Thursday, March 18, 2010

የበተክርስቲያናችን ችግሮች!!!

በአቶ እዩኤል ነጋና በአቶ ጌታቸው ትርፌ የበላይ አቀነባባሪነት ሲመራ የነበረው አስተዳደር ቦርድ ለምርጫው ጥቆማ ከተደረገ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የሰሩትን ስራ በሙሉ ስላነበባችሁ እናመሰግናችኋለን። ዶር. ግርማንና አቶ አበራን ከቦርድ ዉስጥ ለማስወጣት ያዋቀሩት የሂሳብ አገናዛቢ ቡድንም ይህን ህልማቸውን እዉን ለማድረግ የተመረጠ ቡድን አንደሆነም ተገንዝባችኋል። ነገር ግን ይህ ቡድን ሁለቱን ግለሰቦች ብቻ ክቦርድ ማስወጣት አመርቂ ውጤት አያመጣም ብሎ አምኗል። በምርጫው አሸንፈው የገቡትን ጭምር ለማባረር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ደርሰንበታል። የተመረጠበት ደረሰኝ የማመሳከር ስራው እንደተጠበቀው ምንም ውጤት ስላላመጣለት አማራጭ አድርጎ የያዘው የቀድሞው ቦርድ ሆነ አሁን የተመረጠው ቦርድ ተነጋግሮ አብረው መስራት የማይችሉ ስለሆነ ሁሉም የቦርድ አባላት ከስልጣን ታግደው አዲስ ምርጫ ለማካሄድ ተስማምተዋል። የሚመረጡትም አድሶቹ የቦርድ አባላት ቀድሞ የነበረውን የምእመኑን ህብረትና ፍቅር መመለስ የሚችሉ ምርጥ የእኛ ወገን መሆን አለባቸው ብለዋል።
እነዚህ ግለሰቦች
1 የመተዳደርያ ደንቡን ቀድሞ ወደ ነበረው ህግ የሚመልሱ
2 የአባላት የወር መዋጮውን አንደቀድሞ የሚያደርጉ
3 ከሳሾችን ይቅር ብለው ደግሰው የሚቀበሉ ሰዎች መሆን አለባቸው ብለው ያምናሉ።
በዚህ መልክ የሚዋቀር የአስተዳደር ቦርድ አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት ለምን ይሆን?
የቀድሞው ፍቅራችንና ህብረታችን የሚባለውስ ምንድነው?
ውድ አንባቢያን ሆይ! ይህንን ሴራ በደንብ ለመገንዘብ ትችሉ ዘንድ ቀደም ብለው ይሰሩት የነበረውን ስራ ሰሞኑን ተራ በተራ አናቀርብላችኋለን።
ለዛሬው እነዚህን መረጃዎች አብረን አናንብብ!

No comments:

Post a Comment