዴ ፈልጉ ባትችሉ አዘጉ” ተብለው የተለኩ የቀበሮ ለምድ ለብሰው በውስጣችን የሰረጉ ብዙ ተንኮለኞች እንዳሉ ሁላችንም እናውቃለን። የምንኖረው ህግና ደንብ የሚከበርበት ሃገር ላይ መሆኑን የዘነጉ እነዚህ ተኩላውች፡ አንድ ግለ ሰብ ፍርድ ቤት ቀርቦ ጥፋተኛ ነህ ተብሎ ገና አስታልተፈረደበት ድረስ የነጻነት መብቱ የተጠበቀ መሆኑን በመዘንጋት እንደጥፋተኛ ቆጥረው ማህበርተኛው በከፍተኛ ድምጽ
ብልጫ የመረጠውን የቤተክርስቲያን ነጻ አገልጋይ ከሃላፊነትህ ለማውረድ ቅስቀሳ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።
የዚህኑ የወያኔ ድረ ገጽ ቅስቀሳ ለማንጸባረቅ የምትመኙ ካላችሁ ልናሳስባችሁ ይምንመኘው፦
አንደኛ፤-በምድርም የግለሰብ መብት መግፈፍ ነው።
ሁለተኛ፤- በሰማእታትም “እንዳይፈርድባችሁ አትፍረዱ፡በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረዳችኋልና” ማቴወስ ቁ.7/1
ይሚለውን የየሱስ ክርስቶስን ትዕዛዝ መተላለፍ ነው።
“ታስረው እሑድ ከቤተክርስቲያን መጥተው የምእመናንን ዓይን እያዩ ማስታወቂያ መናገራቸው ቢገርመንም” ለሚለው መልስ በቀላሉ እናንተ ብሆዳችሁ ቂም ይዛችሁ “ዛሬ ምን ይባል ይሆን ቤተክርስቲያን ሄደን ምን እንደሚባል እንሰልል” በማለት ሃይማኖተኛ ለመምሰል የእግራችሁን ጫማ አውልቃችሁ የልባችሁን አሳት ይዛችሁ ወደተቀደሰው ቦታ መግባታችሁን የማያውቅ ም
እመን ይኖር ይሆን?
የጠቀሳችሁት ግለ ሰብ ሊያገለግሉ፤” የመጣውን ምእምን ዓይን እያየ የተናገረው” ላላችሁት አገልጋዩ በሆዳቸው ተንኮል ተሸክመው አለመሆኑን ተረዱ። ጥፋት ቢያጠፉም እንኳን፡ ፈጣሪይቸውን ሰው ነኝና ጥፋት አጥፍቻለሁ ማረኝ። የልቤን እምታውቀው አንተ ነህና ይቅር በለኝ ሳይሉ ወደ መድረክ እንደማይገቡ አንጠራጠርም። አምላካችንም እውነት ጥፋት አጥፍተው እንደሆነ አንደ ማራቸው እናምናለን። የናንተን ትንኮልና መርዝ መርጨት የቤተክርስቲያናችን ምእመን የለመደው ስለሆነ በእናንተ
ተንኮል አይበገርም። ለማለቱማ ድሮ ጀምሮ እኝሁን መልካም አስተዳዳሪ ያላላችኋቸው ስድብና
ዘገባ  ይኖር ይሆን?  
ለዛሬው ይሄን የመርዝ ማለስለሻ ይዘንላችሁ ቀርበናል። 
ሰሞኑን በዝርዝር ተፈጸመ የተባለውን አለመግባባት እስትናቀርብላችሁ ድረስ አወናባጆች እንዳያውናብዷችሁ አደራ እንላለን።
ዋናው መታወቅ ያለበት እኝሁ የተባሉት ግለሰብ ህዝቡ የጣለባቸውን እምነት ለመወጣት ሌት
ተቀን ደከመኝ ክስራ አስተጓጎለኝ ሳይሉ ጉልበታቸውን ጊዚያቸውንና ገንዘባቸውን በነጻ የሚሰጡ መልካም አገልጋያችን ስለሆኑ፤ እንኳን አሉ ባልታ ቀርቶ አዉነት አጠፉ ተብለው  ቢፈረድባቸውም ማስወጣት ቀርቶ ጊዜያቸውንም ሲጨርሱ ካገልግሎት እንዳይወርዱ
የምንማጠናቸው ግለሰብ መሆናቸውን የቤተክርስቲያኑ ምእመን ሁሉም ባንድ ድምጽ ደጋፊያቸው መሆኑን ለጠላቶቻችን እናበስራለን። በ መረዋ ብሎግ ላይ የተፍለጠፈው ተግባር እውነት አለመሆኑን ለመረዳት ከፈለጋችሁ በመጀፍመርያ መጠየቅ ያለባችሁ ነገር ቢኖር መረዋ “የመንገድ ሴተኛ አዳሪ ሲያነሱ ተገኝተው” ያለው የተባለችው ሴተኛ አዳሪ የተነሳችው ለግብረ ስጋ ነው? ወይስ ለሚያካሂዱት የእንጀራ ጋጋሪነት ስራ እንድትሰራላቸው ይሆን? ብሎ ማመዛዘን ተገቢ በሆነ ነበር። በፍርድ ቤት እውነቱ  ውጥቶ እስቲፈርድ ድረስ መታገስን አለመሻት ከዓምላካቸን ጋር እንደሚያጣላን አንጠራጥርም።
የቤተክርስቲያኑ አባላትም ይህንኑ አምኖ ቦርዱ በጊዜው የሚወስደውን እርምጃ በጥሞና
እንዲጠብቅ ጥሪአችን ይድረሳችሁ።
ለሁላችንም አምላካችን የሚያመዛዝን ልቦና እንዲሰጠን እንጸልይ።


አሜን!

No comments:

Post a Comment