Tuesday, May 11, 2010

የሌባ አይነ ደረቅ! መልሶ ልብ ያደርቅ!!!!

ውድ ምእመናን ሆይ! እንደምን ከረማችሁ? የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ሲመሰረት የነበራችሁ ሰዎች እንደምታስታውሱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መንበሩ አዲስ አበባ ላይ ሆኖ በአንድ ፓትሪያርክ ስር ይተዳደር ነበር። ዛሬ የምናየው ክፍፍል ባልነበረበት ሰዓት ላይ የተቆረቆረው ደብራችን በመተዳደርያው ደንብ ( By Law) ላይ ቁልጭ ብሎ እንደተጻፈው፦
1ኛ፦ እምነታችን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት መሰረት የሚከናወን ሲሆን

2ኛ፦ አስተዳደሩ ደግሞ ከአባል ምእመናን ውስጥ በሚመረጡ የቦርድ አባላት እንደሚፈጸም ይደነግጋል።



ይህ ደብር ራሱን ችሎ የቆመ ሲሆን፤ ከቤተ ክህነት አስተዳደር ውጭ የተደራጀ ቤተክርስትያን ነው። ቅድስት ቤተክርስትያናችን ዛሬ ባለችበት ፈታኝ ዘመን ደግሞ ከእህት ቤተከርስትያናት ጋር የገለልተኝነት አቋም ይዘን እንገኛለን። ይህንን አቋማችንን ለውጠው በአባ ፓውሎስ አስተዳደር ስር ሊያካትቱን የሚታገሉን፦
1 ማህበረ ቅዱሳን

2 የምእመናንና የካህናት ጉባኤ የሚባል ድርጅት

3 የወያኔ ካድሬዎችና ደጋፊዎች በተለያየ ዘዴ ምእመኑንና ቤተክርስትያናችንን እየተፈታተኑት ይገኛል። ለምሳሌm:-
ሀ፦ አምስት ጊዜ ፍርድቤት ከሰዋል። ከነዚህም ሁለቱን ፍርድ ቤቱ ውድቅ ሲያደርገው፤ ሶስተኛው የተጭበረበረ ስለነበረ በራሳቸው ሰርዘዋል። አራተኛ ይግባኝ ብለው እየጠበቁ ሳለ፤አምስተኛውን ክስ ስማቸውንና ፍርድ ቤት ለውጠው ሰሞኑን ከሰዋል።

ለ፦ ማህበረ ቅዱሳን ቦርዱንና አስተዳደሩን በተቆጣጠሩበት ሰዓት ከ 1.2 ሚሊዮን እስከ 1.5 ሚሊዮን የነበረውን የቤተክርስትያን ካሽ (Cash) ወደ 800 መቶ ሽህ ብር አድርሰዉታል። በሟቹ በአቡነ ይስሃቅ ስም ተከፍቶ በነበረው የባንክ ሂሳብ ውስጥ 450 ሽህ ብር የት እንደደረሰ አይታወቅም።
አቶ አበራና ዶር ግርማ የቦርድ አባል ሆነው እንደተመረጡ፦

1ኛ፦ ቤተክርስቲያናችን የገንዘብ አያያዝና የሂሳብ አሰራር ችግር እንዳለበት ሲረዱ ይሄንኑ ጉዳይ ለቦርድና ለህዝብ አሳወቁ።

2ኛ፦ አመታዊ የሂሳብ ኦዲት ሲዘጋጅ በማህበረ ቅዱሳንና በአቶ ኪዳኔ ምስክር አማካኝነት ወጭ የሆነውና ደርሰኝ ያልተገኘለት 139 ሽህ ብር ቤተክርስቲያኑ ላይ ምንም የሚያደርሰው ጉዳት ስለሌለ እንደጠፋ ገንዘብ እንዳይቆጠርና የኦዲት ሪፖርት ዉስጥ መግባት የለበትም በማለት የቦርዱ አባላት ያዘጋጁትን ሰነድ ስለተቃወሙ፦
እነዚህ ግለሰቦች ትክከለኛ ስራ ለመስራት ባደረጉት ጥረት በጥቅም የተሳሰረ ቀለበት ውስጥ ያሉ ግብረአበሮች ተባብረው በሃሰት ብር ሰርቀዋል በማለት ወንጅለው ከቦርድ እንዲወገዱ ለማድረግ የተሰራውን ሴራ ሁላችሁም አትዘነጉትም።

“ሌባ እናት የገዛ ልጇን አታምንም እንዲሉ “ እኛ መዝረፍ ካልቻልን ሌላውን ሰው ሁሉ ሌባ ነው እያልን እርስ በርሱ እናበጣብጥ ብለው የጠነሰሱት ውንጀላ ነበር። ሆኖም አልተሳካላቸውም።

የአስተዳደር ቦርድ የክህነት ማዕረግ አይሰጥም። ለዚህም ስልጣን የለውም። ሆኖም ግን ቀሳውስትን ይቀጥራል። ስራ ላይም ይመድባል። ይቆጣጠራል። ደመወዝ ይከፍላል። ሲያጠፉም አስተዳደራዊ ውሳኔ ይሰጣል። ሁሉም ካህናት ሲቀጠሩ ይህንን አሰራር እያወቁ ወደው ተስማምተው ተቀጥረዋል። ይህም በመተዳደርያ ደንቡ ውስጥ (By Law) በግልጽ የተቀመጠ ነው። ቦርድ የምንመርጠውም ይህን የመሰለ አስተዳደራዊ ስራዎችን አንዲሰራ ነው።
ውድ ምእመናን ሆይ!

ሀቁ ይህ መሆኑን ተገንዝባችሁ ይህች ቤተክርስቲያን ለልጆቻችን እንጅ ለሌላ ልትሆን እንደማትችል ከላይ ስማቸው ለተጠቀሰው ድርጅቶችና ለአባሎቻቸው “የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ለብ ያደርቅ” ብላችሁ የማያወላውል ማስጠንቀቂያ እንድትለግሷቸው እየጠየቅን፤ ሁላችንም በጸሎት እግዚአብሔርን እንድንለምን፤ የስነስርአት ጉድለትን በሕግ እንድናስከብር፤ ቤተክርስቲያናችንን ዘውትር ሌትም ሆነ ቀን በተጠንቀቅ እንድንጠብቅ፤ ቢጽ ሃሳውያንን እንደተኩላ ከተሰገሰጉበት ከመሃላችን ነቅሰን እንድናወጣ እግዚአብሔር በቸርነቱ ይርዳን!! ቅዱስ ሚካኤል ቤቱን ለማፍረስ ታጥቀው የተነሱትን ሴረኞችና ዘራፊዎች በሰይፉ ይጎብኛቸው።

ቸሩ ፈጣሪያችን ለሁላችንም የሚያስተውል አእምሮ ይስጠን! አሜን!!

1 comment:

  1. Senbete, look what I found. Betru Gebregziabher and Yilma Feleke as the representatives of St. Michael Ethiopian Orthodox Church in Garland. They have been scamming DFW International Community Alliance (dfwica) and DFW community. The actual board of St. Michael Ethiopian Orthodox Church in Garland have responsibilities to request dfw international community alliance in writing in order for the organization to remove the St. Michael Church's name from the fabricated biography of Betru Gebregziabher and Yilma Feleke. St. Michael Church board should request what ever document Betru and Yilma have presented in the name of our church to dfwica to become its board members. The church have the rights to know and have all the required information in order to protect the church from becoming victimized with fraud and misrepresentation in the future.


    Note:
    Yilma Feleke, www.dfwinternational.orgYilma Feleke serves as chairman of the Mutual Assistance Association for The Ethiopian community (MAAEC) in Dallas and as chairman of the Social Committee at St. Michael Ethiopian Orthodox Church in Garland.

    DFW INTERNATIONAL COMMUNITY ALLIANCE BOARD OF DIRECTORS FOR 2010 ...
    File Format: PDF/Adobe Acrobat - Quick View
    for the Northwood University Alumni Leadership Council. AFRICAN LEADERSHIP COUNCIL: Betru Gebregziabher is Speaker of the Ethiopian Leadership .... chairman of the Social Committee at St. Michael Ethiopian. Orthodox Church in Garland. ...
    www.dfwinternational.org/about_us/Board_of_Directors.pdf - Similar” Betru Gebregziabher is Speaker of the Ethiopian Leadership .... of the Social Committee at St. Michael Ethiopian. Orthodox Church in Garland.www.dfwinternational.org


    Eder, Mutual Assistance Association for the Ethiopian Community in DFW
    File Format: PDF/Adobe Acrobat - Quick View
    responsibilities, and titles of the Dallas Ethiopian community Funeral Assistance (DECFA) to operate under the auspices of the Mutual Assistance Association ...
    www.maaecdallas.org/Edir_rRegulations_English.pdf,
    http://www.maaecdallas.org/


    Mortgage and businesses scamming king Betru Geberegziabher and his wife Amsale at Tennessee Court: In the Court of Appeals of Tennessee at Jackson January 25, 2201 Session.

    Betru Gebregziabher and his wife Amsale, a mortgage banker, not only have been stealing the money of many Ethiopians here in Dallas and Memphis Tennessee, but those of the Americans also. Betru Gebregziabher and his wife scammed, wiped clean John Kauffmans'(see page 1 and 2 ‘OPINION’of the court) and when the case was presented to the Court of Appeals of Tennessee, Betru and his wife Amsale filed for bankruptcy and fled to Dallas, where they found new victims to take advantage of, thirty thousand innocent Ethiopians of whom to wipe clean of their property and savings in the name of investments and mortgage fraud. Betru, made a deal on the same how over and over and over without reviling the Kaufmans' deed as you see it from the court report. Therefore be careful all when you are doing business with Betru. In order to educate yourself how to protect your money and your family form this scamming team please Visit, (IN THE COURT OF APPEALS OF TENNESSEE AT JACKSON INDYMAC MORTGAGE ...www.tsc.state.tn.us/opinions/tca/PDF/014/Indymac.pdf)

    ReplyDelete