Sunday, September 6, 2009

ዉድ የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ምእመናን፡
ባለፈዉ እትማችን ላይ አስተያየታችሁን ስጡን ብለን መጠየቃችንን እያስታዎስን
እንዳሰብነዉም ባይሆን ጥቂቶቻችሁ ያደረግነዉን አዳንድ የቀለም ስህተት እና የግል ጥላቻ
ያደረብን መሆኑን ገልጻችሗል።
ለማእመናኑ ለመግለጽ የምንፈልገው
አንደኛ፡
የኮምፒተርም ይሁን የመጻፍ ልምምድ የለንም፡ የቤተክርስቲያናችን ሁኔታ በጣም
ስላሳሰበንና መንገዱም ስላላማረን በተቻለን መጠን ዎደ መልካም መንገድ እንዲመለስልንና
እንደዱሮአችን ለጸሎት ስንገናኝ ተሳስመን ተሳስቀን አብረን በልተን ጠጥተን እስከሚመጣዉ
ጊዘ ጤና ይስጥለን ተባብለን እንድንለያይ ነዉ።
ከዛሬ አራት አመት ጀምሮ የሆነዉን ሁላችሁም ታዉቁታላችሁ። ቤታችንን ሰብሮ ገብቶ
ያበጣበጠንን በግለጽ ዓይናችን እያየ የዘረፈንን (ፓራሳይት) ለማባረር አስበን ነው።
ስለዚህ የቆሳቁስ ስህተቶቻችንን ታገሱና እለፉን።
ሁለተኛ፡
ከአቶ እዩኤልም ሆነ ከለሎቹ ጠብም ትዉዉቅም የለንም። አቶ እዩኤልን የምናዉቀው
እቤቱ ቁማር ስንጫዎት ማደራችንን እና የብዙዎቻችን ቤት ማፍረሱን ነው፡ ዋናዉ
ሃሳባችን፡ ማህበረ ቅዱሳን የተባለ የሰይጣን ተላላኪ ለነፍሱም ሆነ ለስጋዉ ልክ እንደ ቁማር
ማጫዎቱ የማይጠቅመዉ መሆኑን እንዲረዳ እና እነሱን ትቶ ዎደ መልካም ተግባር እንዲመለስልን
በማሰብ ነው።
(እንደምናውቀው የቅዱስ ሚካኤል ወፍጮ ጊዜዉን ጠብቆ ጠላቶቹንና የሚበዘብዙትን
እንድሚፈጭ አንጠራጠርም፡ ጊዜውንም ስለዎሰደ ያልፋቸዋል ማለት አለመሆኑን ይረዱ)
መመለሳቸዉንም የምናዉቀዉ ባስቸኩዋይ ቦርድ የቤተክርስቲያኑን አባላት ሰብስቦ ጥር ሰላሳ
አንድ ቀን ያሳለፉትን አዋጅ በስራ ላይ እንድዉል ሲደረግ ነዉ።
የፈሰሰ ዎሃ ተመልሶ እንደማይታፈሥ ስለምናዉቅ፡ የሂሳቡን የኦዲት ዉጤት ለኛ ማቅረብ በቦርዱ
ላይ የባሰ ሃሜትና መሳለቂያ መሆን እንጅ ምንም ፋይዳ እንደማያተርፍ አሁን ያለው ቦርድ
እንዲያዉቁት እንፈልጋለን።
ይህም ምክንያት ሆኖ ጊዜ የሚያራዝምበት ጉዳይ አይታየንም፡
እስክ እዚህ ዎር መሃከል ድረስ አንድ ዉጤት ካላገኘን ግን ትግላችንን እንደምንቀጥልና ይኽን
መልእክትና ሌሎችንም የተጨበጡ ማስረጃዎች እያቅረብን በእትም ብቻ ሳይሆን በድምጽ ማንበብ
ለማይዎደው ምእመናን እንደምንበትን እወቁለን።
ምእመኑን እንዲያዎናብዱ የምትልክዋቸው ግብረ አበሮቻችሁ ተሰብስበው ቤተክርስቲያናችን
ሊዎሰድ ነዉ ሊከሰስ ነው እያሉ ሃሰት የሆነ ዎሬ ማዉራታቸዉንም እናዉቃለን፡ ሁለት አይነት
ጸጉር ያበቀለ አዛዉንት እንዴት ያልሆነ ዎሬ ያዎራል እያልን እንደነቃለን።
አሁን ላላችሁት ቦርድ አባላት የምናሳስበው ባስቸክዋይ ኦዲት አስደርጉ ብሎ የመከራቹሁ እና ኦ
ዲተር ያቀረበላችሁ ግለሰብ ሊያዋርዳችሁ እንጅ ሊጠቅማችሁ እንዳልሆነ ተገንዘቡ ማንም
እንደሆነ ከነታሪኩ ከዚህ ዎር ግማሽ በኃላ በምናደርገው እትምና ድምጽ እናዎጣለን፣
ልዩ መልእክት፡ ላቶ እዩኤልና አሁን ላላችሁት የቦርድ አባላት.፤
እኛ ካንተ ጋርና ከሞላ ቦርድ አባላት ጋ ምንም ጠብ እንደሌለን አስቀድመህ እዎቅልን የኛ ዋናው
ጠባችን ከማህበረ ቅዱሳን ጋር አብረህ የምትዶልትበት ምክንያት ነው። ለምሳሌ ያህል ባለፈው
ዎር ከከሳሾቻችን ጋር በድብቅ ተገናኝተህ የተስማማኸዉን ስምምነት ተነግሮናል እንዲያዉም ማን
አለብኝ ብለህ ጨለማ ለብሰህ የቤተክርስቲያን በር ከፍተህ አስገብተህ ዉጭ በር ላይ ቆመህ
ጥበቃ ማድረግህን በአይናችን አይተናል.፡
እንዲሁም በይፋ የቤተክርስቲያን ከሳሾች የገንዘብ መሰብሰቢያ ወረቀት እያዞሩ ሲያድሉና
ሲያሳድሉ እያየህ ዝም ማለትህ የሚያሳፍር ተግባር ነው። ይህ ድርጊት አንተ ላይ ብቻ ሳይሆን
በመላው ቦርድ ላይ እንደሚያርፍ ቦርድ አባል የሆናችሁ ተረዱ።
በተጨማሪም ከዕግዚአብሄር ጋ የተላኩልን የቅዱስ ሚካዒል ቄስ እና የቦርዱ ዋና ጸሃፊ ባሉበት
አገር እያቁዋረጡ የሚመጡት የዎያኔና ያባ ፓዉሎስ ተዎካይ በግለጽ ድቪድ እና ጥብቆ ሲሸጡ
ዝም ብለው ሲያዩ እንደነበረ ሰምተናል፡
ይህም ዋና ጸሃፊ አስቆምኩዋቸው ማለቱን ሰምተናል፣ሸጠው ሲጨርሱ ማስቆምና ዎዲያው እንዳየ
ፖሊስ ጠርቶ ማስነጠቅ ተግባሩ እንደነበረ የዘነጋው ይመስላል፡
ምዕመናን ሆይ እኛንና እንደናንተ ያለዉን የ ማህበረ ቅዱሳን ደጋፊ ያልሆነዉን ይሀዉ ጸሃፊ ይሄን
ስራ ሰንሰራ ቢያይ እንደሚያሳስረን አትጠራጠሩ፤
አንዱ የቦርድ አባል የሚያደርገው ሃጤአት ሁላችሁንም የቦርድ አባላት እንደሚያስዎቅስ
እንድታዉቁለን እንፈልጋለን።
እባካችሁ ለኛም ለነብሳችሁም፤ ማህበረ ቅዱሳን ሳይሆን በብዛት ለመረጣችሁ መምእመናን ስትሉ
የተመረጣችሁበትን ዋና አላማ አድርጋችሁ እኛ ምእመናኑ ደስ ብሎን ቅዳሴ ልቡን
ለእግዚአብሔር የሰጠ ቄስ (ባለፈው ስብሰባላይ ላይ ከልብ የሆነ ምስጋና በቅን ልቦናችሁ
ያፈሰሳችሁለት) አይነት ቄስ ፈልጋችሁ አምጡለን እንላለን።
በግልጽ ማህበረ ቅዱሳን መሆኑን አያሳየ በስድስት ዎር የቅስና ሹመት የተሰጠዉና መቅደስ ዉስጥ
ገብቶ የሚያበጣብጠዉን ቄስና ደጋፊዉን ዘባራቂ የእግዚአብሄር መልዕክተኛ አዎናባጅ
አስዎግዱልን እንላለን።
የጠየቅነው ጥያቄ እንዲፈጸምለን ለዓምላክ ከፍተኛ ጸሎት እናቀርባለን!!! ጸሎታችንንም
እንደሚሰማን አንጠራጠርም።
እስከተፈጸመልንም ድረስ በሰላም እንሰናበታችሁዋለን።
መልካም በአል ያድርግልን።
ደህና ሰንብቱ ብለን እዚህ ላይ እንዘጋለን።

No comments:

Post a Comment