Sunday, March 21, 2010

የቤተክርስትያናችን ችግሮች !!!!

ውድ ምእመን ሆይ!
ዶር. ግርማንና አቶ አበራን በገንዘብ ማጉደል ወንጀል ከሶ ምእመንን በቁጣ ስሜት ቀስቅሶ ከቦርድ ውስጥ ለማባረር የተደረገው ሙከራ መክሸፉ ይታወሳል። በተከሳሾች ላይ የቀረበውን ሰነድና ሁለቱ ተከሳሾች እንደ መረጃ ያቀረቡትን ሪፖርት እንድያጣራ የተሰየመው ቡድን ያደረገው ምርመራ የተጠበቀውን ተጨባጭ ውጤት ማምጣት አለመቻሉም ይፋ እየወጣ ነው። ቀድሞውንም ቢሆን በሃሰት የተቀነባበረ አድማ እንጅ የጎደለ ብር ስለሌለ ውጤት ያመጣል ተብሎ አልተጠበቀም ነበር። የኮሚቴው መመስረትና መቋቋም በእለቱ ሳያውቁትና ሳይጠብቁት ተከሳሾቹ ይዘው የቀረቡት ማስረጃ እፍረት ውስጥ ስለጣላቸው ድርጊታቸውን ህዝቡ እንዳይረዳና እንዳይሰማ ተከሳሾችም ማስረጃወቻቸውን ለህዝቡ በአግባቡ ሳያስረዱ ስብሰባዉን ለመበተን የተደረገ ሴራ ነበር። እንደተለመደው ያቀዱት አላማ ግቡን ካልመታ ህዝቡን ለማወናበድ ይችል ዘንድ ለዚህ ኮሚቴ አዲስ እቀድ ሰጥተውታል። ይህም አማራጭ ሃሳብ
1 የቀድሞ ቦርድ የተከፋፈለ ስለነበር አንድ ወጥ የሂሳብ ሪፖርት ይዞ መቅረብ አልቻለም!
2 አዲሱም ቦርድ ቢሆን እንደተለመደው የተከፋፈለ ስለሆነ ከቀድሞው ቦርድ የተሻለ ስራ ሊሰራ አይችልም!
3 በአዲሱ ቦርድ ውስጥ አደገኛ ሁኔታ የሚያመጡት ተከሳሾቹ ዶር. ግርማና አቶ አበራን ጨምሮ አዲስ የተመረጡት የቦርድ አባላት ናቸው፦
ብለው በሚጠሩት ስብሰባ ላይ ምእመኑን ለማሳመን እየተዘጋጁ ይገኛሉ። በጥቅም የተሳሰረ ቀለበት ውስጥ ያሉ ሰወች ከጀርባ ሆነው ቤተክርስቲያኑን ስለሚመሩ የህዝብ ድምጽ፤ መተዳደሪያ ደንብ፡ ለማስመሰል የተቀመጠ ሰነድ እንጅ ቤተክርስቲያኑ የኛ ነው የፈለግነውን ማድረግ እችላለን ብለው ያምናሉ። ስለዚህ ያለው ቦርድ እንዳለ ወርዶ በምትካቸው የምናውቃቸውን አዲስ ቦርድ አባላት መምረጥ አለብን ብለው አቅደዋል። ውድ ምእመናን ሆይ! በቀረበው መረጃ ላይ የተጠቀሱት ግለ ሰቦች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው።
1 ዲን. አለማየሁ ደስታ
2 ሻምበል ግዛው ገድሉ
3 አቶ አክሊሉ አፈወርቅ
4 አቶ መላኩ ታደሰ
5 አቶ ኪዳኔ አለማየሁ
6 ሟቹ የተከበሩ አቶ ሰይፈ ታደሰ
7 ወ/ሮ ንገሥት መኮነን
8 አቶ በትሩ ገብረእግዚአብሄር ናቸው።
መረጃው ላይ እንደምትመለከቱት ብሩን ከቤተክርስቲያን ለመውሰድ የፈጀባቸው ጊዚ ሶስት ቀን ብቻ ነበር። ቀደም ሲል በበጎ አድራጎት በኩል እርዳታ የጠየቃችሁ ምእመን ሁሉ እንደምታስታውሱት እድለኞች ሆናችሁ ከኮሚቴው እሽ የሚለውን የተስፋ ቃል ለመስማት ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅባችሁ የምታውቁት ነገር ነው። ይህ ቡድን ግን ማመልከቻ ሳያስገባ በቃል ጥያቄ ብቻ ጉዳዩ ባጭር ጊዜ ውስጥ ሲፈጸምለት ይህው ሰነድ ያሳያችኋል። ጠይቁ ይሰጣችኋል እንደተባለው ከጠየቁት በላይ እጥፍ ብር ሲለገሳቸው መረጃው ያስረዳል። በመጨረሻም ቼኩ በማን ስም መጻፍ እንዳለበት አቶ መላኩ ታደሰ ተእዛዝ ሲሰጡና አቶ አክሊለ አፈወርቅም ባስቸኳይ ትእዛዙን ሲፈጽሙ እንመለከታለን። እርዳታ የጠየቀው ድርጅት ማንነት ግለጽ ሆኖ የሚመጣው እንደምታነቡት የፋክስ ትእዛዝ ከተላለፈ በኋላ ነው። በድረ ገጻቸው ላይ እንዳብራሩት በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ስር የተደራጁ የኮሚቴው አንድ አካል ነን ብለዋል። እኛ እስከምናውቀው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በውስጡ የሬድዮ ዝግጅት ክፍልና በቅርቡ የተጀመረው መረዳጃ እድር እንዳሉት እናውቃለን። ይህ ራሱን አንድ ጊዜ “የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ” ሌላ ጊዜ ደግሞ “ብሄራዊ የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ” ዛሬ ደግሞ “ጊፍት ኦፍ ሳይት አላያንስ” በመባል የሚታውቀው ድርጅት የኮሚኒቲው ድርጅት መሆኑን አናውቅም። በየጊዜው ስሙን ለምን እንደሚለዋውጥ ግራ ገብቶናል። የህንን የሚያክል ግዙፍ ድርጅት ነኝ ባይ የራሱን ፍቃድ አውጥቶ ራሱን ችሎ ለመስራት ለምን አቃተው? ቀደም ብለን በጻፍነው ጽሁፍ ላይ የቤተክርስቲያኑ የሂሳብ ሰራተኛ የሆኑት አቶ ጌታቸው ሮቢና የቦርድ ተመራጭ የሆኑት ወ/ሮ ተዋበች ነጋሽ የሂሳብ ሰነድ ሲያሸሹ እንደተያዙ መጻፋችን ይታወቃል። በቀረበው መረጃ ላይ እንደምትመለከቱት እኝህ ው/ሮ ከላይ የተጠቀሰውን ድርጅት በሊቀ መንበርነት ሲመሩ የነበሩት የሟቹ የተከበሩ አቶ ሰይፈ ታደሰ ባለቤት ናቸው።እንዲሁም የተመረጡት የሂሳብ አገናዛቢ ቡድን አባላት የ2005- 2006-2007-2008-2009- ሰነዶች እየያዙ ውደቤታቸው እንደሚሄዱ መጻፋችን ትዝ እንደሚላችሁ ተስፋ እናደርጋለን። መረጃው ላይ የቀረበውም ሰነድ የ2005 ዓ.ም መሆኑን እንድገነዘቡ በዚህ አጋጣሚ አደራ አንላለን። እንዲያው ለነገሩ ለምርመራ የተረፈ ሰንድ አለ ብላችሁ ትገምታላችሁ ወይ?
መረጃው ላይ በዲያቆን አለማየሁ ደስታ በኩል የገንዘቡ ጥያቄ እንዲቀርብ ተጠቁሟል። እኝህ ግለሰብ የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ተብለው ተቀጥረው የቤተክርስቲያኑን ገንዘብ ለማህበረ ቅዱሳን ድርጅት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እንደጅረት ውሃ ሲያፈሱ የነበሩ ሰው መሆናቸውን አትዘንጉ። ዛሬም በወ/ሮ ጥሩአየር ፍስሃ አማካኝነት ቤተ ክርስቲያንን እየከሰሱ ያሉ ግለሰብ ናቸው። ወ/ሮ ጥሩአየር ፍስሃ የአቶ ኪዳኔ ምስክር ባለቤት ሲሆኑ እቶ ኪዳኔ ምስክር የዲያቆን አለማየሁ ደስታ አጎት ናቸው። እንዲያው ለነገሩ አቶ መላኩ ታደሰና አቶ በትሩ ገብረእግዚአብሄር ከአቶ እዩኤል ነጋ ጋር በመሆን ቤተክርስቲያናችን አጠገብ ያለውን ህንጻ ለመግዛት የነበራቸው ህልም በምርጫው ውጤት መጨናገፉን ታውቃላችሁ ይሆን?
የዚህ የአይን ባንክ አምባሳደር የሆኑት አቶ ኪዳኔ አለማየሁ ”የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አለም አቀፋዊ የምእመናን ማህበር” ሊቀ መንበር ናቸው። የቀድሞው ቦርድ ሊቀ መንበር የነበሩት አቶ ኢዮኤል ነጋ ደግሞ የማህበሩ ዋና ጸሃፊ ናቸው። ይህ ማህበር ከፓትሪያርክ ጳውሎስ ጋር በቅርበት የሚሰራ ድርጅት ነው። የዛሬ አራት አመትና ባለፈው አመት መጨረሻ ላይ የዚህ ድርጂት አመታዊ ስብሰባዎች እቤተክርስቲያናቸን ውስጥ ተስተናግደዋል። አቶ እዮኤልን በማስቀደም አባ ቆስጦስን የደብራችን ሃላፊ አድርገው በማስመጣት ቤተክርስቲያናችንን ለፓትሪያርክ ጳውሎስ ለማስረከብ ከፍተኛ ጥረት ያደረገ ድርጅት ነበር። ይህ ህልም ሲከሽፍ መላከ ሳህል አወቀ ተሰማን ያስቀጠረውም ይህ ቡድን ነው። በተጨማሪም አባ ቆስጦስን ጋብዘው መላከ ሳህል አወቀ ሲደልልን የደብራችን አለቃ አድርገው እንዲሾሙ ግፊት ሲያደርግ የነበረው ይህ ማህበር ነበር። ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን በማስመጣት ማህበረ ቅዱሳን እንድንሰራራ ድጋፍ ለመስጠት ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረገ ማህበር መሆኑ መዘንጋት የለበትም። ማህበር ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ የሚገታ ውሳኔ ለማሳለፍ በተደረገው ጥረት ላይ ይህ ድርጅት በወቅቱ በነበሩት የቦርድ ተመራጮች ላይ አሳድሮ የነበረው ተጽእኖ የከሸፈው በቅዱስ ሚካኤል ድጋፍ ነበር። ለዚህ እኩይ ሃሳብ አለመሳካት እንቅፋት ሆኑብን በማለት የቀድሞ የቦርድ አባላት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ማማየንና አቶ ሃይሉ አራጋውን የተመረጡበትን የምርጫ ዘመን ሳይጨርሱ ከቦርድ ለማስወጣት በአቶ ኢዮኤል ነጋ በኩል የተደረገው ሙከራ የተቀነባበረው በዚህ ድርጅት በኩል ነበር። የቀድሞው ቦርድ ሊቀ መንበር የነበሩት አቶ ኢዮኤል ነጋ ማንንም ሳያማክሩ የፈለጉትን ሰው መቅጠር፡ ያልተጠበቀና እጀንዳ ያልተያዘለት ሃሳብ  ከየት መጣ ሳይባል እንኩ ፈጽሙ ብሎ ቦርድን አፍጦ ማስገደድ፡ በግል ኮንትራት መፈራረም፡ ከመተዳደርያው ደንብ ውጭ በማናለኝበት በመስራት፡ የተመረጡ የቦርድ አባላትን ለማስወጣት ለሁለተኛ ጊዜ ሲንቀሳቀሱ ይሄው እያያችሁት ነው። ቦርድ በስነ ስራት እንዳይሰራ አቶ እዮኤል ነጋን በማስቀደም ቤተክርስቲያኑን እያተራመሱ ካሉት ድርጅት መሃል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው ይህ ድርጅት ነው።
ውድ ምእመን ሆይ!
የቤተ ክርስቲያናችንን ችግሮች ሰሞኑን ተራ በተራ እናቀርብላችኋለን፡ ብለን በገባነው ቃል መሰረት የጀመርነውን ዝግጅት በመቀጠል ሰሞኑን ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ስለ ማህበረ ቅዱሳን የተላለፈውን መመሪያ እንድታነቡ እንጋብዛለን።

No comments:

Post a Comment