Wednesday, January 19, 2011

እንደምን ከረማችሁ?

ቤተክርስቲያናችንን ከቀበሌ የፍርድ ሸንጎ ወደ ተቀደሰ ደብር ለመለወጥ የተደረገው ጉዞ መልክ እየያዘ መምጣቱ በልዑል አምላካችን ፈቃድና በምእመናኑ ንቁ ተሳትፎ የተገኘ ድል ስለሆነ ሁላችንንም እንኳን ደስ ያለን እንላለን። ስውርና አሳፋሪ የሆነውን ነገር አስወግደናል። በተንኮልም አንሰራም፤ የእግዚአብሔርንም ቃል ከውሸት ጋር አንቀይጥም፤ ይልቅስ እውነትን በይፋ እናስያለን፤ እራሳችንንም በሰው ሁሉ ህሊና ግልፅ እያደረግን በእግዞአብሔር ፊት እንኖራለን።
2ኛ ቆሮንጦስ ቁጥር 4:2 ።
ባለፈው ጽሁፋችን ላይ የቤተክርስቲያናችንን ችግሮች በመጠኑ ለመጠቆም ሙከራ አድርገን ነበር። ችግሮችን ሙሉ በሙሉ ለመፍታት ብቃቱም ሆነ ሥልጣኑ ስለሌለን በዚህች በእኛ ደብር ውስጥ እውነትን በይፋ እያሳየን የእግዚአብሔርንም ቃል ከውሸት ጋር ሳንቀይጥ በፊቱ ለመኖር ቆርጠን ስንነሳ በተቃራኒ ጎራ የነበረውን የሃይል አሰላለፍ አሳውቀናችኋል። ችግሮችን ለመፍታትና ለቤተክርስቲያናችን እድገትን ለማምጣት አስተዋጽኦ ለማድረግ የሚቻለው ግልጽ አሰራር (Transparency) እንዲኖር በማድረግ ነው ብለን ተስማማን።ይህንንም ሃሳብ ከግቡ ለማድረስ አስፈላጊ ናቸው ብለን ያመንባቸውን ነጥቦች በወቅቱ ለነበሩት የአስተዳደር ቦርድ አባላት አቀርብን፤ ከነጥቦቹም ጥቂቶቹ ይሚከተሉት ነበሩ።
1 የቤተክርስቲያኑ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ኋላ ቀር አሰራር ስለሆነ ብዙ ገንዘብ ሲባክን በወቅቱ ለመጠቆምና ለማስተካከል ብቃት አልነበረውም። ስለሆነም በዘመናዊ (Software) ተጠቅመን ማህበርተኛው (On line) በመግባት ወርሃዊ ክፍያውን እንዲከፍል እድል አንዲሰጠውና ያለውንም የገንዘብ እንቅስቃሴ እንዲያይ እንዲደረግ።
2 ማንኛውም የጥገናም ሆነ የቆሳቁስ የግዥ ስምምነት ሲደረግ የአስተዳደር ቦርዱ ህጋዊ ጨረታ እንዲያወጣ፤ አሸናፊ ኩባንያም አሸንፎ የሰራበትን ሰነድ ተቀብሎ ለምእመኑ ባለው የመገናኛ ዘደ ሁሉ እንዲያሳውቅ።
3 የአስተዳደር ቦርዱ ሊቀመንበር የቤተክርስቲያኑን የተለያዩ ኮሚቴወችንና የስራ ዘርፎችን ማስተባበርና መርዳት ካልሆነ በስተቀር ፍጹማዊ የሆነ በግል የፈለገውን የማስፈጸም መብት እንደሌለው እንዲታወቅ።
4 ካህን፤ አስተማሪ፤ ለሌሎችም ክፍት የስራ ቦታዎች ሠራተኛ መቅጠር ቢያስፈልግ፤ “የቅጥር ጊዜያዊ ኮሚቴ” ተቋቁሞ በሚሰጠው ዝርዝር የስራ መመሪያ መሰረት ሶስት እጩወች ለቦርዱ አቅርቦ እንዲቀጠር። 
5 የአስተዳደር ቦርዱ መደበኛ ስብሰባወችን አጀንዳወቹን እያንዳንዱ የቦርድ አባል የሰጠውን ውሳኔ በወቅቱ ለአባላቱ ማሳወቅ። እነዚህን ከላይ የጠቀስናቸው ነጥቦች በወቅቱ ከቀረቡት ሃሳቦች ውስጥ የተወሰዱ ናቸው። ዝርዝሩንም በ (August 26,2009) በዚሁ ገጽ ላይ አውጥተን ነበር። አሁንም ሙሉ ሰነዱን ደግሞ ማንበብ ይቻላል። ዋናው ነገር እነዚህ ሃሳቦች ይህን ያህል አምባ ጓሮና ጭቅጭቅ ማስነሳት ነበረባቸው ውይ?
ውድ ምእመናን ሆይ!
በአምላክ ፈቃድ ዛሬ የደረስንበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። ይህንም በጎ ስራ የሰራው የሚወደን አርሱ ራሱ ፈጣሪያችን ነው፤ የሱም መንፈስ በቤተክርስቲያናችን ውስጥ እየጎላ መሄዱን እያሳየን ነው። እናንተ ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ እያለን ነው። እኛም ክብሩንና ፀጋውን እንድንጎናጸፍ አስካሁን አውቀንም ሆነ ሳናውቅ የበደልነውን ሁሉ ይቅር በለን! ብለን ወደ ውድ ቤተክርስቲያናችን እንመለስ። ክፉ ልቦናንና ተንኮልንም ይዘን ወደ ደብሩ አንግባ፤ መልካም ተግባርን ለመፈፀምና እርስ በእራስ መዋደድን ይለግሰን ዘንድ ሁላችንም በአንድ ልብ ሆነን እንጸልይ!
አሜን!!

No comments:

Post a Comment