Tuesday, September 29, 2009

እግዜኦ!!! አግዚኦ!!!
አቡነ ቆስጦስን ዎደኛ ቤት ክርስቲያን አስመጥቶ ቤት ክርስቲያኑን ለማስረከብ ሙከራ ሲደረግ
ሆዳቸው አልጨክን ያላቸዉ የቤት ክርስቲያኑ ዎዳጆች እንዳከሸፉት ብዙዎቻችን እናስታዉሳለን።
የዳላስ ቤተ ክርስቲያንም አልቀበላቸዉ ሲል በ ዋሽንግቶን ዲሲ አካባቢ ሆነው ያአባ ፓዉሎስን
ትዕዛዝ በስራ ላይ ሲያዉሉ መክረማቸዉ የታዎቀ ነው። በዚህ ዎቅት እኝሁን አቡን የተቀበሉት የ
ድ.ሲ ቤት ክርስቲያን መሪ ( በነገራችን ላይ ዶክቶሩ የ ሊቀ መንበራችን የገል ጓደኛ ) የዎያኔ
መንግስት ፕሬዚደንት ሊያደርጋቸዉ ነዉ የሚል ዎሬ በመላው አሜሪካ ያስነፍሱ የነበሩት ዶክተር
ናቸዉ።
እንዳጋጣሚ በዚሁ ዎቅት የደንቨር ቤት ክርስቲያን ደግሞ ካህን ይፈልግ ነበር። እኝህ በአሁኑ ጊዜ
እኛ ጋ የተጠጉትና መስቀልን እግዚአብሄር የተሰቀለበት ማስታዎሻ ከመሆኑ ይለቅ አንደ አንድ
የማንም የስራ መቀጠሪያ ድፕሎማ ገትረው ዲፕሎማየ ነው የትም ሄጀ መቀጠሪያየ ነው የሚሉት
ቄስ እንዲቀጠሩ ይጠቆማሉ ። ዪህ ጥያቄ አዲስ አበባ በደረሰ ጊዜ የለምንም ማጣሪያ ባስቸኩዋይ
ያባ ፓዉሎስን እቅድ ለሟሟላት እንዲመች ዎደ አሜሪካን ይላካሉ።
የመቅጠር ፍላጎት የነበረዉ ቤተ ክርስቲያን ሚስጥሩን ስለደረሰበት ሃሳቡን ለዉጦ ሌላ ቄስ
ሲቀጥር እኝሁ ጉደኛው የእኛ ቄስ ከአቡነ ቆፕስጦስ ጋር በ ዋሽንግቶን ዲሲ ቤት ክርስቲያን
ተዳብለው ሲበጠብጡ ኖሩ።
አቡነ ቆስጦስ የዳላስን ቤተ ክርስቲያን መረከብ ህልማቸዉ ስለከሸፈ መዕመናኑን ሊበትንና
ሊከፋፍል ይችላል ብለው ያመኑበትን እኝህን ቄስ ከዎያኔ መንግስት ተስፈኛ ፕሬዚዳንት ጋር
በመሆን በቤተ ክርስቲያናችን የቦርድ ሊቀመንበር አማካኝነት አስቀጠሩ።
የሄዉም ሊቀመንበራችን እኝህን ሰው ካስቀጠረ ዶክተሩ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ አዲስ አበባ ሄዶ
የመንግስት ስራ ሊሰጠው ቃል እንደተገባለት ይህን ጉድ ያዎጣዉና ቤት ክርስቲያናችንን ከሽያጭ
ያዳነው ቡድን ገልጾታል።
እኝሁ ቄስ የተማመኑበትን ጋሻ ለማሳየት በየጊዝዉ በሚያሳዩት ተግባር እየገለጹ መሆኑ ለማንም
ድብቅ አይደለም።
ሁለት ጊዜ በተደረገዉ አጠቃላይ ጉባዔ ላይ ተነስተዉ መስቀላቸዉን ክፍ አድርገዉ ይዘዉ
እንጠቅሳለን (ይህን መስቀል እስከያዝኩ ድረስ የትም ሄጀ መስራት እችላለሁ) ብለዉ ደግመዉ
ደጋግመዉ ማስጠንቀቂያ ይሁን ዛቻ እንደነገሩን ሁላችንም ልብ ብለናል።
ይሄም የሚያሳየው የጨበጡት መስቀል ማዎናበጃ እንጅ እዉነት የክህነት ትምህርት አለመሆኑን
ነዉ። ዋና አላማቸዉ ህዝቡን ለመበታተን እንጅ እዉነትም የዕየሱስን ትምህርት ለማስተማር
እንዳልመጡ እየገለጹ መሆኑን ለዕናንተ ለመዕመናኑ እንድትረዱት ማድረግ አስፈላጊ
አይመስለንም የገዛ ስራቸዉ እየገለጠዉ ነዉ።
ፍትኅ ነገስት አንቀጽ 6 ቁጥር 210፦
ቄስ የእግዚአብሄር ሹም እንደመሆኑ ነዉር የሌለበት ይሆን ዘንድ ይገባዋልና፡ በራሱ ፍቃድ
የሚኖር አይሁን፡ ቂመኛ አብዝቶ የሚጠጣ ለመማታት እጁን የማያፈጥን አይሁን ያልታዘዘ
ትርፉን የሚዎድ አይሁን፡ እንግዳ መቀበልን የሚዎድ በጎ ስራን የሚዎድ ንጹህ ድንቀ ቸር የሆነ
ዎዘተ…
አንቀጽ 6 ቁጥር 224፦
የሃጢአተኛዉን ንስሃ የማይቀበል ዎይም በነገር ሠሪነት ሃሰትን በመመስከር የሚታበይ ሕግን
አዉቆ የማይሰራበት ክፉ ስራንም የሚያዘዎትር በጎ አለመስራትን የዎደደ ዎይም አለቃዉ
ሳይፈቅድለት ዎደ ንጉሥ የሚሄድ ቄስ ይሻር።
አንቀጽ 6 ቁጥር 234፦
በነገረ ሥራ አይመስክሩ ሰዉንም ለማክሰስ ዎደ ንⷝስ አይሂዱ፡ ሓሜተኞች አይሁኑ። ለመዕመናን
ክፋትን አይዉደዱ። ከነርሱ ዎገን ይህን ያደረገ ከሹመቱ ይሻር ዎዘተ…….
ቤተ ክርስቲያናችን ይህን መጽኅፍ የምትቀበል ከሆነ የእኛ ሁለቱ ቄሶች መቅደስ ዉስጥ ገብተዉ
መቀደስ ይችላሉ ዎይ?
ዎይስ የአስተዳደሩን ሥራዓት እንዳጣመምነው ዎደ መቅደሱም ችግሩን አስገብተን እያፌዝን
ነው።
ዋና ደጋፊአያቸዉ ያሁኑ ልቀ መምበር የመዕመናኑን መብት እየረገጠ የዎደፊት አገር ዉስጥ ገብቶ
ሊሾም መንገዱን እየጠረገ መሆኑን በግብር እያሳየ ነዉ።
ደግመን ደጋግመን ንስሃ እንዲገባ መለመናችንን አሁንም አንተዉም።
እሱ ግን ከቀን ዎደ ቀን በሚያሳየዉ ተግባር እየባሰበት መምጣቱንና አልፎ ተርፎ ከ ከሳሾቻችን
ገር በጥቅም እየተዋቀረ መሆኑን አጥብቀን መቆጣጠር ይኖርብናል።
በሚቀጥለዉ እትም ከከሳሾች ጋር የሚያደርገዉን ግኑኝነት እናበስራለን።

No comments:

Post a Comment