Wednesday, October 21, 2009

ቤተ ክርስቲያናችንን እናድን እያልን እንማጠናለን!!!!
የዚህ ደብር መዕመን እግዚአብሄርን የምንፈ-ራ ዓምላካችንን የምንወድና የምንታዘዝ ነን! ትሁት
ልቦናችንን አይቶ በጥገኝነት ከምናመልክበት ቤት አዉጥቶ ዛሬ ይህን ትለቅ ሕንጻ የሰጠን
አምላካች ስሙ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን።
መዕመኑ በመላእክትና በጻድቃን ስም ዙሪያ ተሰብስበዉ ይዘክራሉ ይጽልያሉ የበረከቱ ተሳታፊ
ለመሆን እንሽቀዳደማለን ደስ የሚል የክርስትና ሕይወት ነዉ።
በዚህ መንፈስ ለረጅም ዘመን አብሮ ዓማላክን በማምለክ በተመሰረተ ግንኙነት ብዙወቻችን
በጋብቻ በአበልጅነት ዝምድና ፈጥረናል ከሌሎቻችንም ጋር ጥለቅ ወዳጅነትን መስርተናል።
የዚህ ሁሉ መሰረት እያንዳንዱ ግለሰብ ለዓምላኩና ልኃይማኖቱ ባለዉ ፍቅር ሳቢያ የተፈጠረ
ወዳጅነት ነዉ። የተቀረዉ ግንኙነት በዚህ ጽኑ ዓላማ ዙሪያ የተገነባ ክርስቲያናዊ ማሕበራዊ
ህይወት ነዉ።
ከኅዋሪያት መሃል ይሁዳ ጌታን ክዶ እንደሸጠዉ እናዉቃለን። ከኛም መሃከል ለአገልግሎት
መርጠናቸዉ ለጥቅማቸዉ ሲሉ እኛ ዎደማንፈልገዉ አቅጣጫ ልወስዱን እየሞከሩ ያሉትን
ዎንድሞቻችንና እህቶቻችን የመጨረሻዉን ጥፋት ክመፈጸማቸዉ በፊት ማቆም አለብን።
እምነታችን ክማንም በላይ መሆኑን የምናሳይበት ሰዓት ዛሬ ነዉ።
አባ ፓዉሎስ ወያኔ ናቸዉ። ስለዚህም ነዉ ሓገር ቤት ያለዉ ወገናችን ያልተቀበላቸዉ። ባገኘዉ
አጋጣሚ ሁሉ ተቃዉሞዉን እየገለጸ የሚገኘዉ። እርሳቸዉም ክዚህ የተነሳ እንደ አንድ አምባ
ገነን መሪ በደረሱበት ሁሉ በመከላከያ ሰራዊት አባላት የሚጠበቁት።
ሥራቸዉንም የሚሰሩት በሕዝብ ደህንነት ዓባላት ታጅበዉ ነዉ።
ነጻነቱን የተነጠቀዉ መብቱ የተረገጠዉ የሃገራችን ጀግና ህዝብ ይህ ሁሉ ችግር ሳይገታዉ እኝህን
አባት ጥግ ይዘው እንዲንቀሳቀሱ አድርጓል።
እኛ በነጻነት የምንኖር ያለምንም ስጋት ሃሳባችንን መናገር የምንችል ወገኖች ግን የኛዉ ናቸዉ
ይምንላቸዉ ጉዶች ለዚህ አባት አሳልፈዉ ሊሰጡን በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ በግልጽ እየታየ
በፈጠርነዉ ማህበራዊ ኑሮ እርምርጃ ላንወስድ በይሉኝታ ታስረን እንገኛለን።
ከዕምነታችን ይልቅ ወዳጅነታችንን አስቀድመን ወደ ጥፋት ጎዳና እየተጓዝን ነዉ።
ይህ ዝምታችን የሚያበቃዉ መቸ ነዉ?
የቦርዱ ሊቀ መንበር ሰሞኑን ላባ ፓዉሎስ የጻፈዉን ደብዳቤ እንዳነበባችሁ እርግጠኞች ነን፡
ጥቂቶቻችሁም ለሰላም ሲባል የተጻፈ ጥሩ ደብዳቤ ነዉ ስትሉ ተሰምቷል።
ዉድ መዕመን ሆይ! ፋሽስት ሙሶሎኒ ሃገራችንን ሲወር ትምህርት ቤት እከፍታለሁ ሆስፒታል
አቋቁማለሁ መንገድ እዘረጋለሁ ህዝቡን ነጻ እደርጋለሁ ብሎ ነበር ሲከራከር የነበረዉ፡
እንድም ቀን ባሪያ አድርጌ ቀጥቅጨ ልገዛ ነው ብሎ አልተነፈሰም።
ዲያብሎስም ጌታን ሲፈታተን የዓለምን መንግስት ሁሉ ከነ ክብራቸዉ እሳየዉና “ ተንበርክከህ
ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ” አለዉ ማቴዎስ 4፡8-9 ይሁዳ አሳልፎ ሲሰጠዉ ሰይፍ
የያዙት ሰራዊት ክኋላ ተደበቀዉ እርሱ ግን “መምሕር ሆይ! ሰላም ላንተ ይሁን” በማለት ነበር
የቀረበዉ ማቴዎስ 26፡49
የኛም ሊቀ መንበር የጻፈዉ ደብዳቤ ዉስጡ ሲታይ ጉዱ ብዙ ነዉ “እኛ በዓለሙ ሁሉ
ተሰራጭተን የምንገኝ ተባባሪዎች” እያለ የሳቸዉ ተወካይ መሆኑን በደብዳቤዉ መግቢያ ላይ
ገልጾታል።
501፡ c ፈቃድ ያለው ድርጂት አቋቁመዉ ገንዘብ እየሰበሰቡ ነዉ።
ቤተ ክርስቲያናችን ዛሬ ከፍተኛ አደጋ ላይ ነች፡ ሁሉም ሊቀራመትዋት ክበዋታል! የዓምላክን
ጥሪ ተቀብሎ የሚመራ ሰዉ ትፈልጋለች።
ነገሩ ካለቀ በኋላ መጸጸት ፋይዳ የለዉም!
በህብረት ተነስተን ቤተ ክርስቲያናችንን ከነዚህ ቡድኖች መንጋጋ እናዉጣ!!!
እግዚአብሄር ይርዳን።

No comments:

Post a Comment