Friday, May 14, 2010

የኢትዮጵያው ፓትሪያርክ አባ ጳውሎስ የሚካኤልን ደብር በግድም ይሁን በውድ በቁጥጥራቸው
ስር ለማድረግ የማያወላውል ትእዛዝ አስተላለፉ!!
ውድ የቅዱስ ሚካኤል ደብር አባላት በሙሉ!! እንደምን ከረማችሁ?
ፓትሪያርክ ጳውሎስ ወደ አሜሪካን ከላኳቸው እና እዚህም ከመለመሏቸው ካህናት ጋር በ05/12/10 ዓ.ም. ምሽት የቴሌ ኮንፈረንስ (Teleconference) ማድረጋቸው ተረጋገጠ። ከዳላስ ከተማ የስብሰባው ተሳታፊ ከነበሩት መሃል ዋና ዋናዎቹ ፦
1 መነኩሴ ታደሰ አርአያ (ቄስ ታደሰ አርአያ) በሚል መጠሪያ የሚታወቁ- ከባለቤታቸው ጋር  ለአመታት ተጣልተው ተለያይተው ስለነበረ በህገ ቤተክርስቲያን መሰረት ቅስናቸውን ያፈረሱ ሲሆኑ፤ ባለቤታቸውም የጴንጤ ሃይማኖት ተከታይ ናቸው።
· (ሀ) ዘረኛ በመሆናቸው ቤተክርስቲያንን ጥለው የወጡ
· (ለ) በወያኔ ድጋፍ ተክለሃይማኖት/አቡነ አረጋዊ የሚባል ቤተክርስቲያን ያቋቋሙና የሚመሩ።
2 ርእሰ ደብር ሞገስ እጅጉ በ2006 ዓ.ም. በቤተክርስትያናችን ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁከት አስነስተው ምእመኑን እርስ በራሱ አጣለተው ቤተክርስትያንን ለሁለት የከፈሉ፦
 ለዚህም ስራቸው የገንዘብ ድጋፍ ከአቶ ሃይሉ እጅጉ የተቀበሉ
 ባሁኑ ሰአት በአባ ጳውሎስ ስር የሚተዳደር የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን መሪ፦ 
3 መላከሳህል አወቀ ሲደልል፦ ደብራችንን ለአባ ጳውሎስ ለመስጠት ባደረጉት እንቅስቃሴ ከቤተ ክርስትያናችን የተወገዱ፦
 ሻለቃ ተፈራወርቅ አሰፋ
 አቶ በትሩ ገ/እግዚአብሔር
አቶ ተኮላ መኮንን
አቶ ሃይሉ እጅጉ፤ የተባሉ ግለሰቦች የሚገኙበት አስር ሰዎችን ያዋቀረ ኮሚቴ አቋቁመው የትግል ጓደኛቸው ርእሰ ደብር ሞገስ እጅጉ እንዳደረጉት፤  ሁለተኛውን ዙር የቤተክርስትያን ሁከት ያቀነባበሩ፡
ለአምስተኛ ጊዜ ቤተክርስትያናችን ላይ የተፍከፈተውን ክስ ከአቶ ሃይሉ እጅጉ በተገኘ  ገንዘብ አቶ ተኮላ መኮንንና አቶ ጸሃይ ጽድቅ ቤተማርያም በተባሉ ግለሰቦች በኩልእያስፈጸሙ ያሉ፤
 በቅርቡም ሌላ አዲስ ኮሚቴ አቋቁመው ደብሩን ለማፍረስ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ሲሆን።
በቴሌ ኮንፈረንሱ ላይ የወያኔው ፓትሪያርክ ለውይይት ካቀረቧቸው አጀንዳወች መሃል አንዱ ስለ ዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ደብር ነበር።
በዳላስ አካባቢ የተመደቡት ካድሬ ካህኖቻቸው በአንድነት መቆም ሲገባቸው በግል ጥ ቅምና ዝና እየተጠላለፉ ዌር ሃውስ (Ware house) ውስጥ ጥቃቅን ቤተክርስትያናት መክፈታቸው እንዳሳሰባቸው ክገለጹ በኋላ ይህም አሰራር ህዝቡን በአንድ ጥላ ስር አሰባስቦ ለመግዛትና ለማራቆት አመች ስላልሆነ በዚህም ምክንያት ራሳችሁን እንኳ ችላችሁ ለመቆም የገንዘብ እጥረት ችግር ደርሶባችኋል። ስለዚህ፦
1 በመሃላችሁ ያለውን ቅራኔ ባስኳይ አስወግዳችሁ ተቻችላችሁ በአንድነት እንድትሰሩ ፡ 
2 ውህደት ካደረጋችሁ በኋላ በህብረት ሚካኤልን በእኔ በትረ ስልጣን ስር  እንድታዉሉ። ለዚህም ስራ የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ወጭ እንደሚልኩ ቃል ገብተዋል።
3 በእርሳቸው ስር የሚተዳደሩት በአሜሪካ ዉስጥ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ በዚህ ትግል ላይ በሚቻላቸው ሁሉ ትብብር እንዲያደርጉ አዘዋል።
ውድ ምእመናን ሆይ! ይህ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ የሚጀመር አዲስ እቅድ ስለሆነ ቤተክርስቲያናችንን ነቅተን መጠበቅ አለብን።
ተግተን ወደ እግዚአብሄር እንጸልይ!!

No comments:

Post a Comment