Friday, June 11, 2010

ቤተክርስቲያናችን ወደት እየሄደች ነው?
ይህንን ጥያቄ የጠየቁት ወ/ሮ አዜብ ኅይለማርያም ናቸው። ወ/ሮ ፈትለወርቅ ጎላ በምርጫ በተሸነፉበት ጌዜ ለወዳጆቻቸው በሙሉ ያቀረቡት ጥያቄ ነበር። ጊዜም ሳያጠፉ በምርጫው ከተሸነፍን አበራን እና ዶ/ር ግርማን ሌባ ብለን ወንጅለን ህዝቡን በማስቆጣት አነሳስተን ያቀረቡትን ሪፖርት እንኳን ለምእመኑ ሳያቀርቡ ለማባረር ተብሎ በተቀነባበረው ሴራ ውስጥ ያጣሪ ኮሚቴ ሆነው ገቡ። በዚህ ኮሚቴ ውስጥም አቶ ኪዳኔ ምስክር አብሯቸው እንዲገቡ የጠቆሙት እኝህ ወ/ሮ ነበሩ። አቶ ኪዳኔ ምስክር ከባለቤታቸው ከወ/ሮ ጥሩአየር ፍስሃ ጋር ቤተክርስቲያንን የከሰሱ፤ የዲያቆን አለማየሁ አጎትና የቦርድ አባል በነበሩበት ወቅት ወደ ሃያ ሽህ የሚጠጋ ብር ከቤተክርስቲያኑን የዘረፉ ናቸው።
ወ/ሮ አዜብና አቶ እዮኤል ነጋ አዴስ የተመረጡትን የቦርድ አባላት የተተራመሰውን ቦርድ መስመር እስከምናሲዝ ድረስ ስራቸውን እንዳይጀምሩና የድሮዎቹ እንዳሉ እንዲቀጥሉ ለማድረግ ያደረጉትን ጥረት ማን ይዘነጋዋል? ጥረታቸው መክሸፉን ሁላቸንም ያየነው ጉዳይ ነው።
ቄስ ነኝ የሚለው አወቀ ሲደልል በሰራው ሃጢያት ከቤተ ክርስቲያን ሲባረር ቤተክርስቲያን ላይ ሁከት የፈጠረው ቡድን
1  የወያኔ ድርጅት መስራች የሆኑት ያቦ ጸሃየ ቤተሰብና የሟቹ የትግራይ ልማት ድርጅት ሃላፊ እህቶች
 ሀ   ወ/ሮ  የሽ ዘሪሁን
 ለ   ወ/ሮ  ሶፊያ ዘሪሁን
2     የወያኔው መሪ  የአቶ መለስ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ጎላ ቤተሰቦች
ሀ    ወ/ሮ   አዜብ ኅይለማርያም
ለ    አቶ   ጌታቸው ትርፌ
3   ማህበረ ቅዱሳን
4    የወያኔ አባላት እና ደጋፊወች እንደነበሩ ሁላችንም እናስታውሳለን።
ሚካኤል በጥበቡ ይህንን ደባ ሲያከሽፍ ወደ ፍርድ ሸንጎ ተሯሩጠው ነጎዱ። በየቦታውም ጸረ ቤተክርስቲያን ስብሰባወች አካሄዱ። ቤተክርስቲያን የማዘጋት ህልማቸውም ከሸፈ።
ወ/ሮ  አዜብ ግን ትግላቸውን በመቀጠል
1    አቶ   እዮኤል ነጋ   ከእግዚአብሄር ቤት በገዛ ፍቃዱ የኮበለለ፤
2    ወ/ሮ  ፈትለወርቅ ጎላ፤
3    አቶ  ሃይሉ አራጋው   በውሸት ብዛት ምላሳቸው የተቆለፈ፤ በቴፕ ሲቀዱ የነበረውን የቤተክርስቲያን ሰነድ እስከዛሬ ያላስረከቡ፤
4    ሻምበል  ግዛው ገድሉ   ከማህበረ ቅዱሳን ጋር በመሆን ብዙ መቶ ሽህ ብር በላይ ቤተክርስቲያኒቱን ያራቆተ፤
5    አቶ   ኪዳኔ ምስክር  ከባለቤታቸው ጋር የቤተክርስቲያን ከሳሽና ብዙ ገንዘብ ያባከኑ፤
6    አቶ ጌታቸው ትርፌ   ከቀድሞው ቦርድ ጀርባ በመሆን ለደረሰው ጥፋት ሁሉ ግንባር ቀደም አማካሪና አስተባባሪ። ሃሰተኛ ኦዲተር ለቦርድ አቅራቢ፤
7   ሻለቃ ተፈራወርቅ   ቤተክርስቲያኑን የሚከሱና የሚወነጅሉ ሽማግሌዎች ነን የሚሉ ያባ ጳዉሎስ ተወካዮች ግንባር ቀደም አስተባባሪ። አሁንም እንሸመግላለን ስብሰባ ለማድረግ ፐቲሸን አለኝ ብለው ማቅረብ አቅቷቸው June 27 ስብሰባ የጠሩ በዛ ላይ የሚገኘውን ሰው ስም ዝርዝር  ይዘው ለመቅረብ በዝግጀት ላይ ያሉ፤
8   አቶ በትሩ  ቤተክርስቲያኑን የሚከሱና የሚወነጅሉ ሽማግሌዎች ነን የሚሉ ያባ ጳዉሎስ ተወካዮች ጋር የሚዶልቱ፤
ለአብነት ስማቸው ከላይ የተጠቀሱትን ግለሰቦች ከነባለቤቶቻቸው በማስተባበር በህግ የተቋቋመውን ቦርድ አዉርደው ሌላ ቦርድ ለመመስረት በመሯሯጥ ላይ ይገኛሉ።
የመሪነቱን ቦታ አንለቅም ተብሎ ይሄ ሁሉ ትግልና መሰሪነት የሚካሄደው እውነት  ለቤተክርስቲያን ደህንነት ታስቦ ይሆን ወይስ ሌላ የተሸፈነ አጀንዳ ይኖር ይሆን? እና ወ/ሮ አዜብ ቤተክርስትያናችንን ወዴት እየወሰዱት ነው?
መልሱን ለናንተ ለውድ ቤተክርስቲያን ወዳጆች እንተዋለን።
አምላካችን ለቤተክርስቲያናቸን የሚበጀውን ተግባር ይለግሰን አያልን ጸሎታችንን አናቀርባለን።
አምላክ በቸርነቱ ከዚህ ሁሉ ፈተና ያድነን።
ሁላቸንንም ለንስሃ ያብቃን
አሜን! አሚን1 አንበል!!!!!

1 comment: