Wednesday, September 23, 2009

የእዉነት ያለህ
ቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተሰነዘረው ጥቃት የተቀነባበረው በኢሃድግ መንግስት
ነው፡
በደካማ ጎናችን ገብቶ እያጠቃንም ነው፡ ይሕም ሊሆን የቻለው አስተዳደሩ ስራት
ያለምንም ማዕቀብና ቁጥጥር የተዋቀረ በመሆኑ ነው፡ በዚህም ምክንያት ከዉስጥና
ክዉጭ የተሞከረውን አደጋ መቋቋም አቅቶት ሲንገዳገድ ይታያል።
ባለፉት 19 አመታት የተከትልነው አስተዳደራዊ አስራር ተንዶ ለፍርድ ሸንጎ
ዳርጎናል።
ዎደፊት ለመጓዝና ይህን ብልሹ አስተዳደር ለመለዎጥ መፍትሄው፡ ግልጥ! ያለ
የአስዳደር (ትራንስፓረንሲ) ያለው አሰራር መዘርጋት ነው።
የህም ግልጥ አሰራር በሂሳብ መዝገብ አያያዛችን መጀመር አለበት የሚል ሃሳብና
ዕቅዱ ላስተዳደር ቦርዱ ቀረበ። ቦርዱ ግን ይህ የአሰራር ዘዴ ከቀረበለት ቀን ጀምሮ
ይህን እቅድ መቃዎሙን ተቀዳሚ ስራው አደረገ። ይባስ ብሎም ሃሳቡን ያቀረቡ
አባላትን ስም እየጠሩ ስራ አላሰራ አሉን በማለት የስም ማጥፋት ዘመቻን ስራየ
ብለው ተያያዙ። ለምን?
በ2007 ዓ.ም በበጎ አድራጎት ኮሚቲ አማካኝነት ዎጭ የሆነውንና እስከ ዛሪ ድረስ
ይህ ኮሚቲ ደረሰኝ ሊያቀርብበት ያልቻለውን ሰነዶች በ2008 ዓ.ም ላይ
ለመዕመናኑ መበተኑ ይታዎሳል። በዚህ ሰነድ ላይ ስማቸዉ የተዘረዘረው ግል ሰቦች
በሙሉ የዎሰዱትን ገንዘብ አባከኑት ተብሎ ክስ አልቀረበም? ይልቁንም የሰነዱ
መሰራጨት ዋና አላማ የነበረው ማህበረ ቅዱሳን በስሩ የሚተዳደሩ ቤተ
ክርስቲያናትና የራሱን የግል ስራ ለማስፈጸም በአንድ አመት ውስጥ ብቻ ስንት ብር
አንደዎሰደ ለማሳየት የተደረገ ሙከራ ነበር። ዓላማዉ በብዙ ዉጣ ዉረድ ግቡን
ሊመታ ችሏል፡ በዓንጻሩም የህ ሰነድ ዛሬ ይፋ ሆኖ ለመጣዉ ችግር ምክንያት
ሆኗል።
የአስተዳደር ቦርዱ በየሶስት ዓመቱ በሂሳብ አጣሪ (CPA) አስመርምሮ ለመዕመናኑ
የሚያሳዉቀዉን የሂሳብ ዝርዝር (ኦዲት) ማቅረብ ያቃተዉ በዚህ ለሕዝብ
በተበተንዉ ሰነድ ምክንያት ነው።
የኦዲተሩ አቀጣጠር ከመተዳደሪያ ደንቡ ዉጭ ያለምንም ጨረታ በትዉዉቅ መጥቶ
የተቀጠረ ሂሳብ ተቆጣጣሪ ነዉ። ይሄው ተቆጣጣሪ ቀደም ሲል ለቤተ ክርስቲያኑ
ተመሳሳይ አገልግሎት መስጠቱ አይዘነጋም። የሂሳብን መዝገቡ እንደምንፈልገው
በማቀነባበር አቅርብልን (COOK THE BOOK) ማለትም ዋሽልን ተብሎ ሴጠየቅ?
ሳያመነታ የደንበኞቹን ፍላጎት እንጅ የጠራ የሂሳብ የመቆጣጠር ስራ የሰራ
እይደለም።
ይኄዉ ግለስብ ባለፈዉ የአስተዳደር ቦርድ የዎጭ ሰነዶችን ደምረህ በምታገኘዉ
ቅምር ሂሳቡ እንደተዎራረደ አድርገህ አቅርብልን ብለው ቀጥረዉ እንደተጠየቀዉ
ሰርቶ በማቅረብ ኦዲት በ (C P A) ተደረገ ምንም የጎደለ ሂሳብ የለም ተብሎ
በጭብጨባ ሪፖርቱን መዕመናኑ እንዲቀበል ተደርጎ በሽፍንፍን መታለፉን
ሁላችንም እናውቃለን።
የዛሬዉም ቦርድ ይህንኑ አሰራር ለመድገም ቀና ደፋ ሲል ተደርሶበት፡ የለም ይህ
አሰራር ዖዲት ሳይሆን የዎጭ አጠቃላይ ድምር ዉጤት ነው ሲባል ልስራው
መጓተት ምክንያት ሆነ።
ዉድ መዕመናን አንድ ሰነድ ይህን ያህል የሰዉ ዓይን ክገለጸ ዎደ ኋላ የ አስር
ዓመት ሂሳብ ዖዲት ይደረግ ቢባል ዉጤቱ ምን የሚሆን ይመስላችኋል?
እኛ አባላቱ ይህን የመጠየቅ መብት የለንም ይሆን? ዎይስ ጥቅማቸዉ የተነካ
የዘራፊዎች ቡድን እንደሚያሰራጩት ዎሬ ይህን “ የፍሚጠይቁና የሚጽፉ የኛ
ሰዎች አይደሉም “ እየተባለ የኛ ሰዎች አይናቸዉን የከፈቱ አይደሉም
“ያደረግነውን ብናደርጋቸዉ የኛ የሆኑ አይቃዎሙንም” ገንዘባችንና አቅማችንን
አዋጥተን የጀመርነውን ቤት ክርስቲያን መበዝበዝ ቀርቶ መሸጥም እንችላለን እያሉ
ስለሚፎክሩ ከበይ ክፍል ያልሆነ ሁሉ የነሱ ሰዉ አይደለም ለማለት ይሆን?
እንድታዉቁልን የምንፈልገው እኛ አንዳዶቻችን ይሄ ዲርጊት በዛ ይቅር ሳያዋርደን
እናቁመዉና ዎደ መልካም ተግባር እንመለስ የምንል ነን ይሄንንም ያደረግነው
እናንተን ዘመዶቻችንና ጓደኞቻችን ትለቅ የሃፍረት ካባ እንዳትጎናጸፉ ነዉ።
በዚሁ ማስታዎሻ አማካይነት ግለጥ (ትራንስፓረንሲ) አሰራርን አብዛኛቹ የቦርድ
አስተዳደር አባላት የቀድሞዎቹም ሆኑ አሁን ያሉትና ደጋፊዎቻቸዉ ሽንጣቸዉን
ገትረው እየተቃዎሙ መሆናቸዉን እንድታዉቁ ለናንተ ለመዕመናኑ ማስረዳቱ ተገቢ
ነው፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት እንደ ድሮው እንደፈለግን እናደርጋለን እንጅ
ማንም እንዲቆጣጠረን አንፈልግም፡ አንዳንድ እነዙህ የኛን ሰዎች የሚነካ ጥያቄ
ሲነሳ አፍንጫ ሲነካ ዓይን ያለቅሳል እንደተባለው እኛዉ በኛዉ ተጠራርተን
እናፈርሰዋለን እንጅ ከ ዱሮው አሰራር አንዎጣም፡ ዘላለም እንደበዘበዝን አንኖራለን
እንደሚሉ ነዉ።
በሚቀጥለው እስትንገናኝ ደህና ሁኑልን።
ዎስብሃት ለዓምላክ።

No comments:

Post a Comment