Friday, October 30, 2009

እርምጃ መዉሰድ አስፈላጊና ማብታችን ነዉ!!!
እንድታዉቁት ያህል!
ካሁን ቀደም የቦርዱ ሊቀ መንበራችን ቤተ ክርስቲያናችንን ላባ ፓዉሎስ ሊሸጥ ተስማምቶ አቡነ
ቆስጦስን ለማስመጣትና ለማስረከብ ተደርሶበት እንዳልተሳካለት ስንነግራችሁ ልታምኑን
ያልቻላችሁ ሁሉ ለነ አቶ አፈ ቀላጤወች ትልቁ ማስተማኛ ይሄዉላችሁ።
ይሄዉ ሊቀ መንበር ጥር ስላሳ አንድ ላይ ያወጀዉን የቦርድ አዋጅ በመጀመሪያ ቤተ
ክርስቲያናችን ገለልተኛ ነች በተከታይ 501 c ያላቸዉ ቡድንም ሆነ ማንኛዉም ማህበር የቤተ
ክርስቲያኑ መምበር አይሆንም እያለ ይሄዉላችሁ እራሱ ህጉን እየጣሰና እራሱን ብቻ ሳይሆን
የቦርድ ግብረ አበሮቹንና የግል ጓደኞቹን እነ ዶክቶር…. እነ አቶ… እያዋረደ ነዉ።
(ስልካቸዉን ላባ ፓውሎስ በጻፈው ደብዳቢ ላይ ይገኛል)
በጣም የሚገርመዉ እኝህ ዶችቶር ጓደኛዉ አለም አቀፍ ድርጂት ሲሰሩ ኖረው አርፈው ያለ
ምንም ጭቅጭቅ ጡረታቸዉን እግዚአብሄርን እያመሰገኑ በመኖር ፋንታ እዚህ ቁማርተኛ ነጋዴ
እኩያቸዉ ያልሆነ ሰዉ ጋር ዶልተው የሰዉ ስም ሲያጠፉ እየታዩና ቤተ ክርስቲያን ለመሸጥ
እያስማሙ መሆናቸዉን ለአባ ፓዉሎስና ለአዲስ አበባዉ ሲኖድ እንጠቅሳለን “እኛ በዓለሙሁሉ
ተሰራጭተን የምንገኝ ተባባሪዎች” በማለት መማጠናቸዉን እራሳችሁ አንብቡ።
በተደጋጋሚም ልንገልጽላችሁ የምንፈልገዉ አቶ ሊቀ መንበርና እነዚሁ ጓደኞቹ የቴክሳስ ቀረጥ
ነጻ ግብር ክፍያ 501 c አዉጥተዉ ገንዘብ እየሰበሰቡ መሆናቸዉን ላላወቃችሁ ሁሉ እውቁ
እንላለን።
እኝሁ ዶክቶር ጓደኛዉ ባለፈዉ ጥቂት ስብሰባ ላይ ይሄዉ ሰነድ ሲነበብ ሊቀ መንበሩ እኮ የጻፈው
በግሉ ነዉ በማለት ሃፍረታቸዉን ተጎናጽፈዉ ሄደዋል።
አፈ ቀላጤዉም ይሄ ድርጊት አዋራጅ መሆኑን ተመልክቶ አቶ ሊቀ መንበር ይሄን አይጽፍም
እያለ በሃይል ቃል ሲያስተባብል መዋሉን ልንገልጽላችሁ እንወዳለን። ይህንኑ ግለ ሰብ ጓደኛችንን
የዎያኔው ተጠሪ በዳላስ ከተማ ያሉት የቤተ ክርስቲያኑ አስተናጋጅ ኮሚቴ ዋና ሹምና የሊቀ
መንበሩ ብቻ ሳይሆን የማህበረ ቅዱሳን ደጋፊ ዉስጠ ሚስጥሩን ሳይነግሩት በየ ስብሰባዉ ላይ ሁሉ
እንዲጋፈጥ አድርገዉታል።
እጥብቀን ይህን ጓደኛችንን የምንመክረዉ ለነሱ ስትል ስምህን አታጥፋ ነው።
በተጨማሪ ልናሳስባችሁ የምንፈልገው የቦርዱ ጸሃፊ ህዝብ በተሰበሰበበት የመዕማናን ስብሰባ ላይ
ለዛሬ ሳይሉ ግጥም አድርገዉ መዋሸታቸዉን ነዉ እንጠቅሳለን “ የቤተ ክርስቲያኑ ከሳሾች
እቤተ ክርስቲያኑ ዉስጥ ያስገበኋቸው እኔ ነኝ እንጅ አቶ ኢዩኤል እይደለም፡ እንዲያዉም
በቦታው አልነበረም” ብሎ በአይናችን ያየነውን ለማስተባበል ሞክሯል።
ይሄ ሃሰተኛ የቦርድ አባል መሆን ይገባዋልን?
እናንተው ፍረዱ።
በድጋሜም ለቦርድ የምርጫ ኮሚቴ ድሮ የተሰናበተው የማህበረ ቅዱሳን የትምህርት ኮሚቴ
አሁንም ስላለ የምርጫ ኮሚቴ ዉስጥ መግባት አለበት እያለ ማወናበዱን ሰምተናል።
ዉድ ማህበርተኛ ሆይ፦
እነዚህን የቦርድ ሊቀ መምበርና ይህን ከሃዲ ጸሃፊ ምርጫዉ ከመካሄዱ በፊት ማባረር ይገባናል
ብለን ስለምናምን ሰሞኑን ስብሰባ ጠርተን እንዲዎርዱ እንጠይቅ።

No comments:

Post a Comment