Friday, October 30, 2009

የሚወደኝ ህጌን ይጠብቃል ዮሓንስ 10፡15
ህዝበ ክርስቲያን ሆይ መቅደስ ሲደፈር ሰምተህ እንደት ዝም ትላልህ?
ቦርዱ መቅደስ ዉስጥ በመቋሚያና በመስቀል የሚማታ ካህን አቅፎ ይዟል።
ያስተዳድረኛል ብለህ የመረጥከዉ ቦርድ የቀጠረዉ ካህን ከታቦቱ ጋር እንድህ ሲዳፈር ሰምቶ
አንዳልሰማ፤ አይቶ እንዳላየ ፤ ይህን የድፍረት ሥራ ዉጦ ዝም ብሏል።
በዚህ ግለሰብ ላይ እርምጃ ከመዉሰድ ይልቅ ካአባ ፓዉሎስ ሰወች ጋር ቤተ ክርስቲያኑን አሳልፎ
ለመስጠት በሽምግልና ስም ክሚንቀሳቀሰዉ ቡድን ጋር እየተደራደረ ይገኛል።
ምእመናን ሆይ!
መቅደሳችን እንደ ፕሮቴስታንቶች ቤተ ክርስቲያን ባዶ አዳራሽ መሆኑ ነዉ ወይ?
ድብድብ የሚካሄድበት!
እግዚኦ! አግዚኦ! አምላክ ከዚህ ስውረን! ክቁጣዉ አድነን! ወደ ማን እንጮሃለን! ማንስ
ይሰማናል!
ያላባት እንድናመልክ ፈርደዉብን የእግዚአብሄርን ልጆች በተኑን!!
ይሄዉ ዛሬ ደግሞ መቅደስ ዉስጥ የሚደባደብ ካድሬ ለቀቁብን!!
መቸ ነዉ እነዚህን ጉዶች በቃችሁ የምትሉት!!
የሚወደኝ ህጌን ይጠብቃል አሜን!!!

No comments:

Post a Comment