Tuesday, March 16, 2010

እውነትን በግልጽ እንዲያሳየን ለፈጣሪያችን ጸሎት እናደርስ!!


አቶ ጌታቸው የተባለው በሳምንት አንድ ቀን ላንድ ሰአት የቤተክርስቲያኑን ሂሳብ ለማዋቀር ገንዘብ የሚበላው ሂሳብ አዋቃሪ አቶ እዩኤል ነጋ አቶ ሃይሉ የድሮው ቦርድ ጸሃፊ አቶ አክሊለ ድሮ አስረኛ ክፍል ሳይጨርስ አዲስ አበባ አፍሪካ ማህበራዊ ድርጅት እርሳስና ወረቀት ለጸሃፊወች ለማደል የተቀጠረ ተላላኪ መቸም ስደት ለወሬ ይመቻልና ሂሳብ ክፍል ጸሃፊ ስለነበርኩ የሂሳብ አያያዝ አውቃለሁ የሚለውና አቶ መላኩ ጋር ሆነው ሁለቱን የቦርድ ተመራጮችን በሃሰት ከሰን አናባርራቸውና የድሮው ቦርድ እንደነበረ ይቀመጣል በማለት ክስ ሲጠነስሱ እባካችሁ ይቅርባችሁ ያላቸው ግለሰብ አንደሰማው ሁሉ በተለይም አቶ ጌታቸው ካልሆነልንና እዩኤል ክስልጣን ከወረደ ስራውን እለቃለሁ ብሎ በገባው ቃል ኪዳን መሰረት የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ሰሞኑን እንደሚያስገባ ይናገራሉ።
ከመልቀቁ በፊት ግን አዲሱ ቦርድ አዋቂ ሂሳብ ተቆጣጣሪ ተቀጥሮ ሂሳቡን ወደ ኋላ ተመልሶ ማጣራት አለበት በማለት ያቀረበው ፕላን ያስደነገጣቸው ከላይ የተጠቀሱት አብረው ቤተ ክርስቲያኑን ሲበዘብዙ የነበሩት አቶ አክሊሉና የቤተ ክርስቲያኑ ከሳሽ ባለቤት አቶ ኪዳኔ፡ አቶ ጌታቸውን ስራውን ለመልቀቅ ደብዳቤ ክማቅረቡ በፊት የድሮውን ሰነድ ሁሉ አንዲያጠፋ በተመከረው ምክር መሰረት ወይዘሮ ተዋበች የተባሉት የቦርዱ አባል ጋር ካርቶን ሞልተው የቤተክርስቲያኑን የሂሳብ ሰነድ እሮብ ቀን ከሰአት በኋላ ግቢው ጭር ባለበት ሰዓት ሊያሸሹ ሲሉ መያዛቸውን ሰምተን በጣም ተደናግጠናል።
አዲሱም ቦርድ ይሄን ሁሉ ነገር እያወቀ ሰነዱን እንዳለ ለማቆየት የውሰደው እርምጃ አስክዛሬ ድረስ ያለ አልመሰለንም። ሰነዱ ገንዘብ የተከፈለበት የቤተክርስቲያኑ ሃብት መሆኑ እየታውቀ ለምን ከቅጥር ግቢ ውጭ ለማውጣት ተሞከረ ብሎ የመረጥነው ቦርድ ያቀረበው ጥያቄና ቃል በገባውም መሰረት ለ ምእመን ያስታወቀው ነገር ስለሌለ መጥፎ ጥርጣሬ ዉስጥ አስገብቶናል። አቶ ጌታቸውም ወይዘሮ ተዋበችም በተለይም ይሂሳቡን ውዝግብ እንዲያጣሩ የተሰየሙት ኮሚቴውች ያልተባሉትን ሂሳብ ለማጣራት የ 2005፡ 2006 ፡ 2007፡ 2008፡2009 ሰነድ እንፈልጋለን እያሉ ሰነዱን ወደ ቤታቸው እየያዙ መሄዳቸውን ሰምተናል። እንደምታውቁት አጣሩ የተባሉት ከሳሹ አቶ ጌታቸው የቤተ ክርስቲያኑን ገንዘብ ባንክ ሳያስገቡ በሉት በማለት ያቀረበውን ሰነድና ተከሳሾቹ የለም አልበላንም በጊዜው ባንክ አስገብተናል መረጃውም ይሄው በማለት ያቀረቡትን የባንክ ሰነድ ማመሳከር እንጅ! በ 2006፣ 2007 ምን ያህል ገንዘብ ገባ ብላችሁ አጣሩ አልተባሉም ነበር። በ 2005 2006 2007 እነዚህ ተከሳሾች የቦርድ አባል እንዳልነበሩ እየታውቀ ለምን ይሆን እነ አቶ አክሊሉና አቶ ኪዳኔ ወይዘሮ አዜብ ጋር የድሮ ሰነድ የሚጠይቁት ብለን መጠየቅና ይኖርብናል።
በዚሁም አኳያ፡ አዲስ ኦዲተር ተቀጥሮ ወደኋላ ተመልሶ ለማጣራት የሚያደርገው ምርመራ በሚጀመርበት ወቅት ሰነዶች ሁሉ ተስተካክለው ባይቀርቡ ወይም ጠፋ ቢባል፦
1ኛ አሁን ያለው ቦርድ
2ኛ የ 2009 የሂሳብ መጉደልን እንዲያጣሩ የተመረጡትና የልተጠየቁበት ቦታ ገብተው መዝገብ ወደየቤታቸው እየያዙ የሚሄዱት የኮሚቴ ተመራጮች
3ኛ የቤተክርስቲያኑ ቅጥረኛ አቶ ጌታቸው
ተጠያቂወችና የወንጀል ስራ ተባባሪወች መሆናቸውን እንዲያውቁልን ለምእመኑ እናሳስባለን። 
ለአቶ ጌታቸውም በተለይ!
ለፍተን የምናገኘውንም የታክሲ ገቢ እንደዚሁ እያጭበረበረ እንዳያራቁተን አደራ እንለዋለን።
ሁለት ሰነድ ለማመሳከር ለተመረጡትም አጣሪ ኮሚቴ! አንዱን ሰነድ ከሌላው ጋር ለማመሳከር እንዴት ከሁለት ሰአት በላይ ሊውስድባችሁ ቻለ? እንኳን እናንተ ሂሳብ አያያዝ አዋቂወች ነን ባዮች ቀርቶ አኛ መሃይሞቹ በተከሳሾቹ በኩል የቀረበውን ሰነድ እዉነት ከባንክ የመጣ ሰነድ ነው ውይስ ልዩ?  ብሎ ማመሳከር  ከ አንድ ቀን በላይ አይውስድም።
ዋናው ተከሳሽ በፊርማ የተረከበውን ገንዘብ በጊዜው ባንክ አስገብቷል ወይ ?
ወይንስ ከሳሹ አቶ ጌታቸው እንዳቀረበው ማስረጃ አላስገባም!
ገንዘቡን በጌዜው አስገብቶ ከሆነ! ተከሳሹ የተውነጀለው በሃሰት ነው!
እንደቀረበውም ክስ መሰረት ካላስገባ! ባስቸኳይ እንዲያስገባ እንዲጠየቅ ለምእመኑ ሃሳብ ማቅረብ እንጅ እናንተው መርማሪ እናንተው ከሳሽ እናንተው ፈራጅ ሆናችሁ ለመቅረብ አስባችሁ ከሆነ ! ህዝቡ እንዲያውቅና ሽፍን አላማችሁን ብሎም የሂሳብ ሰነድ ማሸሻችሁን እንዲያጋልጥ በየ ተራ የምርምር ጥያቄውችን እንዲያቀርብ ለእውነት ቋሚ ሁሉ እናሳስባለን!!!!
በዚሁም አኳያ አት ኪዳኔ የከሳሽ ባለቤት ከመሆናቸውም በላይ የቤተ ክርስትያኑን ገቢ እስከ አስራ ዘጠኝ ሽህ ($19000) ፈርመው የተረከቡትን እስካሁን ስላልመለሱ በዚሁ ሳቢያ ምእመኑ ፊት ከመቅረባቸው በፊት እንዲመልሱ በትህትና እንጠይቃለን!!
ቶሎ ጊዜው ደርሶ እውነትን በግልጽ እንዲያሳየን ለፈጣሪያችን ጸሎት እናደርሳለን:
አሜን!!

No comments:

Post a Comment