Monday, January 10, 2011

የቤተክርስቲያናችን ችግርች!!!!!

ቀደም ሲል በዚህ ርዕስ ስር መጻፋችን ይታወሳል፤-
ቀን አልፍ ቀን ሲተካ ነገሮች መልካቸውን ለውጠዋል። መሠረታዊ ችግሮች ግን መፍትሄ ሳያገኙ እንዳሉ ይገኛሉ። የቤተክርስቲያናችን መሰረታዊ ችግር የወያኔ መንግስት በቤተክህነት አስተዳደር ውስጥ ጣልቃ በመግባት አመራሩን ሲለውጥ፤ ከገባንበት ቀውስ ውስጥ መውጣት አለመቻላችን ነው።  ዛሬ እንድታነቡት የምንጋብዘው ከላይ የጠቀስነው የጥቃት በትር የራሳችን ደብር ላይ ያደረሰውን
አለመረጋጋት አስመልክቶ የቀረበ አጭር ዘገባ ይሆናል።  ይህ ደብር ሲቆረቆር ቤተክህነት በአንድ ፓትሪያርክ ጥላ ስር ይተዳደር ነበር። ባለንበት ክፍለ ሃጉር በጊዜው የቤተክህነት ተወካይ ሆነው የተሰየሙት ሟቹ አባታችን አቡነ ይስሃቅ ነበሩ። ቤተክርስቲያናችን ተቋቁሞ ሕጋዊ ፍቃድ አውጥቶ የሚተዳደርበትን ሕግ ደንብ አፅድቆ ሲመረቅ በዚህ በዓል ላይ ከተገኙት አባቶች መሃል አንዱ የቀድሞው አባ ጳውሎስ፤ የዛሬው የወያኔ መንፈሳዊ ጉዳዮች ተወካይ አባ ገ/መድህን ነበሩ። እምነታችን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት መሠረት ሆኖ አስተዳደሩ ግን ከሲኖዶሱ ውጭ ራሱን በራሱ የሚያስተዳድር በምእመን የትቋቋመ ደብር መሆኑን የሚገልጽ አንቀጽ
ወጥቶለት በመተዳደርያ ደንቡ ላይ ተካቶ ቤተክህነት የተቀበለችው ሕገ ደንብ አውጥቶ የተቋቋመ ደብር ነው።
ሁላችሁም እንደምታውቁት ወያኔ በቤትክህነት አስተዳደር ውስጥ ጣልቃ በመግባት የመደበውን የመንፈሳዊ ጉዳዮች ተወካይ በተቀበሉና ይህንን አሠራር በተቃወሙ አባቶች ማካከል መከፋፈል ተፈጠረ፤ ይህን ድርጊት አንቀበልም ያሉ አባቶች ሃገር ጥለው ተሰደዱ። በዚህም የቀውስ ሰዓት በምእራብ አህጉራት ውስጥ የሚጠቃለለውና በአባ ይስሃቅ የሚመሩት አብያተ ክርስቲያናት የ እኛ
ደብር ጭምር የተሰደዱትን አባቶች ተቀብለው ማስተናገድና አብረው መስራት ጀመሩ። ዛሬ የ “ውጭ ሲኖዶስ” የሚባለው ተቋቋመ። ከጥቂት አመታት በኋላ አባ ይስሃቅ “ገለልተኛ” ብለው ራሳቸውን አገለሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ “ማህበረ ቅዱሳን” ይሚባል ድርጅት ተመሰረተ።
1ኛ፤- የፈራረሱ አብነት ቤተክርስቲያን አድሳለሁ፤
2ኛ፤- ወደሌላ ሃይማኖት የኮበለሉትን ወጣቶች እመልሳለሁ በማለት መንቀሳቀስ ጀመረ።
ክጥቂት አመታት በኋላ በአሜሪካን ሃገር ውስጥ “የምእመናንና የካህናት ጉባኤ” የሚባል ድርጅት ተቋቋመ። በወያኔ የመንፈሳዊ ጉዳዮች ውስጥ ተወልዶ የጎለበተው ማህበረ ቅዱሳን በአጭር ጊዜ ውስጥ ታዋቂና ጠንካራ ድርጂት ሆኖ ወጣ። በቤተክርስትያንም ውስጥ በወያኔ የተፈጠረውን ቀውስ በክፍተኛ ደረጃ እያሰፋ የራሱን ድርጅት ግን እያሳበጠ ሄደ፤ ምእመናኑን ከቤተክርስቲናኑ
እየገነጠለ በድርጂቱ ውስጥ በአባልነት ማደራጀትን ስራ ብሎ ተያያዘ፤ እነዚህኑ ምእመናን ለቤተክርስቲያን የሚከፍሉትን አሥራት አቁመው ለማህበረ ቅዱሳን ድርጂት የአባልነት መዋጮ እንዲከፍሉ አስደረገ። ለቤተክርስቲያኑ ግን በወር አንድ ብር ብቻ መክፈል ተገቢ መሆኑንና ከዚያ በላይ መክፈል እንደማያስፈልግ ማስተማርን ተያያዙት ። መምህራንን፤ ቀሳውስትን፤ጳጳሳትን ቤተክርስቲያን ከምትከፍለው በላይ ድጎማ በመስጠት መቅጠር ጀመረ። ቤተክርስቲያናትን የሚረዳና የሚደግፍ ሳይሆን እራሱን እያሳደገ ቤተክርስቲያንን ይሚያቆረቁዝ ድርጀት ሆነ። የ አባላቱም ታማኝነት ለፈጣሪያቸው አገልግሎታቸውም ለደብራቸው መሆኑ ቀርቶ
ለማህበረ ቅዱሳን ብቻ እንዲሆን አስደረገ።
የዚህን ድርጅት አካሄድ የተረዱትን አባቶች መስደብ፤ ማዋረድ፤ ማሳደድንም እንደሙያ ተያያዙ። ያስተማሩትን ትምህርት እየከለሱና ያላሉትን አሉ በማለት ላልጠበቀ ምእመን በማሰራጨት ህዝቡን አወናበደ። አልፎ ተርፎም ማውገዝ፤ የቅጽል ስም ማውጣትን እንደሙያ ተክኖት ይገኛል። ባህር ተሻግሮ አሜሪካን ድረስ በመምጣት የድርጅቱን አድማስ አስፍቷል። አሜሪካ ውስጥ ደግሞ ተባባሪ ሆኖ ካቋቋመው ሲኖዶስ ውስጥ “ገለልተኛ” በሚል ስም መጥሪያ ራሱን ያገለለው ስብስብ፤ ክዎያኔ መንፈሳዊ ጉዳዮች ተቋም ጋር በሰፊው የስራ መረቡን ዘረጋ። በሩንም ለማህበረ ቅዱሳን ያለግድብ ክፍቶ ድርጂቱ እንዲደራጅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አደረገ። ማህበረ ቅዱሳንም የገለልተኛ ቤተክርስቲያናትን ገንዘብ ያለቁጥጥር ተጠቀመበት። ሕግና ደንባቸውን ሰብሮ ቤትክርስቲያኖችን ለወያኔ ለመስጠት በቅጥረኝነት ሰራ። ከዳር ሆነው ይህን ሕገወጥ ምዝበራ የተመለከቱ ለጥቅም ያደሩ አባላት እንደማህበረ ቅዱሳን ያለ
የራሳቸው ድርጂት አቋቋሙ።የ “ምእመናንና የካህናት ጉባኤ” ብለው ድርጂታቸውን ሰየሙ። አባታችን አባ ይስሃቅ ከዚህ አለም በሞት ሲለዩ የገለልተኛ ቤተክርስቲያናት ሁሉ ያለ አባት ቀሩ፡ ከላይ የጠቀስናቸው ሁለት ድርጂቶች ቤተክርስቲያኖችን ከ አምልኮት ሥፍራ ወደ ጠላት ስርአት አልባኝነት አሸጋገሯቸው። በተጭማሪም የወያኔ፤ የአማራ ልማት ማህበር (አልማ)፤ ደጀን የፖለቲካ ቡድን እና የ ወ/ሮ አዜብ ጎላ ቤተሰቦች ግንባር ቀደም የጥፋት መልእክተኞች በመሆን ቀን ከሌሊት ይሄው እንደምታዩአቸው በመስራት ላይ ይገኛሉ። በኛ ደብር ውስጥ የተከሰተው ቀውስ በሙሉ በእነዚህ ድርጂቶች አማካኝነት የተሰነዘረ የጠላት፤ የጥፋት ፍላጻወች ናቸው። ከጥፋቶቹ መሃል ጥቂቱን እንመልከት። ማህበረ ቅዱሳን የደብራችን መዘምራን ወደ ኦስተን በመሄድ መቅደስ በመድፈር ሁከት ፈጥሯል። ወደ ዕርቪንግ ማርያም በመሄድ ተመሳሳይ ፅረ ቤተክርስቲያን ስራ ሰርቷል። በእራሳቸን ደብር ውስጥ ሁለት ጊዜ በመደጋገም ፅያፍ ስራውን ፈፅሟል። የማህበረ ቅዱሳን አስተባባሪ የነበረው ዲያቆን ነኝ የሚለው አለማየሁ ደስታ በዘመዱ ያን ጊዜ የቦርድ አባል በነበረው በአቶ ኪዳኔ ምስክር ግፊት የቤተክርስቲያናችን አስተዳዳሪ በነበረት ወቅት ስራውን በገዛ ፍቃዱ ሲለቅ፤
 አንድ፤- የማህበር ቅዱሳን ደጋፊ ነን የሚሉ የቦርድ አባላት፤
 ሁለት፤- የማህበረ ካህናት አባላት የሆኑ መሪዎች በገዛ ፍቃዱ የለቀቀን አስተዳዳሪ ያለምንም ስራ ተዋጽኦ ሳያደርግ ከስድስት ወር በላይ ደመወዝ ከፍለዋል። ከዚህም በላይ የአቶ ኪዳኔ ምስክር የቦርድ አባል ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ ጥሩ አየር ፍስሃን እና ሌሎች አባሎቻቸውን በማስተባበር ቤተክርስቲያን ከሰው ሙግት ላይ ይገኛሉ።
አቶ እዮኤል ነጋ የ “ማህበረ ካህናት” ዋና ጽሃፊ ናቸው፤ በሳቸውም ስም የወጣ የዳላስ የ ቀረጥ ነጻ (501.c) ያላቸው በቤተክርስቲያንም ስም ለራሳቸው ገንዘብ ሰብሳቢ የሆኑ ግለሰብ ናቸው።  ባንድ ወቅትም ያውም የቤተክርስቲያናችን ሊቀ መንበር በነበሩበት ወቅት፤ ለዎያኔ የመንፈሳዊ ጉዳዮች ተጠሪ ለ አባ ጳውሎስ የጻፉትን ደብዳቤ ማስነበባችንን አይዘነጋም። አሁንም ደግመው
ማንበብ ይቻላሉ።
ቄስ መስፍንን ማህበረ ቅዱሳን ሲያስቀጥር የአቶ ኢዮኤል ድርጂት ደግሞ ቄስ አወቀ ሲደልልን አስቀጥሯል። ከስራም ሲታገዱ ይህ ድርጂት ህዝቡን ለ ዓመጽ አነሳስቷል። በአሰሪና ሰራተኛ መሃል የተፈጠረውን የአስተዳደር ውሳኔ ማህበረ ቅዱሳን፤ የካህናትና የምእመናን ጉባኤ፤ ከወያኔ ደጋፊዎች ከ ወ/ሮ አዜብ ጎላ ቤተሰቦች ወ/ሮ ፈትለዎርቅ ጎላና ባለቤቷ አቶ ጌታቸው ትርፌ ጋር በመተባበር ቤተመቅደስ ደፍረው ደብሩን የወንጀል ቦታ አድርገው ለማዘጋት የተደረገው ሙከራ በመክሸፉ ሰብአዊ መብት ተረገጠ ብለው ፍርድ ቤት ሄደዋል። የካህናት ማህበርና ይ ወ/ሮ አዜብ ቤተሰቦች ከኋላ ሆነው ይህን ሁሉ ደባ እየሰሩ ዞር ብለው ደግሞ እናስታርቅ በማለት ማወናበድ ላይ ናቸው። ጂራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል የሚባለው አይነት መሆኑን ተረዱ። አመራር ላይ ሆነው ይህን ሁሉ በደል ሲፈጽሙ የነበረውን የአስተዳደር ብልሽት ምእመኑ ተረድቶ ቢያስወግዳቸው በአስታራቂ ሽምግልና ካባ ተጠቅልለው መልሰው ወደ አስተዳደሩ ለመግባት የጀመሩት ሥልት ነው።
በዚህ ጽሁፍ የቤተክርስቲያናችንን ችግሮች ጠቅለል ባለ መልክ ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ አቅርበናል። ይህ ጽሁፍ የወደፊት ቦርድ አባላትን ስትመርጡ በቤተክርስቲያኑ ችግሮች ዙሪያ የሚደረገውን ደባ በቂ ግንዛቤ ካተረፋችሁ የተጀመረው የቤተክርስቲያን የማዳን ርብርቦሽ ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ አባላትን ከሰርጎ ገቦች ለይታችሁ ለመምረጥ ያግዛችኋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።
አንዲሁ በንፃ የወደደን ዓምላካችን ማስተዋሉን ያብዛልን፡
አሜን! አሜን! እንበል።

1 comment: