Friday, October 30, 2009

በትናንትናው ቀን በሽምግልና ስም አይን ያወጣ ድርቅና!!!! ብለን መጻፋችን ይታወሳል!
ቦርዱ ይህን አንብቦ የስብሰባዉን ሰአት ለመለወጥና ህዝቡ ስብሰባዉን ገብቶ እንዳያዳምጥ
ለማድረግ እየተወያዩ መሆኑን ሰምተናል።
የሄ ቦርድ አይጥና ድመት ይመስል እዉነትን ክህዝቡ ለመደበቅ መሯሯጡን መቸ ያቆም ይሆን?
ለያንዳንዱ ሰዉ የተለያየ ወሬ በመፍጠርና በማሰራጨት ህዝቡን እርስ በራሱ እንዳይተማመንና
እንዳይቀራረብ ማድረግን የእለት ከእለት ዋና ተግባሩ እድርጎ ይዞ ቤተ ክርስቲያኑን ወደ ጥፋት
ጎዳና እየመራ ነዉ።
ከዚህ ይልቅ ህዝቡን ሰብስቦ ላደረሰዉ ጥፋት ይቅርታ መጠየቅና ንስሃ መግባት ይሻለዉ ነበር።
የክርስትና እምነታችንም የሚያዘዉ ይህንን ነዉ።
ቦርዱ ግን ክዚህ ይልቅ ካድሬ ይመስል እየዋሸ መሞትን መርጧል!!
ስለዚህ እኛ ምእመናን ይሄንን እየተከታተልን በስብሰባዉ መሳተፍ ይኖርብናል።

No comments:

Post a Comment