Wednesday, October 14, 2009

የቤተ ክርስቲያናችን ችግሮች በአስተዳደር ቦርዱ እይታ፡
የተመረጣችሁት፦
ተበላሽቶ የነበረዉን የቀድሞ አስተዳደር ለማስተካከል ነበር፡ በማስተካከል ፋንታ እያበላሻችሁ ነዉ
አይደል?
ዛሪ ያን አደራ ረስታችሁ ከቀድሞ የእኛ ሰዎች ከምትሏቸዉ ጋር እየተባበራችሁ በዱሮው አመራር
ያለ ምንም ለዉጥ እየሰራችሁ ነው አይደል?
ማህበረ ቅዱሳን መለካት የማይችል ፍዳ ላይ ጥሎን አሁንም የቢተ ክርስቲያን አባል ልታደርጉ
እየታገላችሁ ነው አይደል?
ይህንንም ባሳተማችሁት የቀን መቁጠሪ አና በይፋ ባፋአችሁም ገልጣችኋል አይደል?
የማህበረ ቅዱሳን አባል እና የ አባ ፓዉሎስ ተጠሪ ቀሳዉስት ቀጥራችሁ ህዝቡን እያስበጠበጣችሁ
ነው አይደል?
ይኅዉ ተጠሪ ካህን በጾም ዎቅት ብር ተቀብሎ ሲያጋባ ዝም አላችሁ አይደል?
ሕዝቡን ሲያዉኩ በመቅደስ ቆመዉ ሲሳደቡ እና ስለማህበረ ቅዱሳን ድርጅት በትምህርት መልክ
ሲያስተላልፉ ሰምታችሁ እንዳልሰማ ሆናችሁ አይደል?
የማህበረ ቅዱሳን አባል ለትምህርት ጋብዛችሁ አስመጣችሁ አይደል?
እነዚሁ ቀሳውስት ሕዝቡ ገንዘብ እንዳያዋጣ ሲቀሰቅሱ ዝም አላችሁ አይደል?
“ሕዝብ ለቢተ ክርስቲያን ገንዘብ እንዲሰጥ ለማስተማር መንፈስ ቅዱስ አላሳሰበንም” ብለዉ
በጉባኤ ላይ ስናገሩ ሰምታችሁ ምን አደረጋችሁ?
የማህበረ ቅዱሳን ቄሶቻችሁ እንግዳ ቄስ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ዎረቀት ሲበትኑ ምን
አደረጋችሁ? ዚም ብላችሁ አያችሁ አይደል?
የአባ ፓዉሎስና የማህበረ ቅዱሳን ቄሶች አድማ መትተዉ መቅደስ ዉስጥ ተደብቀዉ ሲዉሉ ዝም
አላችሁ አይደል?
ቄሶቹም እናንተም ቂም ይዞ ያለንስሃ መቀደስም መጸለይም ይቻላል ብላችሁ ታምናላችሁ
አይደል?
ማህበረ ቅዱሳን አገልግሎት የሚሰጡትን የነሱ ያልሆኑ አባላት ሰድበዉ ሲያባርሩ አይታችሁ ዝም
አላችሁ አይደል?
የሂሳብ አያያዝና የአስተዳደር ሥራት ይለዎጥ ቢባል አሻፈረን አላችሁ አይደል?
ግለጽ አሰራርን አትዎዱም አትቀበሉም አይደል?
ገቢዉን እንደፈለጋችሁ ማዉጣት እንጅ ባጀት አዉጥታችሁ በባጀት መስራትን አትዎዱም
አይደል?
ቤት ክርስቲያኑን እየጎዱ ያሉትን ቀሳዉስት ገንዘብ ባይኖርም ተበድራችሁ ደመዎዝ መክፈል
ታስባላችሁ አይደል?
ከሳሾች ጋር አብራችሁ መዶለታችሁን አትክዱም አይደል?
እነሱ ከዉጭ እናንተ ከዉስጥ ሆናችሁ ቤተ ክርስቲያኑን ለማዉደም እያሰባችሁ አይደል?
ካስዎጡኝ ዎይም እንደገና ካልመረጡኝ ይህን ቤተ ክርስቲያን አዎድመዋለሁ የሚል የቦርድ አባል
እንዳለ ታዉቃላችሁ አይደል?
መጠነ ሰፊ የሆነዉን የቤተ ክርስቲያኑን ችግር ከ መዕመኑ ጋር ስብሰባ ጠርታችሁ መላ መፈለጉን
አትፈልጉም አይደል?
ተቀዳሚ ዓላማችሁ እንደገና ካልተመረጣችሁ ይሄ ቤተ ክርስቲያን የሚደክምበትን እና
የሚዎድቅበትን መንገድ እያዘጋጃችሁ አይደል?
እንደገና በተደጋጋሚ ተመርጣችሁ የዱሮ ግብራችሁን (ብዝበዛችሁን) ለመቀጠል በምታደርጉት
ዘመቻ ይህን ቤተ ክርስቲያን ያለኛ በቀር ማስተዳደር የፍሚችል የለም በሚል ሽፍን ቅስቀሳ በ
አፈ ቀላጤያችሁ እያስዎራችሁ ነዉ አይደል?
ምርጫዉ ካልተሳካላችሁ የእኛ ዎገኖች የምትሏቸዉን ሰዎች አዘጋጅታችሁ ለማስመረጥ ቅስቀሳ
ጀምራችኋል አይደል?
ደብራችን ላይ ይህን ሁሉ ደባ እየፈጸማችሁ ለምን ተብላችሁ ስትጠየቁ ስማችሁ ስለተጠቀሰ
እንደ እብድ አደረጋችሁ ( እዉነቱን ሲነግሩት እንደ ኮለኮሉት ያህል ይስቃል) እንደሚባለዉ
እዉነቱ ሲዎጣባችሁ አሳበዳችሁ አይደል?
የዚህ ሁሉ ጥያቄ መልሱ አዎን ነዉ፡
ማሳሰቢያ፦
በዚሕ አትም አባልና ተቆርቋሪ የሆናችሁ የሚካኤል ዎዳጆች በሙሉ ከላይ የተጠቀሱትን
መንደርደሪያ አድርጋችሁ ቤተ ክርስቲያናችን አደጋ ላይ መሆኑን ተረድታችሁ የሚጠነሰሰዉን
የሃሰት ተንኮል እንድትረዱ ነዉ፡
ለምሳሌ ያህል የቦርዱ ሊቀ መንበር የሚያሰራጨዉ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ የማይፈለጉ ቄሶች
የማይዎጡት ከሳሾቻችን ጋር እንዳይተባበሩ ነው የሚል አሳሳች ሃሳብ የሚያሰራጭ መሆኑን
ነግሯችኋል፡
የህግ ሰርቲፊኬት እንዳለዉ ሊያሳየን ይሆን?
ዎይስ ጠበቃ አነጋግሮ ይሆን?፡ ከከሳሾችህ ጋር ይተበበራል ያለዉ?
ይህ አዎናባጅ ግለሰብ ቤተ ክርስቲያኑን ክመበዝበዝ አልፎ ተርፎ የማን አለብኝ ስራ አየሰራ
መሆኑን መዘንጋት የለብንም።
ዉድ ሊቀ መንበራችንና ግብረ አበሮቹ ህዝቡ እንዳልተደሰተ በየቀኑ የሚደርሳቸዉን እሮሮ
እየሰሙ የመረጣቸዉን ሕዝብ በማገልገል ፋንታ የተለየ አጀንዳ እንዳላቸው ያሳያል፡
የቄሱን አቀጣጠር ባለፈው እትማችን ገልጸናል።
እኝሁ ቄስ ህዝቡን እንዲካፋፈሉ የተቀጠሩበትን ስራ እየሰሩ መሆኑን ለማንም ግልጽ ነዉ፡
እኝሁ ቄስ ”የአስተዳደር ቦርዶች እግሬ ላይ ዎድቀው ተማጥነዉኝ ነው እንጅ እኔ ለማገልገላል
ፍላጎት አልነበረኝም” ማለትም ማንነቴን አዉቀዉ ነው የቀጠሩኝ ማለታቸዉን ብዙ ሰው
ስምቶታል፡
ዪሄዉ ለቀ መንበር የማን አለብኝ ስራ እየሰራ መሆኑ ግለጽ ስለሆነ ከ ቦርዱ እንዲባረር መጠይቅ
የሁላችንም መብት መሆኑን አንዘንጋ።
ይሄው ሊቀ መንበር ካሁን ቀደም ካባረሩኝ፡”ይሄን ቤተ ክርስቲአን አዉድሜው ነው የምዎጣዉ
ማለቱን መዘንጋት የለብንም።
በሰላም ክዎጣም በኋላ የዎያኔ መንግስት ተጣሪ የሆነው ጓደኛዉ የኢትየፕያ መንግስት ደጋፊህ
ስለሆነ ተመለስ ብሎሃል ብሎ እንደመለሰዉ ለማንም ግልጽ ነዉ.
ከዎያኔ መንግስት ነጻ መሆናችንን ለማሳየት የምንችለው ይሄን ግለሰብ እስከጓደኛዉ በሰላም
ስናሰናብት ብቻ መሆኑን እዎቁ።
በሚቀጥለዉ እትም መልካም ዎሬ እንዲያሰማን እንጸልይ።

No comments:

Post a Comment