Thursday, September 10, 2009

አልሞት ባይ ትጋዳይ።

የ ቦርድ አባሎቻችን በየቀኑ የምናስተላልፈዉን ጥያቄ በስራ ላይ ላለማዋል የሚያደርጉትን ጥረት በይፋ እያስታዎቁን መሆኑን ለናንተ ለምዕመናኑ ለንገልጽ እንፈልጋለን።
ጧትና ማታ ቤተ ክርስቲያናችንን አይናችን እያየ አብረው ካንዳንድ የቦርድ አባላት ጋር ሆነው የዘረፉንን እና በቤተክርስቲያናችን ዉስጥ እያሞለጩ የሚሰድቡንን (ፓራሳይት) አስዎግዱልን እያልናቸዉ እንዲያዉም ማን አለብን ብለው እነዚሁ ዘራፊዎች ዎር ተለዉጦ ሌላ ዎር ሲጀመር
የምንከፍተዉን የዎር መቁጠሪያ በገለጥን ቁጥር እያየን ሆዳችን እንዲቆስል፡ሊለጠፍ የሚገባዉ ስንት የቤት ክርስቲያን ምስል እያለ የማህበረ ቅዱሳንን የዘማሪ ምስል ለጥፈው ለመዕመናኑ መሸጣችዉን ልብ ብለን አይተናል።

ይሕንንም የቅሌት ስራ የፈጸመችው የቦርድ አባል ባስቸኩዋይ ህዝቡን ሰብስባ ይቅርታ በፍመጠየቅ የቸረቸረችዉን የቀን መቁጠሪያ ሰብስባ ሌላ ቤተ ክርስቲያኑን የሚዎክል የቀን መቁጠሪያ አሳትማ ለከፈሉት ሁሉ እንድታድል እንጠይቃለን።
ተሳዳቢ የዎያኔ ቄስ ከማስመጣትዋም በላይ ባለፈው ጊዜ እየተነገራት የማህበረ ቅዱሳን ዋና ተዎካይ የሆነ የስድስት ዎር ቄስ ቤተ ክርስቲያናችን ዉስጥ መጥቶ እንዲያስተምር አድርጋለች፡

በትላንትናዉም የቤተ ክርስቲያናችን ክስ ለከሳሾቻችን የተፈረደላቸዉን ፊርድ በሚመለከት የአባላት ስም ዝርዝር እንዲሰጥ ስለተደረገ መደሰቷን ደርሰንበታል።
ይህችም ዎይዘሮ ከበላይ ሆኖ የቦርድ አባላትን ዎደ ሸር መንገድ እንዲጓዙ የሚመራ ባለቤቷ ጋር
የጠነሰሱት መሆኑን በግለጽ ተረድተናል፡

ተጨባጭ የሆኑ ማስረጃዎችንም ከያዝነው ዎር አጋማሽ በኋላ በምናቀርባቸዉ አትሞችና የድምጽ ሲዲዎች እናቀርብላችኋለን፡
የሄ ሁሉ የቦርድ አባሎች ጥፋታቸዉን አዉቀው ንስሃ ክገቡ ማጋለጣችንን እናቆማለን ብለናል እስክዚያ ድረስ ግን አሁንም የቦርድ አባላት ሁሉ ዎደ መልካም ተግባር እንዲመለሱ እንጸልይላቸው!!!!!!።

No comments:

Post a Comment