Tuesday, March 9, 2010

ለዛሬ  ከhttp://selam-tewahdo.blogspot.com/ ከሚባለው ብሎግ "ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል" በሚል ርእስ ከቀረበው ጽሁፍ አብዛኛውን ይዘንላችሁ ቀርበናል።

“ለ አይ አር ኤስ (IRS) በእጃችን ያለውን ማስረጃ አስረክበን ቤተክርስቲያኑን እናዘጋዋለን! መንግስት እንዲወርሰው እናደርጋለን! በኋላ ለምን እንዲህ አደረጋችሁ እንዳትሉን!” በሚል ርእስ ሰላም ተዋሂዶ በሚባለው የማህበረ ቅዱሳን ድረገጽ (ዌብሳይት) ተቀጥላ ብሎግ ላይ የተጻፈው የዘለፋና የማስፈራሪያ ጽሁፍ ሲሆን፤ እውነትም የሚካኤል ጠላቶች የገመዳቸው ጫፍ ላይ መድረሳቸውን ከጽሁፉ በግልጽ መረዳት ይቻላል።

የሚካኤልን ስእለት የበላ በሙሉ በያለበት እንዳበደች ውሻ እየተቅበዘበዘ ከመሆኑም ሌላ ወያኔው እና ለሆዳቸው የቆሙ ግብረአበሮቹ ከቦርድ አንወጣም ብለው ትንንቅ የፈጠሩትንና ሕዝብ አንቅሮ ተፍቶ ከቦርድ የመነቀራቸውን ይዞ፤ በየሰንበቴው ቤትና፤ በየስርቻው እየተሰበሰቡ ሲዶልቱ መክረማቸው ይታወሳል። “ይህን ሁሉ ያመጡብን ያ ዶክተርና አቶ አበራ ስለሆኑ አመጽ አስነስተን፤ ስማቸውን በክለን፤ ሕዝቡን አደናግረን ከቦርድ ማውረድ እና በምትካቸው ፈትለወርቅን መልሰን ማስገባት አለብን” ተብሎ የተሸረበው ሴራም ስለ ከሸፈባቸውና የዘረፉት የሕዝብ ገንዘብ ሲቆጠቁጣቸው አካኪ ዘራፍ!! እያሉ የሚቀበሩበትን ጉድጓድ ሲምሱ ይታያሉ።

ይሄ ምንም እንኳን ክርስቲያን ነን እያሉ ባደባባይ አዋጅ ከሚያስነግሩ የሚጠበቅ ቢሆንም፤ የዘረፋ ምንጩ ሲደርቅ፤ በሕዝብ ገንዘብ መንደላቀቅ ሲቀርና፤ እቁቡ ሲጓደል ወደሚቀጥለው ደረጃ በመሸጋገር የተለያዩ ወንጀሎችን ከመፈጸም እንደማይመለሱ ስለሚታወቅ ሕዝቡ በተጠንቀቅ አይኑን ከፍቶ እንዲጠብቅ፤ እናሳስባለን።

ሂሳብ አዋቂ ነኝ ባዩ ቡክ ኪፐር ያዘጋጁት እጅና እግር የሌለውና ብዙ ስሕተቶችን ያዘለ ዓመታዊ የሂሳብ ዘገባ ሰንጠረዥ ከነመሸኛው በአጭበርባሪው የቀድሞው ሊቀመንበርና ውሸትን እንደ ልብሰ ተክህኖ በተጎናጸፉት አይን አውጣ የቦርድ ጸሐፊ በነበሩት አማካኝነት ለሕዝብ እንዲሰራጭና ግብርአበሮቻቸውም እስከ ስብሰባው ቀን ድረስ ለስም ማጥፊያ እንደመረጃ እንዲጠቀሙበት ካደረጉ በኋላ የጃንዋሪ አጠቃላይ ስብሰባ ሲደረግ ከላይ እንደተጠቀሰው የወያኔ ተወካዮችና ጥቂት ለሆዳቸው የተገዙ አሽከሮቻቸው ስብሰባውን ሃይጃክ በማድርግ የሂሳብ ሹሙን እና ገንዘብ ያዡን በሐሰት በመወንጀል የመናገር መብታቸውን ገፈው ያዘጋጁትን አጭር ሰንጠረዥ እንኳን ለስብሰባው ተሳታፊዎች እንዳያሳዩም ሆነ ስለሂሳቡ ማብራሪያ እንዳይሰጡ ተደርገዋል።

አንባቢያንን ለማስታወስ ያህል፤ የዚች ያለንባት ሐገር ሕግ፤ እንኳን በሐሰት ለተከሰሰ ቀርቶ ከፍተኛ ወንጀልን ለፈጸመም ቢሆን “innocent until proven guilty” የሚል ነው። ሆኖም ጃንዋሪ 30 ቀን በቤተክርስቲያናችን ውስጥ በወያኔ ተወካዮችና የጥቅም ተካፋዮቻቸው አቀነባባሪነት የተካሄደው ትእይንት ግልጽ ያደረገው ነገር ቢኖር ያሉትንም ሆነ መውጣት የነበረባቸውን የቦርድ አባላት የሚቻለውንም ሆነ የማይቻለውን ሁሉ አድርጎ በነበሩበት ሥልጣን ላይ ለማቆየትና የማህበረ ቅዱሳን አባላትንና  ደጋፊዎቻቸውን ለመመለስ እንዲቻል ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የተደረገ ሴራ ነበር።

ከዚህም ሌላ እነዚህ ሁለት ግለሰቦች የቦርድ አባል ሆነው እንደተመረጡ፦
1ኛ:-  ቤተክርስትያናችን  የገንዘብ አያያዝና የሂሳብ አሰራር ችግር እንዳለበት ሲረዱ ይሄንኑ ጉዳይ ለቦርዱ እና ለህዝብ ስለአሳወቁ እና፤
2ኛ:-  ዓመታዊ የሂሳብ ዘገባ ሲዘጋጅ በማህበረ ቅዱሳንና በአቶ ኪዳኔ ምስክር አማካኝነት ወጭ የሆነው መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሽህ ብር ቤተክርስቲያኑ ላይ ምንም   የሚያደርሰው ጉዳት ስለሌለ እንደጠፋ ገንዘብ እንዳይቆጠርና የኦዲት ሪፖርት ዉስጥ መጨመር የለበትም በማለት የቦርድ አባላትና ሂሳብ አዋቂ ነኝ ባዩ ቡክ ኪፐር ያዘጋጁትን ሰነድ ስለተቃወሙ፤
እግዚአብሔርንና ሕዝብን ለማገልገል ሲሉ በቤተክርስቲያን ውስጥ ይፈጸማል ብለው ያልጠበቁትና ያልጠረጠሩት ረመጥ ውስጥ ገብተው ትክክለኛ ሥራ ለመስራት ባደረጉት ጥረት በጥቅም የተሳሰረ ቀለበት ውስጥ ያሉ ሰዎችን በመንካታቸው በሐሰት ተወንጅለው እንዲወገዱ ለማድረግ የተፈጸመ አድማና ሤራ ነበር። በዚያን እለት በነዚህ ሁለት ግለሰቦች ላይ የተደረገው ሁኔታ ከፍተኛ ወንጀል እንደነበረና በሥም ማጥፋትም ሆነ በሕግ ሊያስጠይቅ የሚችል መሆኑን የትእይንቱ አቀነባባሪዎችና ተዋናያኖች የዘነጉት ይመስላል።

እንዲያውም አልፎ ተርፎ የሂሳቡን ጉዳይ የሚያጣሩ ሶስት ሰዎች መመረጥ አለባቸው ተብሎ ስድስት ሰዎች ተጠቁመው ስድስቱም ሂሳቡን እንዲመረምሩ ተመድበዋል። ጠቋሚዎቹ የወያኔ ተጠሪዎች ሲሆኑ፣ ወሳኞቹና መዳቢዎቹ ደግሞ ሃሳዊው ጸሐፊና አለቃው ናቸው። የሚደንቀው ነገር ይህ አጣሪ ቡድን እነማንን የያዘ ነው ቢባል ሁለቱ የሂሳብ ሊቅ የሆነው ቡክ ኪፐር ዘመዶችና አስቀጣሪዎች ሲሆኑ አንዱ ደግሞ ቤተክርስቲያኗን ሲበዘብዝና ሲያዝበዘብዝ የኖረና የከሳሽ ወገን ነው። ከፊሎቹ ደግሞ የወያኔ ዘመዶችና የጥቅም ተካፋዮች ናቸው። እንግዲህ ፍርዱን ለእግዚአብሔርና ለእናንተ እንተወዋለን።

እንግዲህ ይኸው የወያኔ ግሩፕ የወከላቸው ሂሳብ መርማሪዎች ምን ዓላማ ይዘው ይሆን የተነሱት? በጠየቁት ማስረጃ መሠረት ምንም ነገር ማግኘት ስለተሳናቸው ሌላ ተግባር ላይ የተሰማሩ ይመስላል። ምንአልባትም ቤተክርስቲያኑ ያለውን የሂሳብ ሰነድ ሁሉ ሰብስበው ሰላም ተዋህዶ የተባለው ብሎጋቸው እንደጠቆመው ለI.R.S ለመስጠት ይሆን? ለዚህ ነው ሂሳቡ ሐቀኛ በሆነ ኦዲተር ኦዲት መደረግ ይኖርበታል የምንለው። የምርመራቸውን ውጤት እስከምናይ ድረስ ቸኩለናል።

ትናንት የቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ በመምሰል የሕዝብ ገንዝብ ያለአግባብ በበጎአድራጎት በኩል እየወጣ እየተዘረፈ ነው እያለ ያለቦርድ ፈቃድ ዶኩመንት እያወጣ ለአባላት ሲያድል የነበረው የሂሳብ ሰራተኛ፤ ዛሬ ኢትዮጵያ ሄዶ ተቀብቶ ከመጣ በኋላ ከዘራፊ ጋር አብሮ ተባብሮ፤ ገንዘብ ያዡና ሂሳብ ሹሙ ገንዘብ አጉድለዋል በማለት የራሱን ሂሳብ አላዋቂነት ይሁን ወይም አድር ባይነት አልታወቀም፤ በሕዝብ ፊት ግን በአደባባይ ቆሞ እራሱን አጋልጧል። ይህ ለምን ሆነ? የጤንነት ወይስ የእብደት?

ቤተክርስቲያንን ለአመጸኞች አሳልፎ መስጠት በእግዚአብሔር ዘንድ አስጠያቂ ከመሆኑም ሌላ በምድርም በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን መረዳት የእያንዳንዳችን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ቸልተኝነቱም ያስከተለው ውጤት ይኸው ትናንት ቤተክርስቲያናችንን ከመዝረፍ አልፎ ለመንጠቅ፤ ካልሆነለትም ለማፍረስ በስውር ሲታገለን የነበረው የወያኔና የማህበረ ቅዱሳን ቡድን ከነግብረአበሮቹ ዛሬ ቤተክርስቲያንን በምድራዊ ፍርድ ቤት ከሶ ካንዴም ሁለት ሶስቴ ሞግቷል።

ያም አልሆን ሲል በአደባባይ አይኑን አፍጦና ጥርሱን አግጦ “ሌባ እናት ልጇን አታምንም እንዲሉ” እኛ መዝረፍ ካልቻልን ሌላውን ሰው ሁሉ ሌባ ነው እያልን እርስ በእርሱ አበጣብጠን ካልሆነልን እዛኛው ቤተክርስቲያናችን እንሄዳለን በማለት የራሱን መርማሪ ኮሚሽን አቋቋሞ የሚቀበርበትን ጉድጓድ ሌት ተቀን በመቆፈር ላይ ይገኛል። የዚህ ቡድን የመጨረሻው ውርደቱም “ሰላም ተዋሂዶ በመባል በሚታወቀው ብሎጉ ላይ 'የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ' በሚል ርእስ ዘረፋዬን እንድቀጥል ካላረጋችሁኝ ቤተክርስቲያንን ለአይ አር ኤስ ሪፖርት አድርጌ የያዝኩትንም ዶኩመንት አስረክባለሁ” የሚለው ማስፈራሪያው ነው።

አይ አለመታደል! እንዲህ አይነት ከይሲ የሆኑ አሽክላዎች ከምን ውስጥ ይሆን የሚወጡት? ማንንስ ይሆን የሚያስፈራሩት? የመላእክትን አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን?ወይስ ሌብነታቸውን አውቆ አንቅሮ የተፋቸውን ሕዝብ? አይ አር ኤስ እማ ከመጣ በ”money laundering” ሲዘርፉን የከረሙትን እኩያን የተረገሙ ዋልጌዎች ለቃቅሞ ስለሚያስገባልን ቅዱስ ሚካኤል ገላገለን ነበር።

በተረፈ የተሰወረውን ሁሉ የሚያውቅ፤ የሰውን ሃሳብና ተንኮል እስከ አጥንቱ የሚመረምር፤ ሁሉን ማድረግ የሚችል፤ ለሁሉም እንደስራው የሚከፍለው ኃያሉ አምላካችን ሰላምንና ፍቅርን እንዲያመጣልን፤ የዘራፊዎችንና የበዝባዦችን መረብ እንዲበጣጥስልን፤ ሰይጣንን ከሚካኤል ቅጥር እንዲያርቅልን፤ ለቤተክርስቲያን ጠላቶች ልብ እንዲሰጥልን፤ በንጹህ ልብ የሚያገለግሉትን ደግሞ እንዲባርክልን ጠንክረን እንጸልይ!! የነገሩትን የማይረሳ፤ የለመኑትን የማይነሳ አምላካችን የልባችንን ይሙላልን!! አሜን!! 
ለዛሬ በዚሁ ይብቃን። እግዚአብሔር ሰላምና በረከቱን ያብዛልን።
አሜን!!

No comments:

Post a Comment