Friday, September 25, 2009

የሽማግሌን ኮሚቴ በአዲስ መልክ ለማዋቀር ጅምሩ ቀጥሏል!!!!!
የአስተዳደር ቦርድ የአማካሪ ኮሚቴ ብሎ ይጠራቸዋል፡ ህዝቡ ደግሞ የሽማግሌዎች ኮሚቴ ብሎ
ይላቸዋል። እንደት እንደተሰባሰቡ አልፈዉ ተርፈዉ ስማቸዉ ተሻሽሎ የቤተ ክርስቲያን ቋሚ
ኮሚቴ ለመሆን መብቃታቸዉን ሁላችሁም የምታዉቁት ታሪክ ነው።
ይህ በቋሚነት አገልግሎት መስጠት ላይ ያለው ኮሚቴ ክተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ያስገኘዉ ተጨባጭ
የስራ ዉጤት ምን ይሆን? የቤተ ክርስቲያናችንን ችግር ለመፍታት በተደረገዉ ጥረት ዚሁ
ኮሚቴ ድርሻ ምን ነበር?
ዎይስ ካሉን ችግሮች መሃል አንድ ዋናዉ ይሆን?
ለነዚህ ጥያቄዎችና እነማን እንደሆኑ እስከ ሽፍን አላማቸው ጋር ትንታኔ በዎቅቱ ዎደፊት
እናቀርባለን።
ለዛሬ ልንገልጽላችሁ የምንመኘዉ በማህበረ ቅዱሳንና በአባ ጳዉሎስ ተዎካዮች አማካኝነት
ተመርጦ በሽምግልና ስም ቤተ ክርስቲያናችን ዉስጥ መንቀሳቀስ ስለጀመረው ቡድን ይሆናል።
ይህ ቡድን ከአባ ፓዉሎስ ልዩ መልክተኛ ከ ንቡረእድ ጋር በማህበረ ቅዱሳን አማካኝነት
ተገናኝቶ በሽምግለና ስም እንዲቀሳቀስ ከተመረጠበት (August 18 2009) ዓ. ም ጀምሮ
እኛ እስከምናዉቀዉ ድረስ አራት ስብሰባዎች ሲያደርግ ሁለትን ያደረገዉ ከአስተደር ቦርዱ ጋር
ነው፡ ከላይ የተጠቀሱት ስብባዎች ሂደት እንደሚጠቁመዉ ዎደፊት ቋሚ የሽማግሌዎች ኮሚቴ
አባላት ለመሆን እየታጩ መሆኑን ይጠቁማል።
ከ ሰላሣ በላይ የሆን ማህበርተኞች የአስተዳደር ቦርዱን ለማነጋገር እንፈልጋለን ብለን በደብዳቤ
ብንጠይቅ ጥያቂአችንን ላለመቀበል የተለያየ ምክንያት በመፍጠር እንዲጓተት ተደርጓል፡
ሕዝቡን ቀርቦ ማነጋገር ያስፈራቸዉ ለምን የሆን?
ከላይ የተጠቀሰው የሽማግሌ ቡድን ግን የለፈው ቅዳሜ ማታ በስልክ ስብሰባ ጠይቀው ሰኞ ምሽት
ከቦርዱ ጋር መሰብሰባቸዉን እናዉቃለን።
በዚህ የአሰራር ልምድ ስለ ቦርዱ ለመገንዘብ የቻልነዉ ፦
የቤተ ክርስቲያኑ መዕመናን የመረጠዉ ቦርድ የተመረጠበትን አላማ ስቶ ለጥቅም ብቻ
እንደሚተዳደርና የመዕመናኑን ጉዳይ እና እሮሮ አልሰማም አሻፈረኝ እንደፈለጋቸዉ
ይሰደቡ!!ይሰዳደቡ!!! የት ይደርሳሉ?
የሚል አቋም እንዳለው ነው፡
የመረጠዉ መዕመናን ጋር ከሚገናኝ ይልቅ አባ ፓዉሎስ ከላኩት መለክተኛ ጋር መገናኘቱን
ለምን መረጠ ይሆን?
በኛ አስተሳሰብ ቦርዱ ከማህበረ ቅዱሳንና ካባ ፓዉሎስ በሚሰጠዉ መመሪያ እንደሚንቀሳቀስ ይፋ
ማዉጣቱን እያረጋገጠ መሁኑን ያስረዳናል።
እግዜር ቸር ዎሬ የምንሰማበትን ቀን ያቅርብለን።
በሚቀጥለው እትም ስለ ቀሳውስቱና በምን ዘዴ እንተቀጠሩልንና መስቀልን የጌታ እየሱስ ክርስቶስ
ምልክት መሆኑ ቀርቶ ማስፈራሪያ መደረጉን እንገልጽላችኋለን።

No comments:

Post a Comment